የኢትዮጵያውያን ድጋፍ ለኮሮና መከላከል ዘመቻ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 2012ማስታወቂያ
በጀርመን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ተህዋሲ ወረርሽኝን ለመከላከል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ላቋቋመው የኮረና በሽታ መከላከያ ግብረሃይል እንስቃሴ ድጋፍ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ልገሳ መጀመራቸው ተገለፀ:: በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል አቶ ፈቃዱ በየነ ለዶይቼ ቨለ "DW" እንዳብራሩት በቅርቡ በመላው ጀርመን ከሚገኙ የተለያዩ የዕምነት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ የማህበራት አደረጃጀቶች እና ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች የተውጣጣ ኮሚቴ በማዋቀር ተከታታይ የቴሌ ኮንፍረንስ ውይይቶችን በማካሄድ ወቅታዊ መረጃዎችን ከመለዋወጥ ጀምሮ ልዩ ልዩ የቁሳቁስና የገንዘብ ልገሳ ከኢትዮጵያውያን እየተበረከተ ይገኛል ብለዋል :: ኮሚቴው በጀርመን በተህዋሲው የተያዙ ኢትዮጵያውያን ካሉ የጤንነታቸውን ሁኔታ ተከታትሎ ለመርዳት አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርግም ነው አቶ ፈቃዱ ጨምረው ያብራሩት:: ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ