You need to enable JavaScript to run this app.
ወደ ይዘቱ እለፍ
ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
አዲስ ቪዲዮ
አዲስ ድምፅ
ክፍላተ-ዓለም
ኢትዮጵያ
አፍሪቃ
አዉሮጳ
ጀርመን
አርዕስት
ማሕበረሰበ
ሰብአዊ መብት
ጤና
የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ/የአየር ንብረት
ኤኮኖሚ
ማዕቀፍ
ፖለቲካ
ስፖርት
ባህል
አዲስ ድምፅ
አዲስ ቪዲዮ
የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት
ማስታወቂያ
ቻይና
ከ 1.4 ቢሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሏት የቻይና ህዝባዊት ሪፐብሊክ በዓለም በሕዝብ ብዛት ቀዳሚዋ ናት። ቻይና ራሷን በከፍተኛ ደረጃ ያበለፀገች ሀገር ናት።
ቀጣዩን ክፍል እለፈው በዚህ ርዕስ ስር ያለ አጠቃላይ ይዘት
በዚህ ርዕስ ስር ያለ አጠቃላይ ይዘት
የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም.አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢንቨስትመንት፣ ለቤትና ለመኪና ግዥ የሚውል 50 ቢሊዮን ብር በውጭ ሀገራት ለማኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዳያስፖራ በመጪው 2018 ዓ.ም. ለማበደር መዘጋጀቱን አስታወቀ። ምሥራቅ አፍጋኒስታንን በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 812 መድረሱን የአፍጋኒስታን መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት እንዳለው በአደጋው 2,817 ሰዎችም ቆስለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የጋዛ ሰርጥን እንድትቆጣጠርና ህዝቡንም ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር የወጣውን እቅድ እያጤኑ ነው መባሉን ሀማስ ተቃወመ።
DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2017 የዓለም ዜና
መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ የሱዳን ትይዩ መንግሥት መሪ ሆነው መሐላ ፈጸሙ። የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ አቡ ኡቤይዳ በጋዛ መገደላቸውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ገለጹ። ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ዩክሬን በሩሲያ ውስጥ ጥቃት ለመፈጸም ዕቅድ እንዳላት ተናገሩ። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ቫለሪ ጌራሲሞቭ ሀገራቸው ከመስከረም እስከ ሕዳር ተግባራዊ የሚሆን የጥቃት ዕቅድ ማዘጋጀቷን አስታውቀዋል። የቻይና እና የሕንድ መሪዎች በድንበር ይገባኛል የገቡበትን እሰጥ አገባ በመፍታት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ። ኢትዮጵያዊው ኃይለማርያም ኪሮስና ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሐሰን በሲድኒ ማራቶን የቦታውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል አሸነፉ።
የሰኔ 4ቀን 1017 የዓለም ዜና
-መቀሌ ዉስጥ ዛሬ አደባባይ የተሰለፉ የትግራይ ተፈናቃዮች የክልሉ ፕሬዝደንት ፅሕፈት ቤት የሚገኝበትን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ ገቡ።ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደቀያቸዉ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ በአደባባይ ሠልፍ እየጠየቁ ነዉ።---የኢትዮጵያ መንግስት የሕግ ሒደትንም ሆነ የፕሬስ ነፃነትን እንደማያከብር ሁለት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታወቁ።--ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ካጠቃች የኢራን ጦር መካከለኛዉ ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን እንደሚመታ የኢራን መከላከያ ሚንስትር አስጠነቀቁ።
አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ቀነሱ
አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ለ90 ቀናት በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል።
አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ቀነሱ
አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ለ90 ቀናት በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል። ሁለቱ የንግድ ከባድ ሚዛን ተፋላሚዎች ታሪፍ የቀነሱት ከጥቂት ቀናት ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው በተስማሙት መሠረት ነው። በሥምምነቱ መሠረት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ አሜሪካ ገበያ በሚገቡ የቻይና ሸቀጦች ላይ የጣለውን ታሪፍ ከ145 በመቶ ወደ 30 በመቶ ይቀንሳል። ቻይና በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለችው ታሪፍ በአንጻሩ ከ125 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ይላል። ዶናልድ ትራምፕ በታሪፍ የጀመሩት የንግድ ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያቀዛቅዝ አስግቶ ነበር።
የትራምፕ ታሪፍ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንዳቀዛቀዘ የአይኤምኤፍ ትንበያ አሳየ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያውን ባለፈው ጥር ከነበረበት 3.3 በመቶ ወደ 2.8 በመቶ ዝቅ አድርጓል።
የትራምፕ ታሪፍ የዓለምን ኢኮኖሚ ዕድገት እንዳቀዛቀዘ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ አሳየ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለዓለም ዋና ዋና ኢኮኖሚዎች በጥር የሰጠውን የዕድገት ትንበያ የዶናልድ ትራምፕ ታሪፍ ባስከተለው ውጥረት ምክንያት ከልሷል። ተቋሙ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በ6.6% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርጓል። ትንበያው የኢትዮጵያ መንግሥት በ2017 ከሚጠብቀው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በ1.8 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።
የሚያዝያ 11 ቀን 2017 የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ አስታወቀ። ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን ቃል ገቡ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ፋሲካን ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠል ተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች።
ኢትዮጵያውያን ባሸነፉበት የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ቻይና ሮቦቶች ከሰዎች አወዳደረች
በቤጂንግ በተካሔደው ግማሽ ማራቶን 10,000 ሰዎች እና 21 ሰው መሰል ሮቦቶች ሲሳተፉት ኢትዮጵያውያኑ ኤልያስ ደስታ እና ሐዊ ጉደታ አሸንፈዋል።
የሚያዝያ 8 ቀን 2017 የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ “የመምህራን የኅብረት ሥራ ባንክ” በ2018 ሥራ ሊጀምር እንደሚችል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ፍንጭ ሰጡ። ሚኒስትሩ ከትምህርት የቀሩ 7.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ጉዳይ በጣም ሊያሳስብ እንደሚገባ ተናግረዋል። አልሸባብ በማዕከላዊ ሶማሊያ አዳን ያባል የተባለች ወታደራዊ ማዕከል ላይ ጥቃት ከፈተ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ትይዩ መንግሥት መመሥረታቸውን ይፋ አደረጉ። አሜሪካ በኤርትራ እና በደቡብ ሱዳን ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው። ዶናልድ ትራምፕ "ማስፈራራት እና ሥም ማጥፋት እንዲያቆሙ" ቻይና ጠየቀች። እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይገባ መከልከሏን እንደምትቀጥል አስታወቀች።
የሚያዚያ 1 ቀን 2017 የዓለም ዜና
-በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የክልሉን የግንባታ ሥራና እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉን ባለሙያዎችና ሠራተኞች አስታወቁ።ባለሙያዎች እንዳሉት በግንባታ መስክ የተሰማሩ አብዛኞቹ ባለሐብቶች ወደ አዲስ አበባ ሸሽተዋል።-ባለፈዉ የካቲት ጀርመን ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ የመጀመሪያና ሶስተኛዉን ደረጃ የያዙት የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣማሪ መንግስት ለመመሥረት ተስማሙ።-----ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም የንግድ ተሻራኪዎችዋ ጋር የገጠመችዉ የንግድ ጦርነት እየተባባሰ ነዉ።አንዳድ መንግስታት ከፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር ለመደራደር ጠይቀዋል።ቻይና ግን በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ አፀፋ ቀረጥ ጥላለች።
ዲፕሲክ፤የቴክኖሎጂ አብዮት ያስነሳው አዲሱ የቻይና መተግበሪያ
ዲፕሲክ፤የቴክኖሎጂ አብዮት ያስነሳው አዲሱ የቻይና መተግበሪያ
ዲፕሲክ ከጎግል ፕሌይ እና ከአፕስቶር በነፃ የሚጫን መተግበሪያ ነው።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪፍን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ሥልት የዓለም የንግድ ሥርዓትን አስግቷል
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገራቸዉን የንግድ ጉድለት ለማሟላት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም ታሪፍን እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙ ነው። አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ከካናዳ በምትሸምታቸው ሸቀጦች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል ትራምፕ ያስተላለፉት ውሳኔ ለ30 ቀናት እንዲቆም ተደርጓል። በቻይና ላይ የተጣለው ታሪፍ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን የፕሬዝደንት ሺ ዢፒንግ መንግሥት በአጸፋው በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ተመሣሣይ እርምጃ ወስዷል። ቻይና ጉዳዩን ወደ የዓለም የንግድ ድርጅት እንደምትወስድ ዝታለች። የዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ የታሪፍ ውጥረት የፈጠሩ ሀገራት አደብ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።
የዶናልድ ትራምፕ ታሪፍን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ሥልት የዓለም የንግድ ሥርዓትን አስግቷል
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሐገራቸዉን የንግድ ጉድለት ለማሟላት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም ታሪፍን እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙ ነው።
የትራምፕ አስተዳደር የኤኮኖሚ ጦርነት
ኋይት ሃውስ ከገቡ ጥቂት ቀናት ያስቆጠሩት ዶናልድ ትራምፕ፣ የአሜሪካን ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ የውጪ ግንኙነት፣ ልማትና ሌሎችንም መስኮች እያመሱና እየቀየሩ መሆናቸው፣ ነገስ ምን ያረጉ ይሆን?
DW Amharic የጥር 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ “አሁን ያለውን የፖለቲካ ጩኸት እንዳትመለከቱ” የሚል ጥሪ ለብልጽግና ፓርቲ አባላት አቀረቡ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኦምዱርማን በገበያ ላይ በከባድ መሣሪያ በፈጸመው ድብደባ 54 ሰዎች መገደላቸውን የሱዳን መንግሥት አስታወቀ። ኤርትራ፣ ግብጽ እና ሶማሊያን ጨምሮ ቻይና ከበርካታ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የእስያ ሀገራት እንስሳት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች። የአረብ ሀገራት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያንን ወደ ግብጽ እና ዮርዳኖስ ለማዘዋወር ያቀረቡትን ሐሳብ ውድቅ አደረጉ። ዛሬ ቅዳሜ ሐማስ ሦስት ታጋቾች እስራኤል 183 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቀዋል።
የፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነትና የትራምፕ እርምጃ
ትራምፕ ሀገራቸውን በጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓ,ም ፓሪስ ላይ ከተፈረመው የአየር ንብረት ውል በድጋሚ ማስወጣታቸው፤ የስምምነቱን ፈራሚ ሃገራት እያነጋገረ ነው።
ቻይና በአፍሪቃ ተጽእኖዋን እያጎለበተች ነው
ቻይና ለአፍሪቃ ወታደራዊ ግንባታ የ1 ቢሊዮን ዬን ገንዘብ ቃል ገባች
ምዕራባውያኑ ኃያላን አገራት በተለይም ምዕራብ አፍሪቃ ውስጥ የነበራቸው ተጽእኖ በወቅቱ የአካባቢው ፖለቲካዊ ለውጥ መቀዛቀዙ ለቻይና መልካም አጋጣሚ ይመስላል ።
DW Amharic የሕዳር 08 ቀን 2017 የዓለም ዜና
በጋምቤላ ክልል ከ4 ዞኖች ለ138 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ። ሳዑዲ አረቢያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ሰባት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከ100 በላይ የውጪ ሀገራት ዜጎች በሞት መቅጣቷን AFP ዘገበ። ሒዝቦላሕ ቃል አቀባዩ ሞሐመድ አፊፍ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀ። ሩሲያ በ120 ሚሳይሎች እና 90 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በዩክሬን የኃይል መሠረተ-ልማቶች ላይ ከባድ የአየር ድብደባ ፈጸመች። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉትን የስልክ ንግግር ተከላከሉ። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ከአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልፕ ትራምፕ ጋር ለመሥራት ቃል ገቡ።
የመስከረም 18 ቀን 2017 የዓለም ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የተፈራረመችው የመግባቢያ ሥምምነት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ይጥሳል ሲሉ ከሰሱ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሀገራቸው “ዓላማ በቀጠናው የጋራ ዕድገት እና ብልጽግና መፍጠር” እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች በተራዘመ የብድር አቅርቦት የመጀመሪያ ግምገማ ተስማሙ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በምትገኘው አል-ፋሽር ለሁለት ቀናት በፈጸመው ጥቃት 48 ሰዎች ተገደሉ። የሊባኖሱ ሒዝቦላሕ መሪው ሐሳን ናስረላሕ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጠ።
በብር እና በዩዋን የመገበያየት ስምምነት
ኢትዮጵያ ከቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ጎን ለጎን 17 የመግባቢያ ሰነዶች ስለመፈራረሟ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።
የቻይና እና የአፍሪቃ ትብብር
የቻይና እና የአፍሪቃ ትብብር (FOCAC) የላቀ እመርታ በማሳየት ላይ ነው ። የቻይና እና አፍሪቃ የትብብር ጉባኤ ሲጠናቀቅ ቻይና ለአፍሪቃ 51 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቧ ተሰምቷል ።
ዘጠነኛው የቻይናና ዓፍሪካ የትብብር ጉባኤ በቤጂንግ
ዘጠነኛው የቻይናና ዓፍሪካ የትብብር ጉባኤ በቤጂንግ
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥም ጉባኤውንም ሆነ የቻይናንና አፍርካን ግንኙነት ባጠቃላይ፤ አራያነት ያለው ሲሉ ነው የገለጹት
አበዳሪን ከተበዳሪ ያገናኘው የቻይና አፍሪካ ዘጠነኛ የትብብር ፎረም
አንጎላ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ናይጄሪያ ከቻይና በቢሊዮኖች ዶላሮች በመበደር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናቸው።
አበዳሪን ከተበዳሪ ያገናኘው የቻይና አፍሪካ ዘጠነኛ የትብብር ፎረም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ መሪዎች የሚሳተፉበት ዘጠነኛው የቻይና አፍሪካ ፎረም ዛሬ በቤጂንግ ተጀምሯል። ቻይና ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ዋና አበዳሪ ሆናለች። አንጎላ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ናይጄሪያ ከቻይና በቢሊዮኖች ዶላሮች በመበደር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናቸው።
የረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን፤ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
የሁለቱ የምዕራብ አፍሪቃ ጎረቤታሞች ፍጥጫ
ከንግዱ ውዝግብ በስተጀርባ ያለው ምን ይሆን? የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ECOWAS) ወታደራዊ ኹንታውን በማውገዝ በኒዤር ወታደራዊ መንግሥት ላይ ማእቀብ ጥሏል ።
የዓለም ዜና፤ ግንቦት 8 ቀን፣ 2016 ዓ.ም
-ፑቲን፤ ቻይና በዩክሬን ውስጥ ላለው ጦርነት መፍትሄ ለማፈላለግ ስለመሞከርዋ አመሰገኑ። ፑቲን ይህ የተናገሩት ለሁለት ቀናት ጉብኝት መዲና ቤጂንግ ዛሬ ማለዳ ከገቡ በኋላ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የታሰሩበትን ሊቀመንበ ጨምሮ የኅሊና እስረኞች ያላቸው ሌሎች ታሳሪዎች ሁሉ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ይፈቱ ሲል ጠየቀ። በኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጥላ ሥር የሚገኙ፤ 367 ሲቪል ድርጅቶች፤ ሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግስታዊነት ብሎም የሀብት እና የሥልጣን ክፍፍል፤ ዋነኛ የሀገራዊ ምክክር ጉዳዮች እንዲሆኑ ጠየቁ።
ያሻቀበው የዓለማችን የጦር መሣሪያ ግዥና ክምችት
በጎርጎሮሳዊው 2023 በዓለማችን ለጦር መሣሪያ ግዥ የወጣው ገንዘብ ከቀደሙት ዓመታት በ7 በመቶ ማደጉን ዓለም አቀፉ የሰላም ጥናት ተቋም በምህጻሩ SIPPRI አስታውቋል።
ኢትዮጵያ የዕዳ ክፍያ እፎይታዋን ለማዳን የአይኤምኤፍ ባለሙያዎችን የጉብኝት ውጤት ትጠብቃለች
የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎችን ሥምምነት የሚጠባበቀው የዕዳ ክፍያ እፎይታ “ዋጋ ቢስ” የመሆን ሥጋት ተጋርጦበታል። ኦፊሴያል አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ የሰጡት እፎይታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት 1.5 ቢሊዮን ዶላር በዓመት የሚያድን ነው። ለአንድ ሣምንት የተደረገው የአይ.ኤም.ኤፍ. ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ጉብኝት ከዕዳ ክፍያ እፎይታው በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ በጠየቀችው 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ላይ ጭምር ተጽዕኖ ይኖረዋል።
አሜሪካ ቲክቶክን ለምን ማገድ ፈለገች?
የቻይና የመኪና ገበያ በአውሮጳ መስፋፋት
በዓለም ከፍተኛው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መኪኖች ፋብሪካ 3,000 መኪኖችን ወደ ጀርመን ብሬመርሀቨን ወደብ መላኩ አውሮጳ ውስጥም ገበያው መስፋፋቱን ያመለክታል።
የጥር 30 ቀን 2016 የዓለም ዜና
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሥራት ላይ የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነሕ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ታዬ አጽቀሥላሴ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከአምስት ዓመታት ገደማ በፊት በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የተፈረመውን ሥምምነት አፍርሷል ሲል ከሰሰ። ከቱኒያዝ የባሕር ዳርቻ ጀልባ ሰጥማ ሕይወታቸውን ያጡ 13 ሱዳናውያን አስከሬን ተገኘ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ወደምትገኘው ራፋ ለመግባት እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጡ።
ኢትዮጵያ በይፋ ብሪክስን ስትቀላቀል ባለሙያዎች ስለ ፋይዳው ጥርጣሬ ገብቷቸዋል
የብሪክስ መስፋፋት ተጽዕኖውን እንደሚያሳድገው ቢታመንም ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ለሀገራቸው በሚኖረው ፋይዳ ላይ ጥያቄ አላቸው።
ዕዳ መክፈል ከተሳናቸው ሀገራት ጎራ የተመደበችው ኢትዮጵያ ከቦንድ ባለቤቶች እየተደራደረች ነው
መንግሥት እና የኢትዮጵያ ቦንድ ባለቤቶች በወለድ እና ዕዳ አከፋፈል ላይ እየተደራደሩ ነው። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሁሉም አበዳሪዎች እኩል መስተናገድ አለባቸው በሚል አቋማቸው እንደጸኑ ነው
የኢትዮጵያ የዕዳ ክፍያ እፎይታ ከIMF ጋር በሚኖራት ሥምምነት እጣ ፈንታ ላይ የተንጠለጠለ ነው
የዋጋ ንረት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረት የበረታባት ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ የሁለት ዓመት የዕዳ ክፍያ እፎይታ አግኝታለች። ሥምምነቱ ለኢትዮጵያ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት ለነዳጅ መግዣ ብቻ ያወጣችው 4 .1 ቢሊዮን ዶላር ከዕቃዎች የወጪ ንግድ ካገኘችው የበለጠ ነው
ለሊቲየም የሚደረገው ሩጫ በአፍሪካ ሙስናን እያባባሰ ነው?
ዚምባብዌ ሊቲየም ለዓለም ገበያ የምታቀርብ ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ፣ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ እና ርዋንዳ የሊቲየም ቁፋሮ ጀምረዋል፤ አሊያም ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው
የቻይና «መቀነትና መንገድ» ምን ይዟል?
ቻይና «መቀነትና መንገድ» የሚል ስያሜ በሰጠችው ግዙፍ ፕሮጀክት 3ኛ ጉባኤ ላይ ለመምከር የ130 አገሮች መንግስታት እና ተወካዮችና ከ1000 በላይ ተሳታፊዎች ቤጂንግ ተገኝተው ነበር ።
ኢትዮጵያ ከቻይና አበዳሪዎቿ “የዕዳ ጫና ለመቀነስ” እንድትደራደር መወሰኑን አሕመድ ሽዴ ተናገሩ
የቻይናው መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተነጋገሩ በኋላ የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ “ያለባትን የዕዳ ጫና ለመቀነስ” ከቻይና የፋይናንስ ተቋማት እንዲደራደር መወሰኑን አቶ አሕመድ ገልጸዋል
«ዘላቂ የሆነ ሥልታዊ ትብብር» ቻይና፥ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያና ቻይና ትብብር አዲስ ምእራፍ
ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ከቻይናው መሪ ዢ ቺፒንግ ጋ ቤጂንግ ውስጥ ዛሬ ስለሁለቱ ሃገራት ላቅ ያለ ትብብር መነጋገራቸውን ከቻይና የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል ።
የአፍሪቃ የብድር እፎይታን አራዛሚ ቻይና ወይንስ አሜሪካ?
የእዳ እፎይታ በአዳጊ ሃገራት ላይ የሚፈጥረው ሰቆቃ በመጠኑም ቢሆን እየቀነሰ ይመስላል ። ዓለም በጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ እንዳይሰጥ ቻይና እንቅፋት ተደርጋ ተወስዳለች ። ቻይና ምዕራባውያን ተ
ህንድ የምታስተናግደው የቡድን 20 ጉባኤ
የወቅቱ የቡድኑ ፕሬዝደንት ሕንድ ጉባኤውን ለማስተናገድ ዝግቶግቷን አጠናቃ እንግዶቹን እየተቀበለች ነው።
ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት "የተጋነነ ነገር" መጠበቅ የለባትም
ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት "የተጋነነ ነገር" መጠበቅ የለባትም
ከኤኮኖሚው ዓለም፦ ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት "የተጋነነ ነገር" መጠበቅ የለባትም
የብሪክስ የሦስት ቀናት ጉባኤ ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ ጀመረ
የብሪክስ የሦስት ቀናት ጉባኤ ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ ጀመረ
ብሪክስ ጉባኤ፦ በአፍሪቃ እንዴት ይታያል?
ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥዩም Mantegaftot Sileshi
ብሪክስ ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ደቡብ አፍሪቃ ጆሐንስበርግ ውስጥ ይሰበሰባል ። ሆኖም የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በጉባኤው ላይ አለመገኘት ምን ይፈጥር ይሆን?
ቀዳሚ ገጽ
ገጽ 1 የ 6
ቀጣይ ገጽ