በጀርመን የኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ አሳሳቢ ሆንዋል
ረቡዕ፣ ጥቅምት 18 2013ማስታወቂያ
የጀርመን መንግሥት በሃገሪቱ የኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ ስርጭት ማቆምያ የታጣለት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲል አስጠነቀቀ። የጀርመን ኤኮኖሚ ሚኒስትር ፔተር አልትማየትር እንደተናገሩት በሃገሪቱ በአዲስ እየተዛመተ ያለዉ የኮሮና ወረርሽኝ መጠን ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነዉ። እንደ ኤኮኖሚ ሚኒስትሩ እስከሳምንቱ መጨረሻ በጀርመን በ24 ሰዓት ዉስጥ 20 ሺህ ሰዉ በኮሮና ተኅዋሲ መያዙ ይረጋገጣል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በጀርመን የተዛማች ተኅዋሲዎች የምርምር ተቋም « ሮበርት ኮህ » ዛሬ ይፋ እንዳደረገዉ፤ በጀርመን በ24 ሰዓት ብቻ 11,409 ሰዎች በኮሮና ተኅዋሲ መያዛቸዉ ተረጋግጦአል። ከአንድ ሳምንት በፊት በጀርመን በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮሮና የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር 6868 ብቻ ነበር። በሃገሪቱ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ የሚኒስትር መስርያ ቤቶች በቀጣይ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ እየጠየቁ ነዉ።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ