ማስታወቂያ
መሰባሰባቸው የበለጠ ሕብር ፈጥሮ ለሚያቀርቧቸው የሙዚቃ ሥራዎች ውበት ሰጠላቸው። ከትምህርታቸው የሚተርፋቸውን ሰዓት በሀገር ፍቅር ትያትር ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙዚቃ በሕብረት በመዝፈን በልምምድ ያሳልፋሉ። ታዳጊዎቹ ከጦቢያ የቴሌቪዥን ዝግጅት ጋር ሆነው ትልልቅ መድረኮች ላይ የሙዚቃ ሥራ የማቅረብ እድል ያገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ተስረቅራቂ ድምፃቸውን አዋህደው በመድረክ ለታዳሚዎች የሙዚቃ ሥራ ያቀረቡበት ተጠቃሽ ነው።
ይህም ብቻ አይደለም የታዳጊዎቹ እንቁ ዜማ የሙዚቃ ቡድን በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው 23 ኛው ታላቁ ሩጫ ሲከናወን ከርእሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ፣ ከሚኒስትሮች፣ ከታላላቅ አትሌቶች እና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎች ጎን ቆመው የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር የመዘመር እድል አግኝተዋል።
እንቁ ዜማዎች ከፊት ለፊታቸው ብሩህ ተስፋ ይታያቸዋ። ያለፉትም ሆነ በህይወት ያሉት ታላላቆቹ የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ሰዎች ብዙ ታሪክ በሠሩበት ሐገር ፍቅር ትያትር ልምምዳቸውን ሲያደርጉ እነሱም የቀጣይ ዘመን የኢትዮጵያ የሙዚቃ መስክ እንቁ ሆነው የመውጣት ወኔን ሰንቀው ጭምር ነው።#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ