ጀነራሉ ከስልጣን እንዲወርዱ ተጠየቀ
ቅዳሜ፣ ሐምሌ 19 2017ማስታወቂያ
ሰሞኑ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪዎች ነባሮቹን ሽሮ አዳዲስ መሾሙ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ የዞኑ ነዋሪዎች ዘንድ ከባድ ቁጣን ቀስቅሶ ለአደባባይ ሰልፍ አብቅቷቸዋል። የዞኑ የሐገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት መሪዎች ሽም ሽሩን በመቃወም ለትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ለጄኔራል ታደሰ ወረደ አቤቱታ አቅርበዉ ነበር።ፕሬዝደንቱ ከሐገር ሽማግሌዎቹና ከሐይማኖት መሪዎቹ ጋር በዝግ ያደረጉት ዉይይት ያለውጤት ተበትኗል። የደቡባዊ ዞን ሕዝብ ደግሞ የዞኑ ነባር አስተዳዳሪዎች በአዳዲስ መተካታቸዉን በመቃወም በማይጨዉ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ነባሩን የዞን አስተዳዳሪያቸውን አጅበው ወደቢሮው እንዲመለስም አድርገዋል ነው የተባለው። ይህን ተከትሎም የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ወደ ማይጨው ማቅናታ,ውን ሰምተናል። በሌላ ዜና የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ባወጣው መግለጫ የክልሉን ችግር መፍታት አልቻሉም ያላቸውን ፕረዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ጠይቋል። ይህን አስመልክተን የመቐለው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለሥላሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬዋለሁ። ሙሉ ጥንቅሩን የማድመጫ ማዕቀፉን ተጥነው ያዳምጡ።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴን
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር