ኢትዮጵያዊው የሕግ ባለሙያ ተሸለሙ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2012ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊው ታዋቂ የሕግ ባለሙያ ጠበቃ አመኃ መኮንን ፈረንሳይ እና ጀርመን በጋራ የሚሰጡት የሰብዓዊ መብቶች ሽልማት አሸናፊ ሆኑ። ጠበቃ አመኃ ለያዝነው የጎርጎሪዮሳዊ 2019 የፍራንኮ-ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ሽልማት የበቁት ባለፉት ዓመታት ሁኔታው አስቸጋሪ በነበረበት ወቅት ለበርካታ ጋዜጠኞች፣ የድረ ገፅ ጸሐፍት እንዲሁም ፖለቲከኞች ጥብቅና በመቆማቸው መሆኑ በዋናነት መጠቀሱን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የፍራንኮ ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች እና የሕግ የበላይነት ሽልማት በጎርጎሪዮሳዊው 2016 ዓ,ም የተጀመረ ነው። በየዓመቱም በመላው ዓለም ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ለመብት ለሚታገሉ እና እውነት እንድትወጣ ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጥብቅና ለሚቆሙ የሕግ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሽልማት ነው። ጠበቃ አመኃ ሽልማቱ በተለይ ወጣት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንደሚያበረታታ ተናግረዋል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ተሸላሚውን በማነጋገር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ