አነጋጋሪው የጀርመን ግዛቶች የምርጫ ውጤት
ሰኞ፣ ነሐሴ 27 2011ማስታወቂያ
አማራጭ ለጀርመን (AfD) የተባለው ቀኝ ዘመም የፖለቲካ ፓርቲ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍሎች በተካሔዱ ምርጫዎች ድል ቀንቶታል። በሳክሰኒ ግዛት በተካሔደው ምርጫ የመራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ክርስቲያን ዴሞክራቶች ፓርቲ (CDU) 32 በመቶ ድምፅ ሲያገኝ ስደተኛ ጠል እየተባለ የሚወቀሰው አማራጭ ለጀርመን 27.5 በመቶ ድምፅ አግኝቷል።
በበርሊን ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የብራንደንቡርግ ግዛት ግራ ዘመሙ የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ (SPD) 26.2 በመቶ ድምፅ ሲያገኝ አማራጭ ለጀርመን 23.5 በመቶ ድምፅ አግኝቶ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቀኝ አክራሪው የፖለቲካ ፓርቲ በሁለቱ ግዛቶች ያገኘው ድምፅ በጀርመን ዋና መነጋገሪያ ሆኗል። ይልማ ኃይለሚካኤል ተጨማሪ ዘገባ አለው
ይልማ ኃይለሚካኤል
ኂሩት መለሠ