አሳሳቢው የእስራኤልና ኢራን ግጭት-ዉዝግብ
ሰኞ፣ ሰኔ 9 2017አሳሳቢው የእስራኤልና ኢራን ግጭት-ጦርነት
እስራኤል ባለፈዉ በኢራን ወታደራዊ አዛዦች እና በኒውክለር መሰረተ ልማት ላይ ያደርሰችው ጥቃት ብሎም የኢራን ወታደራዊ የአጸፋ መልስ አካባቢውን ወደ ሌላ አስከፊ ጦርነት እንዳያስገባውና የዓለም ሰላምና ምጣኔ ሀብትም እንድይናጋ ያሰጋ ሲሆን፤ መንግስታትና አለማቀፍ ድርጅቶችም ዋና አጀንዳቸው አድርገው ይወያዩበት ይዘዋል።
የአውሮፓ ህብረትና መንግስታት በአሳሳቢው ግጭት
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራም በእስራኤል እርምጃ አሜሪካ እንደሌለችበት ገልጸው፤ ኢራን በተሳሳተ ስሌት በአሜሪካ ጥቅሞች ወይም የጦር ካምፖች ላይ ጥቃት ከፈጸመች ግን አጸፋው አስከፊ እንደሚሆን በመግለጽ የሚሻለው በድርድርና ውይይት ችግሩን መፍታት መሆኑን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ጉዳይ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በስልክ እንድተነጋገሩና እሳቸውም ችግሩ በውይይት መፈታት እንዳለበት እንደሚያምኑ እንደገለጹላቸው ጭምር በማህበራዊ ገጻቸው አስታውቀዋል።: ብርታኒያና ፍረንሳይም ሁለቱ ወገኖች ግጭቱን ከማሳደግና ከማስፋት እንዲቆጠቡ በመግለጽ የችግሩ ምንጭ ነው የሚሉት የኢራን የኒውክለር ፕሮግራም በውይይትና ድርድር እልባት እንዲያገኝ በየበሉላቸው አሳስበዋል። እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌላቸው ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ጨመረ
የአውሮፓ ህብረት በውጭ ግንኑነት ሀላፊ ካያ ካላስ በኩል ባወጣው መግልጫ፤ ኢስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃትና ኢራን በአጸፋው የወሰደችው እርምጃ አደገኛና የመካከለኛውን ምስራቅ በአጠቃላይ፤ የጦርነት ቃጣና ሊያደርግ የሚችል በመሆኑ ሁለቱም ወገኖች ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ ክመውሰድ እንዲቆጠቡና የአለማቀፍ ህግን እንዲያከብሩ ጥሪ አስተላለፏል። በዚህ አሳሳቢ አጀንዳ ላይ ለመወያየት የ27ቱ የህብረቱ አባላ አገሮች የውጭ ጉድይ ሚኒስትሮች አስችኳይ የቪዲዮ ስብሰባ ለነገ የተጠራ መሆኑም ታውቋል።
በካናዳ የሰባቱ ባለጸጋ አገሮች መሪዎች ጉባኤ አንዱ ትኩረት
ከትናንት እሁድ ጀምሮ በካናዳ አልበርታ እየተከሂደ ያለው ፕሬዝዳንት ትራም የሚገኙበት የሰባቱ ባለፀጋ አገሮች መሪዎች ጉባኤም በዋናነት በዚሁ በእስራኤልና ኢራን ጦርነት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል። የባለጸጋዎቹ ጉባኤ በዚሁ ኢስራኤልና ኢራን ግጭት ጦርነት ላይ የጋራ መግለጫ እንደሚያወጣም ይጠበቃል።
የሩሲያና ቻይና የተለየ ሚና የቀጠለው የእስራኤል እና የኢራን ውጥረት
ሩሲያና ቻይና የእራኤልን እርምጃ ቢያወግዙም ችግሩ ግን በውይይት እንዲፈታ ፋላጎታቸው መሆኑን ነው በየበኩላችው የገለጹት ። ኢራን፤ ሩሲያና ቻይና የሚገሚኙበት የብሪክስ ስብስብ አባል ብትሆንም፤ ስብስቡ ግን በአሁኑ ወቅት እንደ ቡድን ገና ተቋም ያልገነባ፤ ወታደራዊ ህብረትም ያልፈጠረና በአባላቱ መካከልም ወጥ አመላካከት የሌለ በመሆኑ፤ ለኢራን ወታደራዊ ድጋፍ ለመስጠት አቅምም ፍላጎትም ሊኖረው እንደማያችል ነው በታዛቢዎች የሚነገረው። ከቡድኑ ውስጥ የኢራን ዋና አጋሮች ናቸው የሚባሉት ሩሲያና ቻይናም በየግላቸው ምክኒያት በወታደራዊ ሀይል ከኢራን ጎን ይሰለፋሉ ተብሎ አይገመትም። ሆኖም ግን ከዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ በተጨማሪ በአደራደሪነት በመሳተፍ ገንቢ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ በሞስኮ የዓለማቀፍ ጥናት ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑት ኒኮላይ ሳርኮቭ ይናገራሉ። “ ሞስኮና ፔጂንግ በኢራን የሚታመኑ ወዳጆች ናቸው፡፤ በማሸማገል ወይም ስምምነት ከተደረሰ ዋስትና በመስጠት በኩል ገምቢ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ በማለት ሁለቱ አገሮች ለኢራን ሊሰጡ ሚችሉትን ድጋፍና አይነቱን አመላክተዋል ።
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ