ማስታወቂያ
ባህልን የሚያስተዋውቁት እህትማማች ታዳጊዎች በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በስፋት የሚከበሩት የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል ባህላዊ በዓላት የሴቶችን መብት ነፃነትና ደስታቸውን የሚገልፁባቸው ልዩ ዝግጅቶች ናቸው። በዚህ የክረምቱ ወርም ደምቀው ይከበራሉ። ሚጋን እና ኔቨን በራሳቸው ጥረት እያደረጉ ባህልን ለማስቀጠል፣ ለማስተዋወቅ እና ለማዳበር ጥረት ያደርጋሉ። እነዚህ ታዳጊዎች በተለያዩ የኪነጥበብ ዘርፎች በመሳተፍ እና በመገናኛ አውታሮች ራሳቸውን እና ትምህርታቸውን በማይጎዳ መልኩ ስራቸውን በማስተዋወቅ ራሳቸውንና በውስጣቸው ያለውን ለመግለጥ ጥረት ያደርጋሉ። ለዚህም የቤተሰባቸው እገዛ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ።
#GirlzOffMute #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች
ዘገባ፤ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፤ ሰለሞን ሙጬ