You need to enable JavaScript to run this app.
ወደ ይዘቱ እለፍ
ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
አዲስ ቪዲዮ
አዲስ ድምፅ
ክፍላተ-ዓለም
ኢትዮጵያ
አፍሪቃ
አዉሮጳ
ጀርመን
አርዕስት
ማሕበረሰበ
ሰብአዊ መብት
ጤና
የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ/የአየር ንብረት
ኤኮኖሚ
ማዕቀፍ
ፖለቲካ
ስፖርት
ባህል
አዲስ ድምፅ
አዲስ ቪዲዮ
የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት
ማስታወቂያ
ኤርትራ
ኤርትራ በሰሜን ምስራቅ አፍሪቃ የምትገኝ የቀይ ባህር ዳርቻ ያለት ሀገር ነች። ከሱዳን፣ ከኢትዮጵያ እና ከጅቡቲ ጋር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አስመራ ነው።
ቀጣዩን ክፍል እለፈው በዚህ ርዕስ ስር ያለ አጠቃላይ ይዘት
በዚህ ርዕስ ስር ያለ አጠቃላይ ይዘት
የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብና ግጭት
ኢትዮጵያና ኤርትራ ለረጅም ጊዜ ጋብ ያለ ይመስል የነበረዉን የድንበር ላይ ግጭት እንደገና የጀመሩ ይመስላል። ሰኔ አምስት በተለይ ጾረና በተባለዉ ግንባር የሁለቱ ሃገራት ጦር ተጋጭተው ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ኃይል ከሁለቱም ወገን መገደሉና መቁሰሉ ተዘግቦአል።
የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብና ግጭት
የኢትዮጵያና ኤርትራ የጦርነት ሥጋት
ሁለቱ ሐገራት ዳግም ሙሉ ጦርነት ይገጥማሉ የሚለዉ ሥጋት፤ ጦርነት እንዳይገጥሙ የሚሰጠዉ ምክርና ማስጠንቀቂያም እንደቀጠለ ነዉ።የሁለቱ መንግስታት ወታደራዊ ዝግጅት እና የቃላት እንኪያ ሰላንቲያ ግን እስካሁን አላቋረጠም።
የኢትዮጵያና ኤርትራ ዲፕሎማቶች ክርክር
የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማቶች ባካሄዱት በዚሁ ክርክር የመንግሥቶቻቸውን እርምጃ ትክክለኛነት ለማስረዳት ከመጣራቸው ውጭ መልሳቸው በእውነተኛው ችግር እና መፍትሄው ላይ ያተኮረ አልነበረም ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል ።
ስለ ኢትዮ-ኤርትራ ግጭት መግለጫ እና የተቃዋሚዎች አስተያየት
የኢትዮጵያ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኤርትራ ኃይሎች ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ ይዞታዎች ላይ በመተኮሳቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች የአፀፋ እርምጃ መውሰዳቸውን ተናግረዋል ።
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ ግጭት፣ ስለድንበሩ ግጭት መረጃ ካካባቢው ነዋሪዎች
በህዳሴ ግድብ ግንባታ የተነሱ የካሳ ጥያቄ ፣ የአዲስ አበባው ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይ መጠናቀቅ፣ በ«ዩሮ 2016» የታየው ሁከት
የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ላይ ግጭት
የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ድንበር ላይ ከባድ ጦርነት አካሂደዉ እንደነበር የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠቅሶ ዘገበ። በዘገባዉ መሠረት ከሁለቱም ወገን በርካታ ሰዎች መቁስልና መጎዳታቸዉን የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ረዳ ዛሬ ከቀትር በኃላ አስታዉቀዋል።
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ ግጭት፣ ስለድንበሩ ግጭት መረጃ ካካባቢው ነዋሪዎች
ኤርትራ፦ «በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል»
በኤርትራ የተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው ሲል የኤርትራን የሠብአዊ መብት ይዞታን የሚያጠናዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ። የኮሚሽኑ ሁለተኛ የጥናት ዉጤትን በተመለከተ የኤርትራ መንግሥት ተቀባይነት የሌለው ብሎታል።
ኤርትራ ነፃነትና ጭቆና
በ1941 ከኢጣሊያ የቅኝ አገዛዝ ነፃ የወጣችዉ ኤርትራ ከሐምሳ ዓመት በኋላ ግንቦት 1991 ከኢትዮጵያ ነፃ ወጣች።ታሪክ እራሱን ደገመ እንበል ይሆን።አልንም አላልንም የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አዉጪ ግንባር ተዋጊዎች የኢትዮጵያን ጦር አሸንፈዉ አስመራን ሲቆጣጠሩ የኤርትራዊዉ ደስታ፤ ፌስታ፤ ፈንጠዝያ ያዩ እንደሚሉት ከ1941 የበለጠ ነበር።
ኤርትራ ነፃነትና ጭቆና
በ1941 ከኢጣሊያ የቅኝ አገዛዝ ነፃ የወጣችዉ ኤርትራ ከሐምሳ ዓመት በኋላ ግንቦት 1991 ከኢትዮጵያ ነፃ ወጣች።ታሪክ እራሱን ደገመ እንበል ይሆን።አልንም አላልንም የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አዉጪ ግንባር ተዋጊዎች የኢትዮጵያን ጦር አሸንፈዉ አስመራን ሲቆጣጠሩ የኤርትራዊዉ ደስታ፤ ፌስታ፤ ፈንጠዝያ ያዩ እንደሚሉት ከ1941 የበለጠ ነበር።
ኤርትራ ነፃነትና ጭቆና
የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ
የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ኤርትራን ደጋግሞ ማዉገዝ-ማስጠንቀቁም ምናልባት የማይመቸዉን የአስመራና የሐያላኑን መቀራረብ የትኩረት አቅጣጫን ከኦሮሚያዉ ዓይነት ግጭትና ሁከት ለማስቀየስ አልሞ ሊሆን ይችላል።ባይሆን እንኳ ጋዜጠኛ ሮንግ እንዳለችዉ የዉግዘት፤ ዛቻዉ መደጋገም ኢትዮጵያ ምናልባት ወታደራዊ ጡንቻዋን ልትሞክር ትችላለች ማሰኘቱ አልቀረም
ኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ
ኤርትራ የተመድ ማዕቀብ እንዲነሳላት ጠየቀች
የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ከሰባት ዓመት በፊት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ በተመድ የኤርትራ ቋሚ ተልዕኮ አምባሳደር ግርማ አስመሮም ጠየቁ።
የመኢአድን መግለጫ ፣ ኤርትራ የተመድ ማዕቀብ እንዲነሳላት መጠየቋ
የአውሮጳ ህብረት አስቸኳይ ጉባዔ፣ እስራኤል የምታፈርሰው የፍልስጤማውያን ንብረቶች፣
የመኢአድን መግለጫ ፣ ኤርትራ የተመድ ማዕቀብ እንዲነሳላት መጠየቋ
ኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ
የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ዉዝግብ፤ ጉልበት ሰጭ መድሀኒትና የኢትዮጵያ አትሌትክስ,,,
የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ዉዝግብ
አዋሳኝ ድንበራቸዉም የጦር ሐይል ፍጥጫ፤ ጠብ እና ቁርቁስ ተለይቶት አያዉቅም።አሁን በሰዎች መታገት በተለይ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሐብት እና የሰዉ ሐይል ዋና ዋና ማዕከል ኦሮሚያን በሚንጠዉ ተቃዉሞና አመፅ ሰበብ እንዳዲስ መቀጣጠሉ «የከፋ ይከተላል» የሚል ሥጋት ማጫሩ አልቀረም-እንደ ሮንግ።
የኤርትራ ስደተኞች
በሜዲትራንያን በኩል አድርገው ወደ አውሮፓ በጀልባ ከሚሰደዱ አፍሪቃውያን መካከል አብዛኞቹ ኤርትራውያን እንደሆኑ ይነገራል። በግምት ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጉ ኤርትራውያን፣ ወይም ከሕዝቧ መካከል አንድ አምስተኛው በውጭ ሀገር ይኖራል። ሀገሪቱ በአምባገነን አገዛዝ ስር ያለች «የአፍሪቃ ሰሜን ኮርያ» ነችም ይሏታል።
ኤርትራ ፣የጦር መሣሪያ ማዕቀብ መራዘሙና ተፅእኖው፣ስደተኞችን ለመታደግ የቆረጡት ጀርመናዊ ካፒቴን ፣ የአፍሪቃ ስደተኞች አስተዋፅኦ በአሜሪካ
ኤርትራ ፣የጦር መሣሪያ ማዕቀብ መራዘሙና ተፅእኖው፣ስደተኞችን ለመታደግ የቆረጡት ጀርመናዊ ካፒቴን ፣
ኤርትራ፣የጦር መሳሪያ ማዕቀቡ መራዘም እና ተፅዕኖው
የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ም/ቤት በኤርትራ ላይ በጎርጎሪዮሳዊው 2009 ዓም የጣለውን የጦር መሪያ ማዕቀብ ባለፈው ሳምንት እስከ እስከ ኅዳር፣2016 ዓም አራዘመ። ምክር ቤቱ የወሰደው ይህ ውሳኔ የአውሮጳ ኅብረት በስደተኞች ጎርፍ የገጠመውን ቀውስ የስደተኞች መፍለቂያ ከሆኑት ኤርትራን ከመሳሰሉ ሃገራት ጋር ባንድነት መፍትሔ ለመሻት በያዘበት ወቅት ነው።
ኤርትራ ለተመድ ፀጥታ ምክር ቤት ያቀረበችዉ ጥያቄ
ኤርትራ በርካታ ዜጎችዋ ሃገርዋን እየለቀቁ ለአስከፊ ስደት የሚዳርጉበትን ሁኔታ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት እንዲያጣራ ጥሪ አቀረበች። የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢውን ፍርድ እንዲያሰጥ የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መግለጫ ጠይቋል።
የተመድ የኤርትራ ዘገባና የጀርመን ሚኒስትር አስተያየት
ተፅዕኖ ማድረግ ይገባናል ይላሉ የጀርመን የምክር ቤት አባል እና በፓርላማው የእህማማቾቹ የክርስትያን ዲሞክራት ህብረት እና የክርስትያን ሶሻል ህብረት ፓርቲ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተጠሪ ፤ ፍራንክ ሀይንሪሽ ።ፖለቲከኛው ከዶይቸ ቬለ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።
የተመድ ወቀሳና የኤርትራ ምላሽ
ከአንድ ሳምንት በፊት የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባቀረበዉ መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በራሱ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የመብት ጥሰት ይፈፅማል ሲል ወቀሳ መሰንዘሩ ይታወሳል።
ኤርትራ-ሥርዓቷና ስደተኞቿ
ከአፍሪቃ በርካታ ሰዎችች ከሚሰደዱባቸዉ ሐገራት በንግንባር ቀደምትነት የምትጠቀሰዉ ኤርትራ ናት። ባለፈዉ ቅዳሜ ሌሊት ከሊቢያ ወደ አዉሮጳ በመቅዘፍ ላይ የነበረች አንዲት አነስተኛ ጀልባ ተገልብጣ ከስምንት መቶ በላይ ስደተኞች የማለቃቸዉ ሰበብ ምክንያት ብዙ እያነጋገረ ነዉ።አደጋዉ የደረሰበት ምክንያት፤ ስደተኞቹ በተገቢዉ ጊዜ እርዳታ ማጣቸዉ፤
የፕሬዚዳንት ኧል ሲሲ ጉብኝት ፍጻሜ፣ የአውሮፓ የልማት ርዳታ ና ኤርትራ የየመን ጊዜያዊ ሁኔታ የድሬዳዋው የግል ተወዳዳሪ የምርጫ ምልክት፣
የፕሬዚዳንት ኧል ሲሲ ጉብኝት ፍጻሜ፣ የአውሮፓ የልማት ርዳታ ና ኤርትራ የየመን ጊዜያዊ ሁኔታ የድሬዳዋው የግል ተወዳዳሪ የምርጫ ምልክት፣
የአዉሮጳ የልማት ርዳታና ኤርትራ
ከኤርትራ በአደገኛ ሁኔታ ወደአዉሮጳ በገፍ የሚነጉዱትን ስደተኞች ለሀገሪቱ የልማት እርዳታ በመስጠት ለመርዳት ጥረት የሚደረግ ስለመሆኑ የዜና አዉታሮች የአዉሮጳ ኮሚሽንን ባለስልጣናት ጠቅሰዉ ሰሞኑን ዘግበዋል። ሮይተርስ
ኤርትራ 6 ጋዜጠኞችን መፍታቷ፤ በሰዉ እጅ የተገደለዉ ኤርትራዊ ጉዳይ፤ የሳዉዲ ንጉሥ ሕልፈትና ቀብር...
ኤርትራ 6 ጋዜጠኞችን መፍታቷ፤ በሰዉ እጅ የተገደለዉ ኤርትራዊ ጉዳይ፤ የሳዉዲ ንጉሥ ሕልፈትና ቀብር....
ኤርትራ 6 ጋዜጠኞችን መፍታቷ፤ በሰዉ እጅ የተገደለዉ ኤርትራዊ ጉዳይ፤ የሳዉዲ ንጉሥ ሕልፈትና ቀብር...
ኤርትራ 6 ጋዜጠኞችን መፍታቷ
የኤርትራ መንግሥት 6 ዓመት ገደማ በእሥር ላይ ያቆያቸውን ጋዜጠኞች መፍታቱን ፤ ዋና ጽ/ቤቱ በፓሪስ፤ ፈረንሳይ የሚገኘው ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) አስታውቋል። የተፈቱት ለራዲዮ ባና ይሠሩ እንደነበሩ የተነገረላቸው፤ በረኸት
ኤርትራ 6 ጋዜጠኞችን መፍታቷ
የሰብዓዊ መብት ይዞታ በኤርትራ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ልዩ ዘጋቢ የሆኑት ሼኢላ ኬቴሩት ሰኞ ዕለት ጅርጅታቸው ይፋ ባደረገው ዘገባ እንደገለፁት በኤርትራ ባለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ የተነሳ በርካታ የሀገሪቱ ሰዎች ከነዚህም ውስጥ በተለይ ወጣቶች ሀገሪቷን ለቀው ለስደት ተዳርገዋል።
73ኛው የድል በዓል፤ የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት--የቻይናው ጠ/ሚ በኢትዮጵያ---
ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣልያ ላይ ድል የተቀዳጀችበት 73ኛ ዓመት በዓል በመላ ኢትዮጵያ ተክብሮ ውሏል።
የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት እንዲሻሻል መጠየቁ
የቻተም ሃውስ የጥናትና ምርምር ተቋም ባልደረባ ጄሰን ሞስሊ በቅርቡ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በአዲስ መልክ ለማስተካከል ሙከራ እንዲደረግ ሃሳብ አቅርበዋል ።
አልበሺር እና የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ጥረት
የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን አልበሺር በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት ከማጎልበት ጎንለጎን በአካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ። ኣልበሺር ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት የሶስት ቀናት ቆይታ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ
የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሃሳብና ያስከተለው ውይይት
አስተያየት ሰጭዎቹ የሁለቱ ሃገራት የሰላም ውይይት ህዝባዊ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚገባ ከማሳሰብ አንስቶ መሠረታዊ የስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ።
አምባሳደር ሺን ፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ
ኤርትራ በበኩሏ ፣ አምባሳደሩ እንዳሉት ፤ ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ እንድትጠቀም ልትፈቅድ ይገባል።
የአፍሪቃ/ኤርትራ ስደተኞች አበሳ
ሮም የታተመ የኢጣሊያ ጋዜጣ እንደዘገበዉ የሶሪያ ስደተኞችን እንረዳለን የሚሉ ሐይላት ከዘጠና አምስት ስደተኞች ላይ መቶ ሺሕ ዩሮ የሚያወጣ ወርቅ፥ሌላ ጌጣ ጌጥና ገንዘብ ዘርፈዋል።ዶን ሙሴ ዘርዓይ እንዳሉት ደግሞ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን እንረዳለን የሚሉ፥ በተለይ የሚያስተረጉሙ ኤርትራዉን የስደተኞቹን ሚስጥር ለኤርትራ መንግሥት አሳልፈዉ ይሰጣሉ
ኤርትራ፣ የምግብ እጥረት እና የመስኖው ፕሮዤ
በዓለም የምግብ እጥረት የሚታይባቸው አካባቢዎች መዘርዝር ሰንጠረዥ ዛሬ ይፋ ሆኗል። ኤርትራ ዘንድሮም ብዙ ሕዝብ በቂ ምግብ ከማያገኙባቸው ሀገራት መካከል ትቆጠራለች።
ኢትዮ-ኤርትራ፣ ኤሌክትሪክ እንደ መደራደሪያ?
ኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ወደሰላማዊ የድርድር መድረክ ለማቅረብ 250 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል በነጻ ለመስጠት አስባለች መባሉንየሚጠቁም ዜና በድረገጾች እየተነበበ ነዉ።
ኤርትራ ከ20 የነፃነት ዓመታት በኋላ
ኤርትራ ከ20 የነፃነት ዓመታት በኋላ የምትገኝበት የፖለቲካ ማኅበራዊና ኤኮኖሚዊ ሁኔታ እንዴት ይታያል? እቅዶችና ተስፋዎች፤ እዉነታዉና ተቃርኖዉስ?
ኤርትራ ከ20 የነፃነት ዓመታት በኋላ
የኢትዮጵያ አካል ሆና የኖረችዉ ኤርትራ ከ30 ዓመታት ጦርነት በኋላ ተገንጥላ ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች ዛሬ 20ኛ ዓመቷን አከበረች። ኤርትራ ነፃነቷን ስታዉጅ በዜጎች ዘንድ የነበረዉ ተስፋና ስሜት ከእነዚህ ዓመታት በኋላ የደበዘዘና የተመሳቀለ እንደሆነ ነዉ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ኬንያ ስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራዉያንን አነጋግሮ የዘገበዉ።
የአል ጀዚራ ስርጭት እና ኤርትራ
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በኤርትራ የአልጄዚራ ቴሌፂዥን ስርጭት ሳንሱር ተደረገ በማለት ቅሬታውን ትናንት ባወጣው መግለጫው አስታውቋል። የኤርትራ መንግስት ግን የአልጀዚራን ስርጭት ሳንሱር አላደረኩም ሲል ለክሱ መልስ ሰጥቷል።። ገመቹ በቀለ እንደሚከተለው አጠናቅሯል።
የፕረስ ነጻነት፤ኢትዮጵያና ኤርትራ
ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባው ምስራቅ አፍሪቃ ከሶሪያ ቀጥሎ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉ የሚጣስበት አከባቢ ሆኗል። ኤርትራ ለስድስተኛ ጊዜ በመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጥላች።
ጠ/ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ና ኤርትራ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ አስታወቁ። አቶ ኃይለማርያም ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብ በድርድር እንዲፈታ በተለያዩ ጊዜያት መጠየቃቸውን አስታውሰዋል ።
አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቋ
ባህርን ተንተርሳ ወደየምትገኘው ሀገር ኤርትራ እንዳይጓዙ ባለፈው ሰሞን ፤ ማስጠንቀቂያ ማቅረቡ የሚታወስ ነው። ባለፈው ዓመት በሚያዝያ ወርም ተመሳሳይ ማሳሰቢያ ቀርቦ እንደነበረ አይዘነጋም። ምክንያቱ ምን ይሆን?
የኢትዮ-ኤርትራ ጠብና የደቡብ ሱዳን የሽምግልና ሐሳብ
አስገራሚዉ ግን ጥሩዉ ሐሳብ የተሰማዉ የሁለቱ ሐገራት ዉዝግብ ጦርነትም-ሠላምም የለም ከሚለዉ ይልቅ፥ ጦርነት የለም። ሠላምም የለም። ግጭት ግን አለ ወደሚለዉ በናበረበት ወቅት መሆኑ ነዉ...የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት ማረጋገጪያ ለማግኘት ሞክረን ነበር።አልተሳካልንም።
ቀዳሚ ገጽ
ገጽ 12 የ 13
ቀጣይ ገጽ