በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት በዓል አክባሪዎችን እወከ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2017የትንሳኤን በአልን ከየ ቤተሰቦቻቸዉ ጋር ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አማራ ክልል የሚጓዙ የአማራ ክልል ተወላጆች ወደክልሉ መሔድ እንዳልቻሉ አስታወቁ።በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩት የአማራ ክልል ተወላጆች ፋሲካን የመሳሰሉ በዓላትን ከየወላጅ-ቤተሰቦቻቸዉ ጋር ያከብሩ ነበር።ዘንድሮ ግን በመንግሥት ፀጥታ ኃይላትና በፋኖ ታጣቂዎች የሚደረገዉ ዉጊያ ጉዟቸዉንም ልምዳቸዉንም እንዳስተጓጎለባቸዉ ይናገራሉ። ለደህንነታቸዉ ሲሉ ስማቸዉ እንዲገልፅ ያልፈለጉ ተጓዞች እንደሚገልፁት በክልሉ የተለያዮ አካባቢዎች በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል በሚካሄደዉ ጦርነት የተነሳ እንደበፊቱ በአልን ከቤተሰቡ ጋር ማሳለፍ እንዳልተቻለ ነዉ የሚናገሩት
<እስከዛሬ እንሄድ ነበር አሁን ግን መኪናም መግባትም አይችልም ይሄኛዉ ሲወጣ ይሄኛዉ አያስገባም ስለዚህ ላለመሄድ ወስነናል ያዉ ቤተሰብ መቅበር እንዃን አልቻልንም እስከዛሬ ቀብረን እንዃን መመለስ እንችል ነበር አሁን መመለስ አይደለም መድረስ እንዃን አልቻልንም እናትና አባቴ እዛዉ ናቸዉ ከሄድን ቆየን አሁን እንደሞትን ነዉ የሚቆጠረዉ ምክንያቱም ቆይተናል አይደለም ለማክበር መቅበር እንዃን አልቻልንም>
የትንሳኤ በአልን ለማክበር መነሻዉን ኮምቦልቻ ከተማ አድርጎ ወደ በቅሎ ማነቂያ መዳረሻዉን ያደረገዉ ወጣት መንገዱ ከፍተኛ ፍተሻ ያለበትና አድካሚ ቢሆንም ሰቀላና ድልብ በተባሉ አካባቢዎች በነበረ ተኩስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉደ ቤተሰቦቹ መድረሱን ይገልፃል
<ከኮምቦልቻ ነዉ የተነሳሁት ቤተሰብ ጋር የትንሳኤን በአል ለማክበር ያዉ በመንገድ ላይ ስንመጣ ፍተሻ አለ ፍተሻዉ ላይ በጣም ሰዉ ያሰቃያሉ ከወልድያ ወደ በቅሎ ማነቂያ ነበር የምንመጣዉ ሰቀላና ድልብ ላይ ተኩስ ነበር ባስቸጋሪ ሁኔታ ነዉ ያለፍነዉ>
በፍኖ ታጣቂዎችነና በመንግስት መካከል ግጭትን ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል አንዱ የሆነዉ የሰሜን ወሎ ግዳን ወረዳን መዳረሻ አድርጐ የተነሳዉ ወጣትም ከወልድያ ከተማ ተነስቶ ሙጃ ከተማ በሰላም ቢደርስም ከዚያ በኃላ ወደ ይባር ለመሄድ ትራንስፖርት በማጣታችን በእግር መጓዙ ለደህንነታችን አስጊ በመሆኑ ትንሳኤን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ የነበረዉ እቅድ እንዳልተሳካ ይናገራል
<ከወልድያ ተነስቸ ወደዚያ ሄጀ ነበር አሁን እዛ ስደርስ በእግር ነዉ ትራንስፖርት እስከዛሬ ሲንቀሳቀስ ነበር አሁን በጦርነቱ ምክንያት መንቀሳቀስ አልቻልንም በእግራችን ይደክማል ለመሄድ ፍላጎት ነበረን ለመመለስ አስቸጋሪ ነዉ የአራት አምስት ሰአት ጉዞ ነዉ በግር የምንሄደዉ ይባር አለ ባጃጅ ይሄድ ነበር እዛ እንዳይሄድ እነሱም እየቀረፁ ስለሚያስቸግሮቸዉ አይሄዱም ትራንስፖርት አቁሞል በተለይ በዚህ ወር በጦርነቱ ምክንያት መሄድ አንችልም ከወልድያ ተነስተን ግዳን ስንደርስ ከዚያ በኃላ በእግር ነዉ ትራንስፖርት የለም እነሱ እንዳይመጣ አግደዋል በአልን እናከብራለን ብለን ነበር መንገድ ተዘጋብን አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነዉ ያለነዉ አሁን>ለመጀመሪያ ጊዜ የትንሳኤ በአልን ከቤተሰብ ዉጭ ለማክበር እንደተገደደች የምትናገረዉ መንገደኛም ህፃናት ልጆችን ይዛ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ መጓዝ ከባድ በመሆኑ በአሉን ባለችበት ቦታ ለማክበር ማሰባን ትገልፃለች
<አሁን በጣም አስቸጋሪ ነዉ እስከዛሬ እየሄድን አመት አልፎን አያዉቅም ነበር የትንሳኤ በአልን ከቤተሰቦቻችን ጋር ነበር የምናሳልፈዉ ዘንድሮ ግን በቃ ካለንበት ቦታ ተነስተን ሰሜን ወሎ ነዉ አካባቢያችን በጣም ይከብዳል ልጂ ይዜ ነዉ የምሄደዉ ደርሰን ለመመለስ እርግጠኛ አይደለንም ህፃን ልጂ ተይዞ በጣም ይከብዳል>
በአብዛኛው ደቡብ ወሎ፣ በተወሰኑ የሰሜን ወሎ እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ኤሌክትሪክ ተቋርጧልበተኩስ መሀል ያሰብኩት ቦታ ደርሸ ከቤተሰብ ጋር በአልን ማክበር አስደሳች ቢሆንም ምንም ደህንነት በማይሰማበት መንገድ መጓዝ ደግሞ ሌላዉ ችግር ነዉና ጉዞችን በፍራት የተሞላ ነበር ይላሉ<የትንሳኤ በአል በየአመቱ ብንሄድ ደስ ይለን ነበር ግን ሰላም ስሌለለ ዛሬም እራሱ እየፈራን ነበር የሄድነዉ ያዉ እንደፈራነዉ መንገዱ ሰላም ስላልሆነ እንደፈለግን መንቀሳቀስ ስለማንችል ብዙ ጊዜ አንሄድም ዛሬም እየፈራን መጣን አሁንም ቢሆን ሰላም የለምና በአስቸጋሪ ሁኔታ ነዉ ቤታችን የገባነዉ ተኩስ ነበረ አስቸጋሪ ነዉ>
ኢሳያስ ገላዉ
ነጋሽ መሐመድ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር