ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2017ማስታወቂያ
የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱን እየሠጡ የሚገኙት በጎ ልቦች በተባለ የረድኤት ማህበር ውስጥ ነው፡፡ በተለይም “ ቁርሴን ለታናሼ “ በተባለውና ማህበሩ በሚያዘጋጀው የተማሪዎች የምግባ ፕሮግራም ላይ ነጻ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱን የጀመሩት በአካባቢያቸው ለሚገኙ ህጻናት “ አንድ ዳቦ ለአንድ ህጻን በሚል መሆኑን የጠቀሱት ታዳጊዎቹ አሁን ላይ “ ቁርሴን ለታናሼ “ በተባለውና ማህበሩ በሚያዘጋጀው የተማሪዎች የምግባ ፕሮግራም ላይ ነጻ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡
“በምንሰጠው አገልግሎት ቤተሰቦቻችንም ሆኑ የሚያውቁን ሰዎች ያበረታቱናል የሚሉት ታዳጊዎቹ ወደፊት ብሌን ተሾመ የሥነ ልቦና ባለሙያ እንዲሁም ታዳጊ ብሌን አንተነህ ደግሞ ንድፍ አውጪ / Disginer / የመሆን ህልም እንዳላቸው ነግረውናል ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ትንቢት ሰውነት
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ