በጀርመን መራኄ መንግስት ፍሪድሪሽ ሜርስ ሹመት የታየው ድንጋጤና እፎይታ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 29 2017የጀርመን ፓርላማ ትናንት ባልተለመደ ሁኒታ የጀርመን ክርስቲያን ዲሞክራት የመሀል ቀኝ ፓርቲ መሪ የሆኑትን ፌረዴሪሽክ ሜርዝን የጀርመን ቻንስለር አድርጎ ሹሟል። ጀርመን በተለይ ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በከፍተኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መቆየቷ የሚታውቅ ሲሆን፤ ባለፈው የካቲት በተደረገው ምርጫ አሸናፊ ሆነው የወጢት የክርስቲያን ዲሞክራቶቹ ህብረት ፓርቲ ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ጋር የጥምር መንግስት ለመመስረት ተስማምተው ነበር ሚስተር ሜርዝን በትንናቱ ፓርላማ ሹመቱን ለማስጸደቅ ያቀረበው። በፓርላማው አብላጫ ድምጽ ባላቸው ተጣማሪ ፓርቲዎች አባላት የተማመኑት ሜርዝ ሚኒስትሮቻቸውን ሰይመው፤ አጀንዳቸውን ቀርጸው ሹመታቸውን ሲጠባበቁ ያጋጠማቸው ግን በጀርመን ታሪክ ተስመቶና ታይቶ የማይታወቅ አስደንቃጭ ክስተት ነበር፤ፍሪድሬሽ ሜርስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆኑ
የድንጋጤ -እፎይታ ምክኒያቶችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች
በሚያምኗቸው የተወሰኑ የፓርላማ አባላት ድምጽ መነፈግ። እነማን እንደሆኑ የማይታወቁ ግን ከተጣማሪዎቹ ፓርቲዎች ውስጥ የሆኑ ቢያንስ ስድስት አባላትላት ድምጽ ነስተዋቸዋል፡፤ሁኔታው የጀርመንን ቀርቶ ያውሮፓን ፖለቲካ ያናወጠ ትልቅ ክስተት ሆኖ ነበር።ወዲያው ፓርላማው እንደገና ተሰብስቦና ዳግም ምርጫ እድርጎ ሜርዝ አብላጫ ድምጽ እንዳገኙና አስረኛ ያአገሪቱ ቻንስለር ሆነው መሾማቸው ሲገለጽ ለብዙዎች በተለይም በበርሊን ብራስልስና ፓሪስ ትልቅ እፎይታ ሆነ። ቻንስለሩም ወዲያው ቃለ መሀላ ፈጽመው ሀላፊነቱን የተረከቡ መሆኑን በመግለጽ የተፈጠረው ክስተት ከስራቸው እንደማያደናቅፋቸው አስታወቁ ።
ያውሮፓና ሌሎች አገሮች መሪዎች አስተያየቶችና መልክቶች
የፈርንሳይና ብራስልስ መሪዎችም ወዲያውኑ ነበር እፎይታ ደስታቸውን የገለጹት። የፈርንሳዩ ፕሪዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ በአውርፓ አጀንዳዎች የጀርመንና ፈረንሳይ ሽርክና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት በመግለጽ የደስት መልእክታቸውን ሲያስተላለፉ፤ የአውሮፓን በተለይም የጅርመንን ድጋፍ በዕጅጉ የሚሹት የዩክሬኑ ዘለንስኪም በሜርዝ ሹመት እፎይታ እንዳገኙና እንደተደሰቱም ቀድመው አስታውቀዋል።
የጀርመን ፓርላማ ውሎ የፈጠረው ስሜት
በአጠቃላይም የዶቪለ የብራስልስ ዘጋቢ ሮሺ ብሪቻርድ እንደምትለው የትናንትናው የጀርመን ፓርላማ ውሎ ለአውሮፓ ከተሞች የድንጋጤና የእፎይታም ቀን ነበር፤ “ ሜርዝ በፓርላማው ሳያልፉ ቀሩ ሲባል ከፍተኛ ድንጋጤ የነበር ሲሆን፤ እንደገና ተሾሙ ሲባል ደግሞ እፎይታና ደስታ ሆነ” በማለት በራስልስና ስትራስቡርግ ባጭር ግዜ የተፈራረቁትን ስሜቶች ገልጻለች።10ኛው የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ
ጀርመን የምታስፈልግበት ወሳኝ ወቅት
አውሮፓ በአሁኑ ወቅት በዩክሬን ጦርነት ምክኒያት ከሩሲያ ጋር ተፋጦና የደህንነት ስጋት ተጋርጦበት ያለ በመሆኑ፤ ከአሜሪካ ጋርም በፒሬዝድናት ትሯምፕ ፖሊሲ ምክኒያት በንግድ ጦርነት ውስጥ በመሆኑ፤ የህብረቱ ትልቋ ኢኮኖሚና ሀይል የሆነችው ጀርመን አመራር በእጅጉ ያስፈልጋል ይጠበቃልም። በዚህም ምክኒያት የህብረቱ ዋና ከተሞች በሙሉ ወደ በርሊን አንጋጠው እንደሚያዩ ነው የፖለቲካ ንትንታኖች የሚናገሩት። ቻናስለር ሜርዝ ቀደም ብሎ ይሁን ትናንት ስልጣናቸውን እንዳረጋገጡ አገራቸውን ከገባችበት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ላማላቀቅና ጠንክራ አውሮፓን ለመገንባት ጥረት እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፤ ሆኖም የትናንትናው ጀርመን ፓርላማ ውሎና የሜርዝ መውረድና መውጣት በዙ የሚናገረው ነገር እንዳለና ቻንስለሩ ሊያጋጥሟቸው እይሚችሉትን ችግሮች የሚጠቁሙ እንደሆኑ ነው ባለሙያዎች የሚናግሩት። የዶቸቬለኢው ሮዚ ብሪቻርድ እንደምትለውም የትናንትናው ውሎ ለቻንስለሩ ጥሩ ጅማሮ አልነበረም ።
የዲሞክራሲ ጥምረት የተሰኝ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መሪ የሆኑት ኦላፍ ቦሃንከ በበኩላቸው፤ የትናንትናው ክስተት ለአዲሶቹ ፖለቲካኞችና ሿማምንት ማስጠንቀቂያና ትምህር ሰጭ ነው የሚሉት፤ “ የተፈጠረው ክስተትና የታየው ሁኔታ ላዲሶቹ ሚኒስትሮችና ለተጣማሪ ፓርቲዎቹ ባጠቃላይ፤ ትምህር የሚስጥና ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስታውስ ነው” በማለት ፖለቲከኖቹ ቆም ብለው ሊያስቡና ሊያስተንትኑ እንደሚገባቸው የሚጠቁም መሆኑን ገልጽዋል።
በፓርላማው ውሎ የታየው ክስተት አንደምታ
ቻንስለር ሜርዝና ፓርቲያቸው የተፈጠረው ክስተት በዕቅድና ስራቸው ላይ ተጽኖ እንደማይኖረውና የፖለቲካና ኢኮኖሚ አጀንዳዎቻቸውን እንደሚያስቀጥሉ እየገለጹ ቢሆንም፤ የትናንትናው ክስተት ግን ከሁሉም በላይ ሜርዝ ከዋና ተቃዋሚያቸው አማራጭ ለጀርመን አክራሪ ፓርቲ በተጨማሪ ከተጣማሪዎቹ ፓርቲዎችና ከራሳቸው የክርስቲያን ዴሞክራቶቹ ፓርቲዎች ሳይቀር ተቃውሞ እንዳለባቸው የሚጠቁም፤ መጭው የስራ ዘመናቸውም በርክታ ተግዳሮቾቶች ያሉበት መሆኑን የሚያሳይ ነው የሚሉት በርክታ የፖለቲካ ተነታኞች
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ