ማስታወቂያ
ታዳጊ አሜን ጌትነት የ11ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን፣ 17 ዓመቷ ነው። ታዳጊዋ "የፋሽን እልፍ ፍቅር አለኝ" ትላለች። ይህም ከልጅነቷ ጀምሮ የምትወደው፣ የምትሞካክረው የሙያ ዘርፍ መሆኑን ትናገራለች። "ፋሽን ስፌት ብቻ አይደለም" የምትለው አሜን ለራሷ የልደት በዓል የሚሆን ቀሚስም የሠራች ታዳጊ ናት።
ሜላት ደሳለኝ 20 ዓመቷ ነው። በቀጣዩ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ትሆናለች። ከስድስት ወራት በፊት የጀመረችው እና ልዩ ልዩ ፈርጦችን በመጠቀም የመዋቢያ ጌጣጌጦች ማለትም የአንገት፣ የዕጅ እና የጆሮ ጌጣጌጥ ሥራ ማዘጋጀት ወደፊት ለምታልመው እና ልትሰማራበት ላሰበችው ሙያ ጅምር መሆኑን ገልፃለች።
ሁለቱም ታዳጊዎች በዚህ የፋሽን እና የመዋቢያ የሙያ መስክ ትልቅ ደረጃ ላይ የመድረስ ሕልም አላቸው።
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሰለሞን ሙጬ