የ7ኛ ክፍል ተማሪ እና የ15 ዓመት ታዳጊ መሆኗኑን የተናገረችው ረድኤት “ በትምህርት ቤት በተቋቋመው የህጻናት ፓርላማ ውስጥ መሳተፍ የጀመርኩት ከ4ኛ ክፍል ጀምሮ ነው ፡፡ በዚህም በራስ መተማመን አግኝቼበታለሁ ፡፡ ሀሳቤን በሰዎች ፊት መግልጽ እንድችል አድርጎኛል “ ብላለች ፡፡
የ15 ዓመት ታዳጊና የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ህይወት ደምሴ በበኩሏ በፓርላማው በርካታ ታዳጊ ህጻናትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን አንስተው እንደሚወያዩ ገልጻለች ፡፡ በተለይም ተማሪዎችን የሚመለከቱና መስተካከል ያሉባቸው ችግሮች ሲኖሩ ለትምህርት ቤቶች ደብዳቤ በመጻፍ መፍትሄ እንደሚያሰጡ የተናገረችው ህይወት “ በተለይም በአካል ጉዳት እና በአዕምሮ ውስንነት ምክንያት በወላጆቻቸው ከቤት እንዳይወጡ የተከለከሉ ህጻናትን በመለየት አግባብ አለመሆኑን ለቤተሰቦቻቸው ግንዛቤ የመሥጠት ሥራዎችን እንሠራልን፡፡ በዚህም ውጤት አግኝተንበታል “ብላለች ፡፡
ወይዘሮ የወይንእሸት ብረሃኑ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች እና ህጻናት መብት ማስጠበቅ ቡድን መሪ እንደሚሉት የፓርላማዎቹ መኖር ታዳጊ ህጻናት መብትና ግዴታዎቻቸውን በማወቅ በከተማቸው እና በአካባቢያቸው ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ እያስቻላቸው ነው ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ትንቢት ሰውነት
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ